የዘመራ ራዲዮ ሳምንታዊ ዜና 11,ህዳር,2018

የሦስቱ ሀገራት መሪዎች በቀጠናው ሰላምና ደህንነት ዙሪያ አብሮ ለመስራት መስማማታቸውን ገለጹ፣ ከ40 በላይ የሜቴክና የደኅንነት አባላት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ፖሊስ አስታወቀ፣ በካፋ ዞን ቦንጋ ከተማ ህዝባዊ የተቃውሞ ሰልፎች ተካሄዱ፣ በሁለት ኢምባሲዎች በኩል 30 ሚሊዮን ዶላር ግምት ያለው እቃ ከውጭ አገር ወደ ኢትዮጵያ መግባቱን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታውቋል። ዝርዝሩን ያድምጡ […]

የዘመራ ራዲዮ ሳምንታዊ ዜና 04, 11, 2018

ወሮ ብርቱካን ሚደቅሳ ከመንግስት በተደረገላቸው ጥሪ የፊታችን ሃሙስ ለሹመት ወደ አገር ቤት እንደሚገቡ ተዘገበ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ለ3 ቀናት ያካሄዱት የአውሮፓ ጉብኝት ስኬታማ ነበር ተባለ፣ በምዕራብ ኦሮሚያ በኦነግ ስም ህዝቡን እያሸበሩ ያሉ ሃይሎች በአፋጣኝ ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ የክልሉ ፕሬዚዳንት አሳሰቡ፣ በኢየሩሳሌም የሚገኘውን ዴርሱልጣን ገዳምን መንግስት እንዲታደገው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ […]

በአማራ ክልል በተለያዩ ከተሞች ህዝባዊ የተቃውሞ ሰልፎች ተካሄዱ

በባህር ዳር፣ደብረታቦር፣ደሴ፣ወልዲያ፣ደብረማርቆስ፣ሰቆጣና በሌሎች በርካታ የክልል ከተሞች የራያና ወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄ ምላሽ እንዲያገኝ እንዲሁም ጣና ሐይቅና ላሊበላ ውቅርአብያተ ክርስቲያን የተደቀነባቸውን አደጋ መግስት አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጥ የሚጠይቅ ነው፡፡በተለይም ሰሞኑን የራያና አላማጣ ነዋሪዎች አደባባይ በመውጣት የፌዴራል መንግስት ለጥያቄቸው ምላሽ እንዲሰጥ በጠየቁበት ወቅት የትግራይ ልዩ ሀይል ፖሊስ ከ10 በላይ ሰዎችን መግደሉ […]

Zemera radio Weekly News 28,Oct,2018

የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ በኖርዌይ ጤናማና ውጤታማ ማንነት የተሰኘ መፀሃፍ አስመረቀ፣ ህገ-ወጥ ወታደራዊ ስልጠና በጫካ ውስጥ ሲሰጡ የነበሩ 10 አሰልጣኞች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለፀ፣ በአማራ ክልል በተለያዩ ከተሞች ህዝባዊ የተቃውሞ ሰልፎች እየተካሄዱ ነው፣ በሐረር ከተማ እየተስተዋለ ያለው የመጠጥ ውሃ እጦት የህግ የበላይነት ባለመከበሩ ምክንያት መሆኑን የሐረሪ ውሃ እና ፍሳሽ ባለስልጣን፣ […]

በወንዶች ጥረት ብቻ የተገነባ አገርም ሆነ ቤተሰብ የለም!!ሴቶች የቤተስብም የሃገርም ምሶሶ ናቸው!!

ኢትዮጵያ አራተኛዋን ፕሬዘደንት መረጠች!!የኢትዮጵያ የመጀመሪያዋ ሴት ፕሬዝዳንት ክብርት አምባሳደር ሳህለወርቅ ዘውዴ ሆነዋል!! የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያለ ድምፅ ተዓቅቦ በሙሉ ድምፅ ሥልጣኑን አፅድቆላቸዋል፡፡በበአለ ሲመታቸውም ላይ ከተናገሩት የሳበኝን እንዲህ ያሉት ነው የጀመርነው የለውጥ ጉዞው ውስብስብ እና በርካታ ፈተናዎች ያሉበት እንደሚሆን ይጠበቃል። እንዚህን ፈተናዎች አንዱ ሲገነባ አንዱ በማፍረስ ሳይሆን አንዱ […]

ታላቅ ሀገራዊ ጥሪ !

➨ ለኢትዮጵያዊያን መሀንዲሶች ፣ ለአርክቴክቶች ፣ ለስራተቋራጮች (ኮንትራክተሮች )፣ ለአማካሪ መሀንዲሶች ፣ ለቅርስና አርኪኦሎጂ ተመራማሪዎች ና ለዩኒቨርሲቲ ምሁራኖች በሀገራችን የህንፃ ጥበብና አሰራርን ከላይ ወደታች በመስራት ከአንድ ወጥ ድንጋይ የተሰራው ላሊበላ ከ900 አመት በላይ አገልግሎት የሰጠ ፣ ከሀገራችን አልፎ በአለም ቅርስነት የተመዘገበው የላሊበላ ውቅር አቢያተ ክርስቲያን እኛ ኢትዮጵያዊያን መሀንዲሶች […]

የለውጥ ሀይሉ እውነተኛ ከሆኑ ስራቸውን ይስሩ እኛም ስራችን እንስራ

በ ርዕዮት አለሙ የለውጥ ሀይሉ እውነተኛ ከሆኑ ስራቸውን ይስሩ እኛም ስራችን እንስራ:: ማገዝ የሚለውን ቃል አልወደውም :: ምንድን ነው ማገዝ ማለት ለመሆኑ ? እኔ እኮ ኢትዮጵያ ሀግሬን ዲሞክራሲያዊ ለማድረግ ድሮ ያኔ ለትግል ስነሳ ዶር አብይ የሚባል ሰው ከነመፈጠሩም አላውቅም :: የ ትግሌ አላማ እና ግብ ዶር አብይን ለማገዝ […]

ኢሕአዴግ በቀጣዩ ምርጫ ያሸንፋል? (በዶ/ር ተክሉ አባተ)

ሀዋሳ በተካሄደው የኢሕአዴግ 11ኛ ጉባኤ ዶ/ር ዐቢይ ከ177 ድምጾች ውስጥ 176ቱን በማግኘት የኢሕአዴግ ሊቀ መንበርነታቸውን አስጠብቀዋል። ዶ/ሩ እንደሚያሸንፉ ብዙ ኢትዮጵያውያን ሲገምቱ ነበርና ውጤቱ ብዙም አላስደነቀም። የእርሳቸውን ያህል አቅምና የሞራል ልዕልና ያለው ሰው እስካሁን ድረስ ከኢሕአዴግ ውስጥ አላየንምና! ይልቁንስ ብዙ ያወያየ የምክትሉ የአቶ ደመቀ ጉዳይ ነበር። እርሳቸውም 149 ድምጽ […]

ኢትዮጵስ ጋዜጣ፣ መስከረም 27/2011 ዓ.ም

ኢትዮጵስ፦ ወደ ወቅታዊው የሀገራችን ሁኔታ እንግባና፣ በዶ/ር አብይ የመደመር ስሌት፣ እርሰዎ የትኛው ዛቢያ ላይ ነዎት? የዶ/ር አብይን አመራር ያምኑበታል? ዶ/ር ታዬ፦ ጥርጣሬ አለኝ። ፊት ለፊት እናገራለሁ። ይሄን ሁለተኛው ምዕራፍ ነው የምለው። አንደኛው ምዕራፍ፣ አሜሪካኖች ወያኔን ያስገቡበት ድራማ ነው። በሁለተኛው ምዕራፍ፣ የወያኔ ስርዓት በወጣቱ ትግል ሲወድቅ፣ አዲስ ነፍስ ዘርቶ […]

የዘመራ ራዲዮ ሳምንታዊ ዜና መስከረም 30, 2018

የኢሬቻ በዓል በቢሾፍቱ እየተከበረ ነው፣ የተሻለ ሀሳብ ከቀረበ በስራ ላይ ያለውን ሰንደቅ አላማ ለመቀየር መንግስት ዝግጁ መሆኑ ተገለጸ፣ የድሬዳዋ ከተማ የፍትህ ፀጥታና ህግ ጉዳዮች ሀላፊ የነበሩ ያለመከሰስ መብታቸው ተነስቶ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለፀ፣ በአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ የሌለባቸው በህገወጥ መንገድ የተያዙ 500 ቤቶች ተገኙ ተባለ፣ ዝርዝሩን ስለምታዳምጡን እናመሰግናለን