ማህበራዊ

ወይዘሮ ሪታ ፓንክረስት ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

የታዋቂው የኢትዮጵያ ታሪክ ተመራማሪና ፀሐፊ ሪቻርድ ፓንክረስት ባለቤት ወይዘሮ ሪታ ፓንክረስት በ92 ዓመታቸው ከዚህ አለም በሞት ተለዩ፡፡

የፕሮፌሰር ሪቻርድ ፓንክረስት ቤተሰብ በኢትዮጵያ ስነ-ጥበብ፣ ስነ-ህንፃ፣ በቅኝ አገዛዝ ስርዓትና በሌሎች የኢትዮጵያ ታሪክ ላይ ያጠነጠኑ በርካታ መፅሀፍትን አበርክተዋል፡፡

ወይዘሮ ሪታ ፓንክረስት በቀድሞው የአፄ ኃይለስላሴ ዩኒቨርስቲ እና በብሔራዊ ቤተ መጽሐፍት ውስጥ በሞያቸው ሲያገለግሉ ቆይተዋል፡፡

የፕሮፌሰር ሪቻርድ ፓንክረስት ቤተሰብ ለኢትዮጵያ ባላቸው ፍቅርና ለሀገሪቱ ባበረከቱት በጎ አስተዋጽኦ ምክንያት የኢትዮጵያ የክብር ዜግነት ተሰጥቷቸዋል፡፡

ወይዘሮ ሪታ አሉላ እና ሄለን ፓንክረስት የተባሉ 2 ልጆችን ከባለቤታቸው ፕሮፌሰር ሪቻርድ ፓንክረስት አፍርተዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም ከባለቤታቸው ጋር በመሆን ኢትዮጵያ ሬሚነሰንስ (”Ethiopian Reminiscences,’’ ) በግርድፍ ትርጓሜው የኢትዮጵያ ልምድና ታሪካችን የተሰኘ መፅሃፍን አበርክተዋል፡፡

ይህ መፅሃፍ በኢትዮጵያ በፈረንጆቹ በ1950 እና 1960ዎቹ የነበሩ ትልልቅ ህዝባዊ ሁነቶችን የሚሳይ ነው፡፡

ባለቤታቸው ፕሮፌሰር ሪቻርድ ፓንክረስት ከሁለት አመት በፊት በ89 አመታቸው ከዚህ አለም በሞት መለየታቸው የሚታወስ ነው።

Categories: ማህበራዊ

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s