ማህበራዊ

ይድረስ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ሁሉ የእናትነት ምርቃትና በረከት ባላችሁበት ይድረሳችሁ!

በዚህች እኩለ ሌሊት! ወትሮም እንደማደርገው! በሠላም ያዋለኝን አምላክ አመስግኜ: ለሌሊቱ ደግሞ በሠላም እንዲያሳድረኝ የዘወትር ፀሎቴን አድርሼ ጋደም ስል!

እንደተለመደው በሐሳብ ወደ ሕዝቤ የሰሞኑ ከረሜታ አሰብኩና: ተፈፀሙ ከሚባሉት ክፋትና አስቸጋሪ ሁኔታዎች ይልቅ:
እስከዛሬ በዚህ ሁሉ መሐል ደግሞ የታዩ የሕዝቤን ታጋሽነት እያሰብኩ:
ለኢትዮጵያ ሕዝብ ያለኝ አድናቆት በድንገት እጅግ ገዘፈብኝና:ልቤ በደስታ እና በማድነቅ ተሞላ::

አምላኬን በፀሎት አመሰገኜ ሳበቃ:
ሕዝቤንስ እንደው የት አግቼው ላመስግነው? እያልኩ ሳሰላስል ቆይቼ:

ለነገ ጠዋት እንዲያነቃኝ የማንቂያ ደውሉን ምልክት ላደርግ እጆቼን ወ ወደ ስልኬ ላይ ጣል ሳደርግ:

መቼም አይኔ አላስችል አለኝና የፌስቡክ ገፄን በቆረጣ ስመለከት:
What’s on Your mind ?
ምን እያሰብሽ ነው?
ብሎ ሲጠይቀኝ:
ሐሳቤን በነፃነት የማጋራበትን ፌስቡክን የፈጠረውን አዕምሮ እያመሰገንኩ!

ሐሣቤማ አልኩና ! እንደው የኢትዮጵያን ሕዝብ ባለበት ሁሉ መባረክና መመረቅ አሰኘኝ አልኩት ለፌስ ቡኩ!

እንቅልፉም መኝታው ቀረና ጣቶቼ የፌስቡኩ ፊደል መተየቢያው ላይ አረፉና መጫጫር ጀመሩ:

“ የቀደመው ሥርዓት የፈረሰ ሰሞን: “ወግ ያለው መንግሥት“ በምድሪቱዋ ሳይኖር:
የኢትዮጵያ ሕዝብ ለወራትት ያህል ከመንደሩ ከቀየው ከወረዳና አውራጃው ሕዝብና ጎረቤት ጋር: በፍቅርና በመከባበር የቆየበትን ያንን ጨዋ ዘመኑን እያሰብኩ!
ያችን ዘመን በጨረፍታ ጥቂት አይቼያት ስለነበር:

ትውልድ ምድሬን ለቅቄ : በምፃተኝነት ያለፉትን ሀያ ስድስት ዓመት የተለየሁዋትን ምድሬን እንደገና በምናቤ በእኩለ ሌሊት የጎበኘሁዋት!

ይባስ ብሎ ከሁሉ የበለጠ የደነቀኝ ደግሞ: “መንግሥት ተብዬው“ በሥልጣን ላይ በነበረበት ዓመታት ሁሉ ደግሞ:
አገሪቱዋንና ሕዝቡዋን: አንቀፅና አዋጅ አውጥቶ: እስከመገነጣጠል ድረስ የሚፈቅድ መንገድን ልቅ ቢያደርግለትም:

እንኩዋን ሊገነጣጠል ቀርቶ: “አንፈልጋችሁም“ ብሎ ጥሎ የሄደና የተገነጠለውን ወገኑን ሕዝብ እንኩዋን ሳይቀር: በናፍቆትና በስስት እንደገና ሲገናኝ:

በደልን ሳይቆጥር: በፍቅርና በእምባ የሚያስተናግድ ሕዝብ: ምንኛ የተባረከ ነው ብዬ እጅግ አደነቅሁት!

የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ እጅግ ታላቅ ክብርና ምስጋና ይገባሀል!

ትውልድን ከአርባ ዓመታት በላይ ገብረህ: ዛሬም ከበቀል ይልቅ ለፍቅርና ለይቅርታ የተዘጋጀ ልብ ስላለህ: ትልቅ ክብር ይገባሀል!

ይህን ልዩ ቅንነትና ርሕራሔ: ቸርነትና በጎነትን ያጎናፀፈህ እግዚአብሔር ስሙ ይባረክ!

አደራ ከምስጋናው ጋር ደግሞ የማሳስብህ!

“ በእግራቸው እንዳይረግጡት ተመልሰውም እንዳይነክሱአችሁ: የተቀደሰውን ለውሾች አትስጡ: እንቁዎቻችሁንም በእሪያዎች ፊት አትጣሉ “ እንደተባለው በማቴዎስ 7:6 ላይ
አደራ አደራ አደራ!

ይህን ደግነት: ቸርነት ርሕራሔና እንግዳ ተቀባይነት እንቁህን: ሊያስጥሉህና
በሐይማኖት በቁዋንቁዋና በሚጠፋ ዘር: ሰበብ አድርገው ሊያናክሱህ ወጥመድ ከዘረጉልህ የክፉ ስራ መጠቀሚያ ውሾች ተጠበቅ!
እንቁህንም አጥብቀህ ያዝ!

ልዑል እግዚአብሔርም: ማንኛውንም የምድሪቱን ሕዝብ ሁሉ ይባርክ!
ደመናም ባናይ : ንፋስም ባይኖር!
የእግዚአብሔር የምህረትና የፍቅር ዝናብ ምድሪቱዋን ያረስርስ!

ትላንትን የሚያስረሳ: የነገን ብሩህ ተስፋ የሚያስናፍቅ ጉልበት: ለሕዝባችን ሁሉ: ከፀባዖት ይለቀቅ!

ልቡ ያዘነውንና ልቡ የተሰበረበትን! የሚጠግን: የሚፈውስና የሚክስ ታላቅ ዘመን ከፊታችን ይሁን!

ትውልድ ከእንግዲህ ከምድሪቱዋ አይጨንግፍ!
የደስታና የዜማ ግዜ ለምድራችንና ለሕዝባችን ይፍጠን!

ትውልድን ባማጠ ማሕፀኔ ላይ እጆቼን ጭኜ! እንደ እናት ሕዝቤን ባረክሁ🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏መረቅሁዋችሁም!

ቅዱሥ የእግዚአብሔር መንፈስ!
በዚች ውድቅት ሌሊት: በሩቅ ምድር ሆኜ ስለ አገሬ በምሰማው ክፉ ነገር: ከማዘንና ከመጨነቅ ይልቅ:

እኔን በደስታና በሠላም ሞልተህ! እንደ እናት ትውልዱን እንድባርክ መንፈሴን ስላነቃቃህ አመሰግንሀለሁ!

የምድርም የሠማይንም በረከት: በሕዝቤና በትውልድ ምድሬ ኢትዮጵያ ላይ: እንደገና ስለምታፈልቅ አመሰግንሀለሁ!

በሠማያት የምትኖር አባታችን ሆይ!አንተ ራስህ ለሕዝባችን ካለህ ፍቅርና ርሕራሔ የተነሳ : ቃሌንም ስለምታፀናው አመሰግንሐለሁ!

በጌታችና በመድሐኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አሜን ይሁንልን!

የትውልድ እናት ሰዋስው
ከሰሜን ዋልታ ኖርዌይ
በመንፈቀ ሌሊት ተጣፈ

Categories: ማህበራዊ

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s