ፖለቲካ

የማንቂያ ደወል የተኩስ አቁም ስምምነት ጥሪ!

አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶክተር አብይ አህመድ : እስካሁን ያላቸውን አካሄድ ከሚያደንቁላቸው ሰዎች መሐል አንዱዋ ነኝ::
እስከ ዛሬ ስጮህበት የነበረውን
“ፍትሐዊ እርቅና ብሔራዊ መግባባት“ አጀንዳም: ዛሬ ዛሬ ሁሉም ይህን ሐሳቤን ሸምቶት: እያስተጋባው እያለ በማየቴና እርሳቸውም ይህንኑ እያሉ ስለሆነ በጣም ተስማምቶኛል::

ነገር ግን በኢትዮጵያ ውስጥ
“ፍትሐዊ እርቅና መግባባት“ እንዲመጣ የእውነት ከተፈለገ!
በመንግሥትም ሆነ በተቃዋሚዎች መሐል: ቅድመ ሁኔታዎችን ማስቀመጥ ማቆም አለባቸው ባይ ነኝ: ምክንያቱም

1ኛ- መንግሥት ተብዬው “ሕገመንግሥቱን ካላከበራችሁ አልነጋገርም “ ካለ
ቀድሞውኑ ሲጀመርም የአብዛኛው ተቃዋሚዎች ቅሬታ የጀመረው : በሕገ መንግሥቱ ላይ ይመስለኛል::
ያም የኢትዮጵያን ሕዝብ ያላካተተ : ጥቂት የመጀመሪያዎቹ ፖለቲካ ድርጅቶች ብቻቸውን የወሰኑት: አገርን እስከ መገነጣጠል ድረስ የሚፈቅድ: የቀደመውን ብሔራዊ ባንዲራን ሽሮ: የራሱን ባንዲራ ያደረገ ወዘተ. ነው ብለው መሰለኝ ወደ ተቃውሞ የገቡት!

2ኛ- ሲቀጥልም ይህንኑ “ሕገ መንግሥት ተብዬውንም “ እንኩዋ ቢሆን እስከ ዛሬ ድረስ በአብዛኛው ያላከበረው: እራሱ መንግሥት ተብዬው ለመሆኑ እስከዛሬ በመንግሥት ተብዬዎቹ የተደረጉት ጭፍጨፋዎች: ዝርፊያዎች: ሕዝብ ማፈናቀሎች ስደቶች: እስራቶች: ወዘተ. ዎች በቂ ማስረጃዎች ናቸውና:

ራሱ ያላከበረውን ሕገመንግሥት ሌላውን አክብሩ ማለት አግባብ አይሆንም::

3ኛ- በተቃዋሚው በኩልም ደግሞ እንዲሁ:
“ይህን ይህን ካላደረግህልን? “ ከእናንተ ጋር አንደራደርም ማለት አግባብ አይሆንም:
ባይሆን በተለይ በውጭ ያሉ ፖለቲከኛ ድርጅቶች ወደ አገር ቤት መግባት ካለባቸው: እንደማይታሰሩ ዋስትና ቢጠይቁና በዛ ዋስትና መሠረት ቢገቡ: አለያም በውጭ በመንግሥት ተወካዮችና በተቃዋሚ ተብዬዎች መሐል: በድብቅ ሳይሆን በግልጥ : በገለልተኛ አገርኛ ልጆች በኩል አንዲነጋግሩ ቢያመቻቹ?

4ኛ. ምንም እንኩዋን በየትኛውም ወገን የሚደረግ ጦርነትናየትጥቅ ትግልን ባልስማማበትም:
በመንግሥት በኩል
“ በሠላማዊ ትግል እንጂ በሁለገብ ትግል የሚታገሉትን አልቀበልም “ ካለ:

ሲጀመርም ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር የትጥቅ ትግል በማድረግ: እስከዛሬ ድረስ የኢትዮጵያን ሕዝብ የጨፈጨፈውና የትጥቅ ትግሉን በሕዝቡ ላይ የጀመረውም “ መንግሥት ተብዬው እንጂ ተቃዋሚዎች ስላልነበሩ: ሕዝቡንም ሲገድል የነበረው በትጥቅ እንጂ በልምጭ ስላይደለ:

ተቃዋሚ ተብዬዎቹም በተለይም የትጥቅትግልን የጀመሩት የሚሰጡት ምክንያት “ በሕዝባችን ላይ እየተደረገ ያለውን ይህን ጭፍጨፋ ለመከላከል የተጀመረ ትግል ነው “ ስለሚሉ

5ኛ. የትጥቅ ትግል ወይም የተኩስ ማቆም ስምምነት መደረግም ያለበት በሁለቱም ማለትም በመንግሥት ተብዬውም: በተቃዋሚ ተብዬዎችም መሐል መሆን ስላለበት:

6ኛ- ይህንንም ማድረግ ያለባቸው ከሁለቱም ወገን “ አሸናፊ ለመሆንና አንደኛውከሌላው የበለጠ ጎልቶ ለመታየት ሳይፈልጉ “ የትዕቢት ካባቸውን“ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ጠቅላላ ደህንነት ሲሉ ራሳ ቸውን አዋርደው : ለጠረጴዛ ውይይት ራሳቸውን እንዲያዘጋጁ?

7ኛ- እሰከዛሬ ትውልድን በተነጠቁ ቤተሰቦች ስምና: ሁለቱ ዝሆኖች ቢጣሉ የሚጎዳው መላው የአገሪቱ ሕዝብና ጠቅላላ አካባቢ ቀጠናው ስለሆነ: ስለዚህ ምስኪን ሕዝብ ስትሉ: የውጭ ሐያላን መንግሥታት እያስገደዱአችሁ: ለእነርሱ ከምታጎበድዱ:

“የአገሩን ሠርዶ: በአገሩ በሬ“ እንደሚባል: ከዚህችው የተቀደሰች ምድር የወጣን እናቶችና አባቶች: አዛውንቶችና ሽማግሌዎች የምንለምናችሁን ተማፀኑን?
ይህንን ስል ነገር ሁሉ አበቃ ለማለት ሳይሆን: “ምን ይደረግ?“ ብለው መክረው ለሕዝብ በማቅረብ “አዎንታን“ እንዲጠይቁ ነው::

ይህን መልዕክት በዶክተር አብይ በኩል ለሚመራው መንግሥትም: ሆነ ለተቃዋሚ ተብዬዎች ሁሉ አደራ አደራ አዳርሱልኝ?

የትውልድ እናት ሰዋስው
ከሰሜን ዋልታ ኖርዌይ

Categories: ፖለቲካ

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s