ፖለቲካ

ባለካርዶቹና ካድሬዎቹ!!!

ሀገራችን ኢትዮጵያ ከ 27 ዓመት የግፍ ፣ የስቃይ የግድያ እና የአፈና አመታት ጉዞ ግድያውም አፈናወም እየተባባሰ ስርዓቱ ክፉኛ እየተንገዳገደ የሚይዘውንና የሚጨብጠውን በማጣት የፍርሃት እርምጃውን እንደብቸኛ መፍትሄና አማራጭ ተያይዞታል

ለኦሮሚያ አብዮት ምስጋና ይድረሰውና ሃገራችን ከመበታተን ህዝቦቹዋም በይበልጥ የተሳሰሩበት የህልውና ገመድ በይበልጥ እንዲጠናከር አዲሱ ትውልድ በደሙ አስደናቂና ታላቅ ታሪክ ለቀጣዩና አሁን ላለው ትውልድ አስመዘገቦአል

ህወአት ላለፉት 27 ዓመታት በአደራዳሪዎች ድጋፍ ባጋጣሚ በወቅቱ የታጠቀ ወይም የተደራጀ አሽናፊ ወይም አቻ ሀይል ባለመኖሩ ባጋኘው አጋጣሚ እና በአሜሪካኖች ተጽእኖ ኢትዮጵያን የሚያክል ታላቅ ሰፊ መሬትና በተፈጥሮ ሀብት የበለጸገች ፣ ወራሪዎችን በመቅጣት አኲሪ ታሪክ ያለው ህዝብና ጥንታዊ ገናና ታሪክ ያላት ሃገር ተረከበ

በነዚህ 27 ዓመታትም ህዝቦቹዋን በመግደል ፣ በማሰር ፣በማሰቃየት ፣ በማፈን ፣ በማፈናቀል ፣በማሰደድ ፣ የሀገሪቱን ሀብት ወታደራዊ የበላይነትን በማሰፈን በቢሊዮን የሚቆጠር ሀብትና ንብረት አካብተዋል አሽሽተዋል

ከዛም ባሻገር የትግራይን ህዝብ ያለፍላጎቱ ከተቀረው የኢትዮጵያ ህዝብ ለመገንጠል ባለፉት 27 ዓመታት ካርታ ሰርተው ሌሊት ተቀን ያላአንዳች ተቀናቃኝ ዘና ብለው እየዘረፉና እየሰሩ በፍጹም በማይታሰብ መልኩ እነሱ እንደሚሉት ብሶት የወለደው አብዮት እንደደራሽ ጎርፍ አሁን ይከሰታል ብለው ባልጠበቁበት ሰአት ከተፍ ብሎ ይንጣቸው ፣ ያሰጨንቃቸው ከጀመረ ሁለት ዓመታት እያለፉ ይብሱንም በፍርሀት የሚወስዱት እርምጃ እየባሰ በአሁኑ ሰዓት ለሃገራችንና ለህዝባችን ታላቅ የፈተና ወቅት ላይ እንገኛለን

ጥንቱንም በግድያ ፣ በአፈና በጠመንጃ ሀይል በጉልበት ለመግዛት ስልጣን ከህዝብ የነጠቀን መንግስት በምርጫም ሆነ በሰላማዊ መንገድ መልካም አሰተዳደር ያሰፍናል ተብሎ ባይጠበቅም እስካሁን የተደከመበት በሺዎች የሞቱበት ፣ በመቶ ሺዎች የታሰሩበት ፣ በመቶ ሺዎች የተሰደዱበት እና ሌሎች መስዋዕትነት የከፈሉበት ለገዢው ለህወአት ምንም ማለት ባለመሆናቸው ሳይወድ በገዱ ለህዝባችን ያስተማረውም መንግስት በጠመንጃ እንደሚመሰረት በጠመንጃ በስልጣን እንደሚቆይ በመጨረሻም በጠመንጃ እንደሚውገድ በመሆኑ ህዝባችን ለሰላማዊ ትግል ያለውን ጽናትና ቁርጠኝነት እራሱ መንግስት አፍርሶታል

በዚህም የተነሳ አዲሱ ትውልድ ስርዓቱ ራሱን እንዲያስተካከል መልካም አስተዳደር እንዲያሰፍን ካልቻለ ስልጣን ለህዝብ እንዲያሰረከብ ጊዜው በመድረሱ ለ 27 ዓመት ከህዝብ ጫንቃ አልወርድ ላለ ስርዓት ክፉኛ መንግዳገድና መቁሰል የግድ የሆነው ይህም ማለት ለውጥ በኢትዮጵያ አይቀሬ መሆኑን አሰጨብጧል

አሁን ወያኔ አዲስ ስልጣን ላይ ወደነበረው ሀይልና ስልጣን መመለስ እንደማይችል እሱም ህዝባችንም ጠንቅቆ ያውቀዋል ለስድስት ወር የሚያቆየው የአስቸኲይ ጊዜ እንደምንም አጭበርበሮ በአደባባይ ግፈኛ መንግስት መሆኑን ለዓለም አሳይቶ ለስድስት ወራት  ዜጎችን ለመግደል፣ ለማፈንና ከተቻለ አብዮቱን ለመቀልበስ አዲስ ካርድ ፍቆ ሞልቶ በግለሰብ እና በጅምላ  እየገደለ ፣እያፈነ እና እያሰረ ይገኛል

ባለስደሰት ወሩ ካርድ የሞሉት ህወአቶች እንዲሁም ገዳዮቹ አጋዚያውንና ተባባሪዎቻቸው ከሌሎች ክልል የተውጣጡ የመከላከያ ሰራዊት አባላት አሁን በያዙት ፈጣን ግድያ ብቻ በወለጋ በአምቦ ከ 15 በላይ በመግደል ብዙዎችን በማቁሰል ፣ በመደብደብ በሺዎች የሚቆጠሩ ወደ እሰር በማጋዝ ፣ በተለይም በሞያሌ ያለ አንዳች ሁኔታ ሰላማዊ ዜጎችን በጅምላ 13 ሰው በመግደል እና ክ25 በላይ ሰዎችን በተቀነባበረ ሆን በሎ በታቀደ ዘዴ በጥይት ከፈጁ በሁላ ኦነግ ሰርጎ ገብቶ በስህተት በደረሰ መረጃ መሰረት አንድ ሻለቃ ጦር ውስጥ የሚሰሩ አምስት አባላትን እና አዛዡን አስሬአለሁ በማለት ይቅርታ በማለት ፣ በማሾፍ በሞቱት ወገኖቻችን ደምና በታላቁ የኦሮሞ ህዝብ እንዱሁም በመላው ህዝባችን ንቀታቸውንና ስላቃቸውን በመንግስታቸው ሚዲያ ነግረውናል

በዚህ የግድያ እርምጃቸው እንደበቅሎዋ በገዛ እጃቸው ገመዳቸው እንዳጠረ ያላቸው የግድያ አገልግሎት ሂሳብ በፍጥነት እያለቀ መሆኑን አበክረን እንነግራቸዋለን ይህም ማለት እስከ ሰድስት ወር የማያቆያቸው መሆኑን ነው

ከኦሮሚያ ቄሮዎች እንደሰደድ እሳት የተቀጣጠለው አብዮት ከጥግ እስከ ጥግ ተዳርሶኧል ዛሬ ፋኖን ዘርማን አፍርቶኧል ደፋር በባዶ እጁ ሞትን የማይፈራ ትውልድ አፍርቶኧል ህወአትን በኢኮኖሚ አሽመድምዷዋል ፣ የአፈና መረቡን በጣጥሱኧል የአገዛዙ ፋብሪካዎች ሰራ አቁመዋል ፣ እንደልብ ከቦታ ቦታ ተዘዋወሮ መዝረፍ ቆሞኧል ፣ በስርአቱ ውስጥ የለውጥ ሀይሎችና ግለሰቦችን አፍርቶኧል ሰርአቱ በወታደራዊ እና በመረጃ አፈና መዋቅሩ የቆመ ቢመስልም ውስጥ ውስጡን እንደሚፍረከረክ አይቀሬ ነው

ካድሬዎች እንደበፊቱ በህዝባችን ሊፈነጩ ሊቆርጡ እና ሊያስገድሉ እንዳይችሉ በደረሰባቸው ቅጣት በአንዳድ ቦታዎች በቂ ትምህርት አግኝተዋል ሆኖም አሁንም በሰርአቱ በሚሰፈርላቸው ማማለያና መደለያ በማዎቅም ይሁን ባለማዎቅ ህዝባቸውን በመጠቆም ፣ በማስገደል እና በመምራት ለገዳይ አጋዚና ፌደራል ሃይሎች አሳልፎ መስጠት በሀገርና በወገን ጎዳፋ ታሪክ መስራት ከተጠያቂነት እንደማያስመልጥ መረዳት ወቅቱ የሚጠይቀው ሃላፊነትና የዜግነት ግዴታ ነው

በመጨረሻም ለህወአት የማይቀረው የቁልቁለት መንገድ በተጠናከረ መልኩ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በጽናትና በተጠና በሰከነ መልኩ የተለያዩ አሻጥሮችን በመፈጸም በመንግስት ሰራ በመለገም ፣ በቤት ውስጥ በመቀመጥ ፣ የአገዛዙን ምርት ባለመገዛት ፣ የንግድ ተቁዋማትን ማዳከም እንዲሁም ራሰን መከላከልን ጨመሮ ማናቸውንም ትግል በፈረቃ ሳይሆን በኦሮሚያ ፣ በጉራጌ እንደተካሄደው አገዛዙን ምጥ ያሳያዘ ህዘባዊ እምቢተኝነት በተመሳሳይ ቀናቶችና ሰአታት በመላው ኢትዮጵያ መደረጉ ወሳኝ እና የሚደረግ በመሆኑ ሁሉም ኢትዮጵያዊ እንዲዘጋጅ ጥሪው ቀርቡዋል

እንግዲህ ባለካርዶችም ጥልቅ ተሃደሶ ከጠበባችሁ ስር ነቀል ለውጥ ሰፋ ያለ ነውና ሳትወዱ በግድ ከጥበታችሁ እንድምትወጡ ልናረጋገጥላችሁ እየወደድን ካድሬዎች ለህዝባዊ እምቢተኝነት እንቅፋት ወይም ጠንቅ እንዳትሆኑ እናሳሰባችሁኧለን

እግዛብሄር ኢትዮጵያን እና ህዝቦቹዋን ይጠብቃል

ድል ለህዝባችን !!!

ተመስገን ተስፋዬ ከኖርዌይ

Categories: ፖለቲካ

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s