ፖለቲካ

ከኢትዮጵያ ሰማይ ስር ሰንደቅ ዓላማችንን ለዘመናት ከታሰረችበት እናስፈታት።

ከኢትዮጵያ ሰማይ ስር 3
ውድ ኢትዮጵያዊያን ይህን ፅሁፍ ሼር በማድረግ ለጀመርኩት አላማ መሳካት ከጎኔ እንድትቆሙ በታላቅ ትህትና ጥሪዬን አቀርባለሁ።
ከኢትዮጵያ ሰማይ ስር ሰንደቅ ዓላማችንን ለዘመናት ከታሰረችበት እናስፈታት።
ስለዚህ ጉዳይ የምጮኸው ዝም በዬ በስሜት አይደለም። የማውቀው ታሪክ ስላለ ነው።
ሜጋ አምፊ ቴአትር የህፃናት ቴአትር በምሰራበት ወቅት አንድ ምርጥና ትሁት ሰዓሊ አውቅ ነበር። መስፍን የሚባል።
በወቅቱ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ የሆነችው ንፁህ ባንዲራችን ላይ ገዢዎቻችን የሆነ ነገር ማስቀመጥ ፈልገው ነበር። ባንዲራችንን እጅግ ከመጥላታቸው የተነሣ ጨው መጠቅለያ አድርገዋት እንደነበር አንረሣውም።
ያኔ የጠ/ ሚ የቅርብ አማካሪ የሆኑት የአህያ አፍቃሪ መክረዋቸው እንደሆን ባላውቅም ባንዲራው ላይ ምን ዓይነት ምስል ይቀመጥ በሚለው ክርክራቸው የአህያ ምስል ይቀመጥበት ተባብለው እንደነበር በጆሮዬ ሰምቻለሁ።
በመጨረሻ ጠ/ሚው መስፍኔን በማስጠራት አሁን ያለውን የኮከብ ምስል እንዲስል ያዙታል። ክፍያውም 5000(5ሺ) ብር ነበር፡፡ የተወሰነውን ክፍያ ከፍለውት ቀሪውን ሳይከፍሉት እንዳመላለሱት መስፍኔ በድንገት ከዚህ አለም በሞት ተሸኘ። እጅግ በጣም ትሁትና ብቃት ያለው የጥበብ ሰው ነበር።
ይህ የኮከብ አርማ
ለምስኪኑ ህዝብ የብሄረሰቦችን እኩልነት ማረጋገጫ ነው የሚል ተረት ተፈጥሮ ተነገረው፡፡
ይህ ባንዲራ ከሃገሬ ሰማይ ስር መውለብለብ ከጀመረ ጀምሮ ግን አንኳን የብሔረሰቦች ነፃነት ሊረጋገጥ ይቅርና አንድነታችን መላላት፤ በዘር ተከፋፍሎ እርስ በርስ በጥርጣሬ መተያየትና መጨራረስ ነው የተረፈን፡፡
ኮከቡ በመጀመሪያ የተቀመጠው ቢጫው ላይ ብቻ ነበር። ተኝተን ስንነሳ ግን እነደ ህፃን ልጅ እድግ እያለ ሙሉ ባንዲራዋን ሊውጣት ትንሽ ነው የቀረው።
.
አሁን አዲስ ለውጥ በማየታችን ተስፋችን አንሰራርቷል፡፡
ብዙ አስረኞች ተፈተው ደስ ብሎናል ሰንደቃችን ግን እንዳትውለበለብ በህግ ታስራለች።
ሀገር ካልተፈታች እስረኞች ቢፈቱ ከትንሽ እስር ቤት ወደ ትልቅ እስር ቤት አንደተዘዋወሩ ነው የሚቆጠረው፡፡
የአፍሪካ ህዝብ የነፃነት አርማ፤ አንድ የነበረችው የታላቋ ኢትዮጵያ የአንድነት አርማ፤
የሀገር ወዳድ ዜጎች መኩሪያ ንፁኃ ባንዲራችንን ከታሰረችበት እናስፈታት፡፡
ደስታችን መሉ ይሁን፡፡

ፍትህ ለአረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሰንደቅ አላማችን፡፡
ከያኒት አስቴር በዳኔ

Categories: ፖለቲካ

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s