ማህበራዊ

ታላቅ ሀገራዊ ጥሪ !

➨ ለኢትዮጵያዊያን መሀንዲሶች ፣ ለአርክቴክቶች ፣ ለስራተቋራጮች (ኮንትራክተሮች )፣ ለአማካሪ መሀንዲሶች ፣ ለቅርስና አርኪኦሎጂ ተመራማሪዎች ና ለዩኒቨርሲቲ ምሁራኖች በሀገራችን የህንፃ ጥበብና አሰራርን ከላይ ወደታች በመስራት ከአንድ ወጥ ድንጋይ የተሰራው ላሊበላ ከ900 አመት በላይ አገልግሎት የሰጠ ፣ ከሀገራችን አልፎ በአለም ቅርስነት የተመዘገበው የላሊበላ ውቅር አቢያተ ክርስቲያን እኛ ኢትዮጵያዊያን መሀንዲሶች በህይወት እያለን ላሊበላ ከህንፃነት ወደ ፍርስራሽ አፈርነት ፣ ከመለወጡ በፊት ከአማራ ክልል ባህልና ቱርዚም ጋር በመተባበር ከተለያዬ የምህንድስና ጥበብ ባሌቤት ጋር በመሆን ” የመሀንዲሶች ቡድን ” አቋቁመን የላሊበላን ውቅር አቢያተ ክርስቲያንን በጋራ እንታደገው።

የበጎ ፈቃደኛ ቡድን

1) የሲቪል ምህንድስና (material engineer ) ቡድን
2) የአርክቴክቶችና የስትራክቸር መሀንዲሶች ቡድን
3)የሀይድሮሊክስና የሀይድሮሎጂ የመሀንዲሶች ቡድን
4) የመካኒካልና የእሌትሪካል የመሀንዲሶች ቡድን
5)የ Geotheck ከመሬት በታች ያለን ስትራክቸርና የአፈሩን የድንጋዩን ባህሪ የሚያጠና የጂኦሎጂስት ቡድን
6) የቅርስና የአከባቢ ጥናት ቡድን
7) የአከባቢው ነዋሪዎች የኪነህንፃ ጥበብና እውቀት ያላቸው አባቶች ቡድንና ተመራማሪ ተማሪዎችን ያቀፈ ቡድን

እነዚህንና የመሳሰሉትን የሙያው ባለቤት የሆኑ የምህንድስና ቡድን አቋቁመን በአጭር ጊዜ ውስጥ ሁሉም በሚመደብበት ዘርፍ ጥናት አድርጎና አዳዲስ አሰራሮችን በመፍጠር ፣ የሚመለከተውን አካል አስተባብረን የላሊበላን ህንፃ ከእኛ ኢትዮጵያዊያን ውጭ ማንም ስለማይጠግንና መንግስትም በቂ በጀት ስሌለው በፍላጎት ላይ የተመሠረተ የነፃ በጎ ፈቃደኛ በመሆን ሙያዊ ግዴታችንን እንወጣ !!!

አጠቃላይ ሁኔታውን ከቅዳሜ 03/02/2011 ከቀኑ 7.45 ጀምሮ በአማራ ቲቪ በኤቫሾው እንገልፃለን !! አሁኑኑ በጎ ፈቃየኞች በውስጥ መስመር መመዝገብ ትችላላችሁ ! እውቀት ያለው በእውቀቱ ፣ ማሽን ያለው በማሽኑ ፣ የሚያስፈልገውን ጥሬ እቃ አቅርቦትን በተመለከተ በአቅርቦት በሚቻለው ነገር ሁሉ አግዙን !!!

የስራተቋራጮችና አማካሪዎች የመንግስት ተቋማት አስፈላጊውን ትብብር እንድታደርጉልንና ለበጎ ፈቃደኛ ሰራተኞች ፍቃድ እንድትሠጡአቸው በእግዚአብሔር ስም ትለምናላችሁ!!!
ላሊበላን ወደ ፍርስራሽነት ሳይለወጥ እናድነው !!! እንደ ሀኪም ወንድሞቻችን ሙያዊ ግዴታችንን ለሀገር እንወጣ!!!

ላልደረሠ በማድረስ ተባበሩን !

” Eva Show on ATV ” ላይክ ብላችሁ መልክት አስቀምጡ

እግዚአብሔርአብሔር ኢትዮጵያንና ልጆቿን አብዝቶ ይባርክ!!!

Categories: ማህበራዊ

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s