Category: ዜና

75 ህገ-ወጥ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በማላዊ መታሰራቸው ታወቀ

75 ኢትዮጵያዊያንና አንድ ቡሩንዲያዊ ስደተኞች በአምስት ማላዊያን አሽከርካሪዎች በመታገዝ በህገ-ወጥ መንገድ ወደ ማላዊ  ሲገቡ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የማላዊ የኢምግሬሽን መምሪያ ሀላፊ አርብ ዕለት አስታወቀ።    የማላዊ ሰሜናዊ ግዛት የኢሚግሬሽን የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆኑት ብላክዌል ሉንሱ በበኩላቸው 76ቱ ህገ-ወጥ ስደተኞች በሦስት ሚኒባሶች ተጭነው ሲጓዙ በቺዊታ ተራራ አካባቢ መያዛቸውን ገልጸዋል። […]

በምስራቅ ሐረርጌ በኦሮሞና ሶማሌ ልዩ ሀይል ፖሊስ መካከል የተቀሰቀሰው ግጭት እየተባባሰ መሆኑ ተገለጸ

በምስራቅ ኢትዮጵያ በመኢሶን ከተማ አቅራቢያ ከፍተኛ ጦርነት እየተካሄደ እንደሚገኝ ተገለጸ።በኢትዮጵያ ሶማሌና በኦሮሞ ጎሳዎች መካከል በወሰን ምክንያት የተቀሰቀሰው ግጭት ለወራት መዝለቁ የሚታወቅ ሲሆን ባሳለፍነው ሳምንት በርካታ የአካባቢው ነዋሪዎችን ያሳተፈ ጦርነት መካሄዱን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል።የሶማሌ ጎሳዎች ልዩ ፖሊስ እየተባሉ በሚጠሩት ወታደሮች መደገፋቸውን መረጃዎች አመልክተዋል።የጥፋት ሀይል በሆነው በልዩ ፖሊስ በግልፅ በመታገስ […]

በጣና ሐይቅ ላይ የተከስተውን እምቦጭ የተሰኘ አደገኛ አረም ለማስወገድ ዘመቻው ቀጥሏል

በጣና ሐይቅ ላይ የተከሰተው እንቦጭ የተሰኘ አደገኛ አረም ለማስወገድ ህዝባዊ ዘመቻ ተጀመረ። የክልሉ አንዳንድ መስሪያ ቤቶች፤ የባህር ዳር ከተማ ነዋሪዎችና የሐይቁ ተፋሰስ አካባቢ ነዋሪዎች በመቀናጀት አረሙን በእጅ የመንቀል ተግባር እያከናወኑ ነው። አረሙን ለማስወገድ የሚያስችል መሽን በሀገር ውስጥ ተሰርቶ በሙከራ ላይ መሆኑም ተገልጿል። ከሸዋ፣ወሎ፣ጎንደርና ከተለያዩ አካባቢዎች ሀገር ወዳድ ወጣቶች […]

በቀለ ገርባ በካቴና ታስረው ፍርድ ቤት ቀረቡ – ዋስትናቸው ተቀባይነት ሳያገኝ ቀረ

(ዘ-ሐበሻ) የዋስትና ጥያቄያቸው ተቀባይነት ሳያገኝ ፍርድ ቤት ሲመላለሱ የቆዩት እውቁ ፖለቲከኛ አቶ በቀለ ገርባ በዛሬው ዕለት የዋስትና ጥያቄያቸው በፍርድ ቤቱ ተቀባይነት እንዳላገኘ ምንጮች አስታወቁ:: እንደ ምንጮች ዘገባ አቶ በቀለ አንዴ ዳኛ ታሟል ሌላ ጊዜ መዝገብ አልቀረበም የሚሉ አሰልቺ ምክንያት እየተሰጠ የዋስትና ጥያቄያቸው ሲጉላላ የሰነበተ ሲሆን በዛሬው ዕለት ብርቱካናማ […]

የህወሓት መንግስት ግራ መጋባቱ ተጠቆመ ! ! !

ቢቢኤን ነሐሴ 01/2009 በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች እየተካሔዱ ያሉ ህዝባዊ ተቃውሞች በህወሓት ላይ ድንጋጤ መፍጠራቸው ተጠቆመ፡፡ በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች ህዝቡ የስራ ማቆም እና ከቤት ያለ መውጣት አድማ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ የተመለከቱት የህወሓት አመራሮች፣ እንዲህ ያሉ ተቃውሞች መቋጫ ማጣታቸው እንዳሳሰባቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡ ህወሓት የህዝቡን ትኩረት ለመሳብ የተለያዩ የመንግስት የስራ […]

ትግራይ ውስጥ ባሉ የንግድ ድርጅቶች የሚሰቀሉ ታፔላዎች በትግርኛ ቋንቋ ብቻ እንዲጻፉ አዋጅ ተደነገገ

ኢሳት ዜና ትግራይ ውስጥ ባሉ የንግድ ድርጅቶች የሚሰቀሉ ታፔላዎች በትግርኛ ቋንቋ ብቻ እንዲጻፉ አዋጅ ተደነገገ። የትግራይ ክልላዊ መንግስት፤ ማንኛውም የንግድ ማስታወቂያ ታፔላና የግድግዳ ላይ ማስታወቂያ መልዕክቶች በትግርኛ ቋንቋ እንዲፃፉ የሚያዝ አስገዳጅ አዋጅ ሰሞኑን አፀድቆ በስራ ላይ መዋል መጀመሩን አስታወቀ። እንደ አድማስ ዘገባ የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አዋጁን እንዲያስፈፅም […]

ንብረትነቱ የም/ጠቅላይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን ከሆነው ሚሽከን ኮሌጅ ተምረው የተመረቁ ተማሪዎች ከስራ ገበታቸው እየታገዱ ነው ተባለ

ምስል ከፋይል የአገሪቱን ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የገጠመው የጥራት ጉድለት በአገዛዙ ባለሥልጣናት ጭምር መተቸት ጀምሯል። ደመቀ መኮንን የህወሃት አገዛዝ ለይስሙላ ካስቀመጣቸው ጠቅላይ ሚንስትሮች አንዱ የሆነው ደመቀ መኮንን የትምህርት ሚንስትር በነበረበት ወቅት በሸርክና ያቋቋመው ሚሸከን ኮሌጅ በማህበራዊ ሳይንስ የትምህርት መስኮች፤ በማኔጅምንት ፣ በአካውንቲንግ እና በኢኮኖሚክስ ዘርፎች ላለፉት 5 አመታት አስተምሮ […]

የጋምቤላ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ አርነት ግምባር / ጋህዴአግ/ የኦህዴድን የግዛት ማስፋፋት ጥያቄን እንደሚያወግዝ አስታወቀ

የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት / ኦህዴድ / ከጋምቤላ ክልል ጋር በተያያዘ እያካሄደ ያለውን  ማስፋፋት ጥያቄ እንደሚያወግዝ የጋምቤላ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ አርነት ግምባር / ጋህዴአግ / ባወጣው መግለጫ አስታወቀ ። በአሁኑ ጊዜ የኦሮሞም ሆነ የጋምቤላ ህዝብ አንገብጋቢ ጥያቄ የግዛት መስፋፋት አለመሆኑን  ጋህዴአግ  ገልጿል ። የጋምቤላ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ አርነት ግንባር /ጋህዴአግ/ […]

በአዲስ አበባ ጎርፍ ባስከተለው ዶፍ ዝናብ 5 ሰዎች ሞቱ

በአዲስ አበባ ባለፉት ሁለት ቀናት ከፍተኛ ጎርፍ ባስከተለው ዶፍ ዝናብ 5 ሰዎች መሞታቸውን የአደጋ መከላከል ባለስልጣናት አስታወቁ ። በከተማዋ በስተደቡብ ጫፍ ላይ አንድን ወንዝ በመሻገር ላይ የነበሩ 4 ሰዎች በጎርፍ መወሰዳቸውን የአዲስ አበባ የእሳት አደጋ መከላከል ቢሮ ቃል አቀባይ አቶ ንጋቱ ማሞ መግለጻቸውን ዘገባዎች አመልክተዋል ። የቱርኩ የዜና […]