Category: ፖለቲካ

የሳሙኤል አወቀ የግድያ ቅንብር፤ (ከደኅንነት ቢሮ የወጣ)

ከብሔራዊ ደኅንነት አዲስ አበባ ሳሙኤል አወቀ እንዲገደል ትእዛዝ ባሕር ዳር ላለው የደኅንት ቅርንጫፍ ተላለፈ፡፡ ባሕር ዳር ያሉት የደኅንነት ሠራተኞች ሳሙኤል ስለመገደሉ እንጅ ለምን እንደሚገደል በጊዜው የሚያውቁት ነገር የለም፡፡ በሕወሓት በደኅንነት አንድን ኦፕሬሽን አለ አከናውኑ ከተባሉ ያለ ምንም ጥያቄ ኦፕሬሽኑን ማከናወን ነው፡፡ ይህን ኦፕሬሽን ለማከናወን ደረጀ አላምረው የተባለ የደብረ […]

ሽሽት እና አባዱላ ገመዳ

ክንፉ አሰፋ  ከሰሜን እና ከበስተ-ምስራቅ አቅጣጫ እየነፈሰ ያለው አውሎንፋስ መርከብዋን እያናጋት ይገኛል።  ጫፍ ላይ ጉብ  ያሉትን አስተናጋጆች እያንጠባጠበ የሚገፋው ሃይል እየበረታ መጥቶ፣ አሁን ከካፒቴኑ ቁጥጥር ውጭ የሆነ ይመስላል። ይህ ሁላችንንም የሚያስማማን መራራ ሃቅ ነው። ችግሩ እዚህ ላይ አይደለም። ግን… እየሰመጠ ካለው ከዚህ መርከብ ለማምለጥ የተገኘችውን ቀዳዳ እየተጠቀሙ የሚሾልኩትን ሁሉ “ጀግና” ብለን ለመጥራት […]

ኦሮማይ-2፡ ከለውጥ ማዕበል ወደ ብጥብጥ!

ስዩም ተሾመ በሕዝቡ እየተነሱ ያሉ ጥያቄዎች ተገቢ ምላሽ እስካልተሰጣቸው ድረስ ግጭትና አለመረጋጋቱ እየጨመረ ይሄዳል። ይህን የለውጥ ጥያቄ ለማስቆም መሞከር ከትውልድ ጋር ግጭት ውስጥ እንደ መግባት ነው። መንግስት ሕዝቡ እያነሳቸው ላሉት የዴሞክራሲ ጥያቄዎች ተገቢ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ በኃይል ለማፈን የሚደረገው ጥረት ሀገሪቱን ወደ ለየለት ግጭትና አለመረጋጋት ያስገባታል። የኢህአዴግ ባለስልጣናት […]

የአማራ ብሔርተኝነት እንቆቅልሽ (የመቋጫ መጣጥፍ) … በፈቃዱ ዘ ሃይሉ

“የአማራ ሥነ ልቦና” በሚል ርዕስ ቀደም ሲል የጻፍከት አጭር የእንግሊዝኛ መጣጥፍ ብዙ ጥያቄዎችን አጭሯል። የጽሑፉ ዋነኛ ዓላማ ስለአማርኛ ቋንቋ ዕድሜ፣ ወይም ስለአማራ ሕዝብ ኅልውና ባይሆንም፣ ብዙዎቹ አንባቢዎች ግን የተረዱት በዚያ መንገድ ነበር። ወሳኙ ቁም ነገር እኔ የጻፍኩበት ዓላማ ሳይሆን አንባቢ ጋር ሲደርስ የሰጠው ስሜት ስለሆነ ይህንን ጽሑፍ አስከትያለሁ። […]

የማይሻሻል ሕገ መንግስት በመጨረሻ ተቀድዶ ይጣላል

በዓለም ላይ ሁሉም ነገር ይቀየራል። ሁሉም ነገር ሂደቱን ጠብቆ ይለወጣል። በእርግጥ በዓለም ላይ የማይለወጠው አንድ ነገር ነው። እሱም “ለውጥ” ራሱ ነው። ኢትዮጲያ ውስጥ ግን ሁለት የማይለወጡ ነገሮች አሉ። እነሱም “ለውጥ” እና “ሕገ-መንግስት” ናቸው። አሁን ላይ ሀገራችን ከዴሞክራሲና ብሔራዊ መግባባት አንፃር እያሳየችው ላለው የኋሊት ጉዞ ዋናው ምክንያት የእነዚህ የማይለወጡ […]

HR 128/SR 168 ጸሐይ እየጠለቀችበት ነው!

ለኢትዮጵውያን ታላቅ ተስፋ ይዞ የተነሳው HR 128/SR 168 በሞት አፋፍ ላይ እንደሚገኘ ተነገረ። የህወሃት/ኢህአዴግን ህልውና በማያፈናፍን አጣብቂኝ ውስጥ እንደሚከት ብዙ የተባለለት ይህ ረቂቅ ሕግ ወደ ሕግ መወሰኛ ምክርቤት ቀርቦ ድምጽ ከማግኘቱ በፊት ጊዜውን ጠብቆ እንዲሞት የማቀዛቀዝ ተግባር እየተፈጸመበት ነው። ኢትዮጵያውያን ተባብረው በመታገል ይህ ዕድል እንዳያመልጣቸው ማድረግ እንዳለባቸው ማሳሰቢያ […]

እምቢተኝነት በተግባር!

“ሕዝቡን ካፈንከው እና ከመቃወም ሌላ አማራጭ ካሳጣኸው ይፈነዳል፤ ወጣቱ በሙሉ ዓመጽ ላይ ነው፤ ትውልድ አምጿል”። የኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጠኛ JEFFREY GETTLEMAN በኢትዮጵያ ያለው ወቅታዊ ሁኔታ በተነተነበት ጽሁፍ ላይ ከተናገረው። ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ። ዛሬ በተከበረው የመስቀል በዓል ላይ የህወሓትን ማስፈራሪያና ዛቻ ከምንም ባለመቁጠር የውቅሮ፣ ዓዲግራት፣ መቀሌ፣ ጎንደር፣ […]

የከፍታው ዘመን እና የዘር ፖለቲካው ድምር ውጤት

የሰው ልጆች በተለያዩ  መስፈሪያዎች /መለኪያዎች /  ጊዜን ሰፍረዋል ወይም ለክተዋል።እነዚህም መስፈርያዎች ለእለታት  ለዘመናትና  ለአመታት  ምልክት ይሆኑ ዘንድ   የፀሀይንና  የጨረቃን  እንቅስቃሴ  መሰረት ያደረጉ  ሲሆኑ  እነዚህም እለት ፤ ወር  እና  አመት ናቸው። እነዚህን የተፈጥሮ ኩነቶች በመከተልም ዘመን እንቀይራለን የተለያዪ ባእላቶችንም እንደየወቅታቸው  እናከብራለን። ባሳለፍነው ሳምንት የህወሀት አገዛዝ  የአስራ ሶስተኛውን ወር የጳጉሜን […]

ሁሌ እናስታውሳቸው  ተቀብሮ እንዳይቀር አኩሪ ታሪካቸው!በመኮንን ተስፋዪ

ገነት ግርማ ማን ናት???? ባላማዋ ፀንታ እስካሁን በመታገል ላይ የምትገኝ የኢህአፓ ኮከብ!!! የውጭ ወራሪን ለመመከትም ሆነ ለፍትህ፤ ዲሞክራሲና ለነፃነት በኢትዮጵያ ህዝብ በተደረገው ትግል ሴቶች ከወንድ ጓዶቻቸው ጎን ቆመው ያሳዩት መስዋእትነትና ጀግንነት የተሞላው ተሳትፎ በታሪክ መዝገብ ላይ ተፅፎ ሲዎሳ ይኖራል። ጣልያንን ካንበረከከው ከአድዋ ጦርነት በኋላ በሰፊው ሴቶችን ያሳተፈው የካቲት […]