ዜና

በአማራ ክልል በተለያዩ ከተሞች ህዝባዊ የተቃውሞ ሰልፎች ተካሄዱ

በባህር ዳር፣ደብረታቦር፣ደሴ፣ወልዲያ፣ደብረማርቆስ፣ሰቆጣና በሌሎች በርካታ የክልል ከተሞች የራያና ወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄ ምላሽ እንዲያገኝ እንዲሁም ጣና ሐይቅና ላሊበላ ውቅርአብያተ ክርስቲያን የተደቀነባቸውን አደጋ መግስት አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጥ የሚጠይቅ ነው፡፡በተለይም ሰሞኑን የራያና አላማጣ ነዋሪዎች አደባባይ በመውጣት የፌዴራል መንግስት ለጥያቄቸው ምላሽ እንዲሰጥ በጠየቁበት ወቅት የትግራይ ልዩ ሀይል ፖሊስ ከ10 በላይ ሰዎችን መግደሉ በአካባቢው ከፍተኛ ቁጣ ቀስቅሷል፡፡ የራያ የማንነት ጥያቄን በተመለከት መጀመሪያ ጥያቄው ለትግራይ ክልል ቀርቦ ምላሽ የማያገኝ ከሆነ በፌደሬሽን ምክር ቤት እንደሚታይ የፌደሬሽኑ አፈ ጉባዔ ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም አስታውቀዋል። የራያ የማንነት ጥያቄ የተመለከተ እስካሁን ለፌደሬሽን ምክር ቤት ጥያቄ አለመድረሱን አስታውሰው ማህበረሰቡ ህገመንግስቱን ተከትሎ ጥያቄውን በደረጃ ካቀረበ ምላሽ የማያገኝበት ምንም ምክንያት የለም ብለዋል።በሌላ በኩል ትናንት በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ የክልሉን መንግስት በመቃወም አደባባይ በወጡ ነዋሪዎች ላይ የክልሉ ልዩ ሀይል በወሰደው እርምጃ ቢያንስ አምስት ሰዎች ላይ ከባድ ጉዳት መድረሱን ከስፍራው ያገኘነው መረጃ ጠቁሟል፡፡

Categories: ዜና

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s