ፖለቲካ

በወንዶች ጥረት ብቻ የተገነባ አገርም ሆነ ቤተሰብ የለም!!ሴቶች የቤተስብም የሃገርም ምሶሶ ናቸው!!

ኢትዮጵያ አራተኛዋን ፕሬዘደንት መረጠች!!የኢትዮጵያ የመጀመሪያዋ ሴት ፕሬዝዳንት ክብርት አምባሳደር ሳህለወርቅ ዘውዴ ሆነዋል!!
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያለ ድምፅ ተዓቅቦ በሙሉ ድምፅ ሥልጣኑን አፅድቆላቸዋል፡፡በበአለ ሲመታቸውም ላይ ከተናገሩት የሳበኝን እንዲህ ያሉት ነው የጀመርነው የለውጥ ጉዞው ውስብስብ እና በርካታ ፈተናዎች ያሉበት እንደሚሆን ይጠበቃል። እንዚህን ፈተናዎች አንዱ ሲገነባ አንዱ በማፍረስ ሳይሆን አንዱ በሰላማዊ መንገድ ሌላው በትጥቅ ትግል ሳይሆን መንግስትም ሆነ ተፎካካሪ ፓርቲዎች የጋራ ቤት እንደሚገነባ ቤተሰብ እርስ በእርስ በመደማመጥ በመፈቃቀር እና በመተሳሰብ የሚለያዪንን ጉዳዮች በማስፋት ወደ ጠብ አጫሪነት ከመሄድ ይልቅ አንድነታችችንን በሚያጠናክሩ ጉዳዮች ላይ በማተኮር መሻገር ይጠብቅብናል።ስር የሰደደውን ጥላቻ መናናቅ እና አልፎ አልፎ የሚታየውን ጠብ አጫሪነት በኢትዮጵያዊ ጨዋነት በዳበረ የቤተ እምነቶች ጥበብ እና የሽምግልና ስርዓት ከወዲሁ በመገታት ለራሳችንም ሆነ ለትውልድ የምታኮራ አገር መፍጠር ይኖርብናል።ታላቅ አገር የመገንባት ህልማችንን እውን ለማድረግ ከሰላም ውጪ ምንም አቋራጭም ሆነ አማራጭ የለንም።ሰለዚህ ሁላችንም ሰላማችንን አጥበቀን እንድንጠብቅ ከሁሉ በላይ ሰላም ሲታወክ በምትሰቃየዋ የእናት ስም አጥብቄ እጠይቃችኋለሁ፣
ሰላም ከራሳችን ጋር
ሰላም በቤተሰብ
ከጎረቤቶቻችን ጋር
ሰላም በመንደራችን
ሰላም በወረዳዎች መካከል
ሰላም በክልሎች መካከል
ሰላም ከጎረቤት አገሮች ጋር
ሰላም ከዳያስቦራዎች ጋር
ሰላም ሰላም ሰላም እላለሁ እጅግ ከጠበቀ አደራ ጋር!!!!!!!
በሰላም እጦት ሴቶች ዋነኛ ተጠቂዎች በመሆናችን በዚህ በሃላፊነት ቆይታዪ የኢትዮጵያን ሴቶች እና ሰላም ወዳድ ወንዶችን እንዲሁም በመላው አለም የሚገኙ ሰላም ወዳድ የሆኑትን ሁሉ ከጎናችን በማሰለፍ አብረን እንደምንሰራ እተማመናለሁ!! ለጥቁር ህዝቦች የነጸነት ምሳሌ እና የኩራት ምንጭ የጥንታዊ ስልጣኔ መነሻ እና የአፍሪካውያን መሰባሰብያ መዲና ሆና የቆየችው ሃገራችን ኢትዮጵያ የድህነት ምሳሌ ሆና ለዘመናት የመቆየትዋ ምስጢር በዋነኛነት የሰላም ዕጦት ነው!! ስለሆነም የሰላማችን ጠንቅ የሆኑትን ሁሉ በማስወገድ ሴቶችን እና ወጣቶችን እኩል ተሳታፊ በማድረግ መላው የሃገራችን ሴቶች እና ወጣቶች በርትታችሁ የልማቱ ተሳታፌ በመሆን ድህነትን በጋራ እንድናስወግድ አደራ እላለሁ!!!
ሌላው ከተናገሩት ሴቶችን ያጎሉበት መስመር ነው እናንት ሴት ልጆቻችሁን ከወንዶች ባላነሰ ሁኔታ ትልቅ ደረጃ እንደሚደርሱ ለራሳቸው፣ ለቤተሰቦቻቸው እና ለወገኖቻቸው የተስፋ ምልክት እንደሚሆኑ ሳትታክቱ የመከራችሁ በሞራል፣ በጸሎት እንዲሁም አቅማችሁ በፈቀደው ሁሉ ፍቅር እየሰጣችሁ የደገፋችሁ ወላጆች እኔ የዚህ ድጋፍ ውጤት ስለሆንኩ እንኳን ደስ ያላችሁ!!ሴቶች ከወንዶች እንደማያንሱ በየተሰለፋችሁበት መስክ በተለይ በቤት ውስጥ ለጆቻችሁን በትጋት የምታሳድጉ በገጠርም ሆነ በከተማ በእርሻ ስራ፣ወይም በንግድ። በህክምና ፣ በመምህርነት ወዘተ ኑሮዋችሁን ለማሸነፍ ሌት ተቀን የምትለፉ የምተተጉ በቂ እንቅልፍ ሳታገኙ ፣በቂ ምግብ ሳትመገቡ፣ በቂ እርፍት ሳይኖራችሁ ፣ በቂ ገቢ ሳይኖራችሁ አንድ ቀን ያልፍልኛል፣ለኔ ባያልፍልኝ ለልጆቼ ያልፍላቸዋል ለሃገሬ ያልፍላታል በሚል ጉልበታችሁን ጊዜያችሁን ገንዘባችሁን ሳትሰስቱ ትግል የምታደርጉ ሁሉ ልፋታችሁ ከንቱ ሆኖ ስለማይቀር ከጥረታችሁ ወደኋላ እንዳትሉ አደራ ልላችሁ እፈልጋለሁ!! እኔም የዚ ጥረት ውጤት እንደሆንኩ ጠንቅቄ አውቀዋለሁ በወንዶች ጥረት ብቻ የተገነባ አገርም ሆነ ቤተሰብ የለም!!ሴቶች የቤተስብም የሃገርም ምሶሶ ናቸው!! ሴቶች ሲጎዱ ቤተሰብ ይጎዳል ከሁሉ በላይ አገር ትጎዳለች! ሰለዚህ ሴት ቤተሰብ ነች ቤተስብ ደግሞ የአገር ትንሹ ምሳሌ ነው።ሰለዚህ ሴት አገር ነች አገርን ደግሞ ወንዱም ሴቱም ሊንከባከበው ይገባል።ወንድም ሆነ ሴት ለራሱ ሲል ሃገሩን ለራሱ ሲል እናቱን፣እህቱን፣ ሚስቱ የሆነችውን ሴት ሊንከባከብ ይገባል።የሴቶችን ማንኛውም አይነት ጥቃት የማይቀበል ትውልድ ልንገነባ ይገባናል።ሰለሴት አብዝቼ የተናገርኩ የመሰላችሁ ገና ምኑ ተነካና በማለት ከሴቶች ጋር አብረው ለመስራት ሴቶችን ወደፊት ለማምጣት እና የሴቶችን ተሳትፎ ከፍ ለማድረግ ማቀዳቸውን በንግግራቸው አንሰተዋል እኛ ከዘመራ የራዲዮ ዝግጅት ክፍል ለፕሬዘዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ መልካም የስራ ዘመን ተመኝተናል።

Categories: ፖለቲካ

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s