ፖለቲካ

“የምጮኸው ጩኸት በውስጡ ወፍራም እውነት ስላለበትና: ቢያንስ ከዝምታም ስለሚሻል ነው“ የትውልድ እናት ሰዋስው 

አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ! የዚህን ወይም የዛኛውን ብሔረሰብ: ጎሳ: ሐይማኖት ወይም ድርጅትን አባላት ሳይሆን: በአምሳልህ የፈጠርክውን በኢትዮጵያ ምድር እናት አምጣ የወለደችውን የሰውን ልጅ ሁሉ አስብ?

አንዳንድ ግዜ ብቻችንን ስንጮህ ሰሚ ያጣን ሲመስለን: 
“ምናልባት የተሳሳትኩት እኔ እሆንን?“ ብለን ራሳችንን እስከመጠራጠር እንደርሳለን!

ሰዎች ቢያምኑበትም ባያምኑበትም: እኔ ግን ሠማይና ምድርን የፈጠረ እግዚአብሔር እንዳለ አምናለሁ!
ይህ የማምነው እግዚአብሔር :ከሰባት ዓመት በፊት: በሌሊት ከእንቅልፌ አንቅቶኝ: 
“በኢትዮጵያ ውስጥ ትውልድ እንዳያልቅ: ጩሂ ! በአስቸኩዋይም በኢትዮጵያ ውስጥ ብሔራዊ እርቅ እንዲካሄድ መንግሥትን አስጠንቅቂ“ አለኝ::

በዛን ግዜ በኢትዮጵያ ስላለው ሁኔታ በቂ እውቀት አልነበረኝም ነበር:: ነገር ግን ከሠማያት ለመጣልኝ ድምፅ ለመታዘዝ ስል ብቻ ይህንን ጩኸቴን እነሆ ለሰባት ዓመት ሙሉ በጉዋዳም በሚዲያም ከመጮህ አላቁዋረጥኩም!
ለዓለም አቀፉም ለአገር አቀፉም ሕብረተሰብ: ለፖለቲከኛውም ለሐይማኖተኛውም: ለምሑሩም ለመሐይሙም: ለሴቱም ለወንዱም: ለንጉስም ለተራ ግለሰብም:በአደባባይም በጉዋዳም ጮህኩ!

ትንሽ የተስፋ ጭላንጭል ያየሁ ሲመስለኝ ደግሞ ጩኸቴን ጋብ አድርጌ: እግዚአብሔርንም : ለሠላም የሚተጉትንም ሳመሰግን ቆይቼ ሳላበቃ:ከወደ ትውልድ ምድሬ የሚሰማው ነገር እጅግ ያስፈራል:: 
“ለውጥ ሲካሄድ ያለ ነገር ነው“ የሚሉም ድምፆች አልጠፉም: ግን ዕለት ዕለት የሚረግፈው ቅጠል ሳይሆን ሰው ነውና: እንዴት የሰውን ልጅ: ዘጠኝ ወር በማሕፀኑዋ ተሸክማ አምጣ ለወለደች እናት: ዝም የሚያሰኝ አንጀት ከወዴት ይምጣ?

ዛሬም ዕለት ዕለት ትውልድ እንደቅጠል ሲረግፍ :ከየቀዬው ሲፈናቀል: ሰው ሁሉ ፌስቡኩን: የክልሉን: የብሔረሰቡን የጎሳና የመንደሩን ስም እየጠራ:ድርጊቱን ሲያወግዝ: ሻማ ሲያበራ ስመለከት: የቱን ዘር ጠርቼ የቱን እንደምተው: ለየትኛው ሻማ ቢጤ ነገር አብርቼ : የቱን እንደምተው ግራ እስኪገባኝ ድረስ ግራ ተጋባሁ::
RIP እያሉ ከመፃፍና😭 እምባ መሳይ ምስል ከመለጠፍ ያለፈ ጉልበትስ ከወዴት ይምጣ?

ሰው አገሩንም ትውልዱንም ወቅትንም የሚያገለግለው:በአቅሙ በችሎታው: ልቡ በሚቃጠልበትና: በተሰጠው ፀጋ ልክ ነው::

እለት እለት ስለሚረግፈው ትውልድ: ስለሚሰቃዩት ሕፃናት: ግራ ስለሚጋቡ እናቶችና አባቶች: የነገ አገር ተረካቢ ወጣቶች መከራና ግራ መጋባት ስሰማና ስመለከት: ትውልድን እንዳማጠች እናት ውስጤ ያነባል::

ማንም እየተነሳ በጎሳው :አለያም በፖለቲካ ድርጅቱ: በሐይማኖቱ ስም አለያም በግሉ: ሌላውን ወገኑን ለማጥቃት: በመሳሪም በቃላትም በመሐበራዊ ሚዲያውም : ጦር ሲሰብቅ ሲሰማና በተግባርም ሲተገብረው ሲሰማ እስከ መቼስ ችላ ይባላል?

እየሆነ ያለው ጉዳይ ባለቤት “እከሌ የሚባል ዘር ወይም የፖለቲካ ድርጅት አለያም እከሌ የሚባል ግለሰብ ነው“ : ተብሎ እንኩዋን መፈረጅ እስከማይቻል ድረስ: 
ምድሪቱዋም ችግሩዋም መከራዋም: ባለቤት ያጣ እስኪመስል ደርሶአል::

ነገር ግን ይህንን ሸክም እግዚአብሔር ከውስጤ እስኪያወጣው ድረስ: ሰሚም ባላገኝ ዛሬም “ፍትሐዊ ብሔራዊ እርቅ በአስቸኩዋይ!“
እያልኩ መጮሄን አላቁዋርጥም: 
ምክንያቱም የምጮኸው ጩኸት: በውስጡ እጅግ ወፍራም እውነት ስላለበትና “ቢያንስ ከዝምታ ይሻላልና“ ነው::

አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ! የዚህን ወይም የዚያን ጎሳ አለያም ሐይማኖት ተከታይ ሳይሆን:
በአምሳልህ የፈጠርክውን ሕዝብህን አስብ?
የትውልድ እናት ሰዋስው
ከሠሜን ዋልታ

Categories: ፖለቲካ

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s