ፖለቲካ

ሃገርንም ያጠፋል!!

ሃይማኖታዊ ትውፊታችን፣ ባህላችንና ታሪካችን የኢትዮጵያውያን እሴቶቻችን ወዴት ሄዱ?? ኢትዮጵያ ውስጥ እምነት የሌለው ሰው እንደሌላው አገር በምንም የማያምን ፓጋን አለ በዪ አላምንም የሁሉም ሃይማኖት የሚያስተምረው ፍቅርን ትህትናን፣ደግነትን ፣ የዋህነትን እርህራሄን ነው። ታድያ እንደዚህ አይነት ትውልድ የተፈጠረው ይህ ጭካኔ እና ክፋት የተቀዳበት ምንጩ የት ነው? በገዳ ሰርዓት ፣ በአውጫጭኝ እና በሌሎችም ስርዓቶች እየተዳኘ ያደገው ህዝብ አኩሪ እሴቱን የት ጥሎት ነው በቤንዚን አቃጣይ ክቡር ይሆነውን ሰው ዘቅዝቆ ሰቃይ የሆነው? ያ የከበረው የዳኝነት እና የፍትህ ሥርዓት እሴታችን የት ገባ በኢትዮጵያ ረዥም ዘመን ታሪካችን የዳኝነት ሥርዓት የተከበረ ነው፡፡ ለሚፈሰው የህዝቡ ደም ለሚቃጠሉ ቤተ እምነታት ተቆርቋሪ መንግስት ባይኖር ያሳደገው “የሕግ አምላክ”እያለ የሚያከብረው ህግ የት ሄዶ ነው ህግ ባለበት አገር ያጠፋን ሰው ልህግ ማቅረብ ሲቻል እራሳቸው መርማሪ፡ እራሳቸው ፈራጅ፡ እራሳቸው ቀጪ እራሳቸው ባልተጣራ መረጃ የሚፈርዱ፣ እራሳቸው በግብታዊነት የሰውን ህይወት የሚቀጥፉ፣እራሳቸው ንብረት በእሳት የሚያወድሙ ሆነው ይህን አሰቃቂ ድርጊት የፈጠሙት?? በዛሬው ቀን እጅግ አሰቃቂ ለማየት የሚያም ተግባር ተፈጽሟል። በምንም ሚዛን ላይ ቢቀመጥ አሳማኝ እርምጃ አይደለም።ኢትይጵያዊ እንደዚህ ያድርግ እንደዚህ በወገኑ ላይ ይጨክን ይሄ የስርዓት አልበኝነት መገለጫ እንጂ ሌላ ስም የለውም። ማቃጠል መግደል እና መስቀል ኋላ ቀርነት ነው!!!
ኢትዮጵያውያን “በፍርድ ከሄደችው በቅሎዬ፤ ያለ ፍርድ የሄዳችው ጭብጦዬ ታሳዝነኛለች” የሚል ጽኑ የፍትሕ ጥማት የነበራቸው ናቸው።የቀደሙት በስልጣኔ በጣም ይበልጡናል እኛ ግን ብዙ ይቀረናል!! የአንድ ሥልጡን ማኅበረሰብ አንዱ መገለጫው ይህን ከመሰለ ባሕላዊ እሴቱ ጋር አለመጋጨቱ እና አለመቃረኑ ነው፡፡ የአሁኑ ጊዜ እየታየ ያለው ነገር ግን መጋጨት ብቻ ሳይሆን ማፈራረስ ነው።
ዛሬ ጊዜና ጊዜ ቦታ በሰጡን ኃላፊነት ላይ ያለን ሁሉ “የሰው እንባ እሳት ነው ያቃጥላል ካላልን የዘራነውን እንክርዳድ ወደ ስንዴ ካልቀየርን አንድ ቀን ይሄ መነዳት እና የሰውን ደም ማፍሰስ ለኛ እንደሚሆን አንዳንዘነጋ!! ይልቁኑስ በዚ ላይ ልትሰሩበት ይገባል!! መጀመርያ የናዳችሁትን እሴቶቻችንን ቦታው መልሱልን በኔ አምላክ ሳይሆን በህግ አምላክ የሚል ትውልድ ፍጠሩ ፍርያችሁን እያያችሁት ነውና!! ከራሳችን የእምነትና የእሴት ስሌት በተቃራኒ ስለቆምን በእውነት አልሰለጠንም፡፡እግዚአብሔር በግፍ የሚፈሰውን የእያንዳንዱን ሰው ደም ከእጃችሁ ይፈልጋል እግዚአብሄር የፈጠረው ፍጥረት ሁሉ የተቆጠረ ነው ግፍና በደል ይበቃችኋል!! የፈጠራችሁን እንኳን ባታምኑ ሕሊና፣ ታሪክና ሕዝብ አለ ብላችሁ እመኑ፡፡ ይህ ትውልድ የባሕላችንን እሴቶች በልቡናው ጽላት ቀርጾ በእነርሱ መመራት ካልቻለ፡፡ ፍትሕ ትጨነግፋለች፡፡ እውነት ከምድሩ ትጠፋለች፡፡ ፍቅር ጓዟን ጠቅልላ ትበናለች፡፡ ክህደት ታብባለች፡፡ ማስመሰል ትነግሳለች፡፡ ውሸት ትወፍራለች፡፡ ሥልጣኔ እና የምንለፋለት ዲሞክራሲ ዲሞክራሲ ቅዥት ትሆናለች፡፡ከምንም በላይ ሀገርንም ያጠፋል። በዛሬው እለት በጨካኞች የተፈረደባትን ነፍስ ጌታ ይቀበላት

Categories: ፖለቲካ

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s