ፖለቲካ

ዳገቱ ላይ አትዛል ጉልበቴ የተራራው ጫፍ ፍቅር ናት ርስቴ

እውቁ ከያኒ ደራሲ ገጣሚ እና ድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን እንደቈዋጨው ታላቅ መልዕክት ባለው ውብ ዜማው የተራራው ጫፍ ላይ ፍቅር የምትባል ርስት አለችን ለሀላችንም የምትሆን ይለናል እሱዋን ለመውረሰ ደሞ በዳገቱ እና መራራው የህዝባዊ አብዮት የትግል ጉዞ ጉልበታችን እንዳይዝል ተራራውን ከወጣን በሁላ ደሞ ቀላል ይሆናል ይለናል

ቴዲ ብላቴናው ሁል ጊዜ መጪ ጊዜን ይቀድማል እንጃ በራይ ይታየዋል መሰለኝ ! ብቻ ለማንኛውም ለሃገራችንና ለህዝባችን ነጻነት ውድ የሆነውን የህይወት ዋጋ ለከፈላችሁ ሎጋ ወጣቶች ከአረመኔው እና ከጨቁዋኙ ህወአት የፌደራልና የአጋዚ እስካፍንጫው የታጠቀ 27 ዓመት የበሰበሰ ስርዓት በባዶ እጃችሁ ጉሮሮ ለጉሮሮ በመተናነቅ ስርዓቱን ወይ እንዲታረም እምቢ ካለም እንዲወገድ የምትፋለሙ ወጣቶች እናቶች አባቶች የቴዲን ጥዑመ ዜማ ተጋበዙልኝ

በቀጥታ ወደ ህዝባዊ እምቢተኝነቱ እናምራ በረጂሙ የዝባዊ እምቢተኝነት ትግል ባለፉት ዓመታት ከ 2015 እስከ 2017 ቄሮ ያቀጣጠለው እሳት ወላፈኑ ህወአትን ክፉኛ በመለብለብ በተለይም በኦሮሚያ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ የአገዛዙን የአፈና መዋቅር በጣጥሶታል

የቄሮዎች ትግል ወደ አማራውና ወደ ተለያዩ የገሪቱ ክፍሎች ለመዛመት ጊዜ አልፈጀበትም ምደክንያቱም በ 27 ዓመታት ከመጠን ባለፈ የአፈና ስርት መዋቅር ፣ የአንድ የትግራይን ህዝብ እንወክላለን በሚሉ የሽፍታዎች ስብስብ የሃገሪቱን ኢኮኖሚያዊና ወታደራዊ ቁልፎችን ሙሉ በሙሉ በመጠቅለል በመላው ህዝባችን ያደረሱት ትውልድ፣ ታሪክ ና ፈጣሪ ይቅር የማይሉት አሰቃቂ ግፎችና በደሎች በመላው ኢትዮጵያውያን በመፈጸሙ ነው

አሁን አዱሱ ትውልድ ለውጥ ይፈልጋል ተወደደም ተጠላም ለውጥ አይቀሬ ሆኖኧል ምን ዓይነት ለውጥ ?

1/  በፊዚክስ ህግ physical change (መስረቱን ሳይለቅ)በቀላሉ ጥገናዊ ለውጥ እንደ
ሀ〉እራሱ ኢሃዴግ የሽግግር ሄደት ፈቃጅ፣ አባልና ተሳታፊ
ለ〉በጠረጴዛ ሁሉንም በሀገሪቷ እና በውጭ ያሉ ተቃዋሚ ሀይሎችን በሀገሪቱ ጉዳይ ያግባኛል የሚሉ ማና ቸውም ተቋማትና ድርጅት መሪዎች ጋ በመደራደር
ሐ〉የጀመረውን ጥልቅ ተሃድሶ በእውነትና በተገቢ ዋስትና በመፈጸም በፍጥነትና በተግባር ማሳየት ነው

2/  chemical change ( በአንድ ወይም ከዛ በላይ ተቃራኒ ሃይል መዋሃድ ግጭት የሚፈጠር ስር ነቀል አካላዊ እና ባህሪያዊ ለውጥ ነው)

በመጀመሪያ በቁጥር 1 ባለው ህግ  27 ዓመት ተቃዋሚ ሃይሎችና ሰፊው የኢትዮጵያ ህዝብ ሳይታክት የህይወት ዋጋ እስክአሁን እየከፈለበት የስርዓቱ ባህሪይ ባለመሆኑ የተፈለገው መልካም አስተዳደር ፣ ፍትሀዊ የሀብት ክፍፍል ፣ የህግ የበላይነት ፣ የፍትህ እጦት፣ አድልዎ ፣ መገለል፣ ከቦታ ቦታ መፈናቀል ፣ የመሬት ነጠቃ ፣ መሰረታዊ ሰብዓዊ መብት ጥሰት እናሱ ለቁጥር የበዙ መብት ገፈፋዎች በተጨማሪም ውስብስብ ውማህበራዊ ፣ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች በመሻሻል ፋንታ የባሰውኑ እያመረቀዙ ፣ እያዡ እና ጠንቅ እየሆኑ እንደሰደድ እሳት ለተቀጣጠለው ህዝባዊ እምቢተኝነት ዋነኛ ምክንያቶች በመሆን ስርአቱ በመጀመሪያው ህግ ለለውጥ ፈቃደኛ ባለመሆኑ ወጣቱ ትውልድ ሁለተኛውን የለውጥ ጥያቄ እንዲያነሳ ራሱ ስርአቱ አስገደዶታል

ወደ ሁለተኛው የለውጥ አይነት ስንመጣ መንግስት በመረጠው ህዝብ ተገዶ በያዘው ትግል ወይም ጥያቄ የአብዮት ቅርጽ እየያዘ መምጣቱ የአደባባይ ሃቅ ሆኖ ሀገሪቱንና ህዝቡዋን በህወአት/ ኢሃዴግ በመነሳት እንደማዕበል ለሁለት እና ከዛም በላይ ዓመታት አሁንም እየናጠው ይገኛል

የተጀመረው የህዝባዊ እምቢተኝነት አሁን ለገዢዎቻቸን ህዝባዊ አብዮት መሆኑ ገብቱዋችዋል ለዚህም ነው ሲራጅ ፈርጊሳ ትላንት ባደባባይ የመሰከረውና ያመነው ምን አልባትም የመጀመሪያው ህጋዊና እውቅና በመስጠቱ በራሱና በመንግስቱ ታላቅ የግብ ጎል ያስቆጠረው

አሁን ከእንግዲህ የኢትዮጵያን ህዝብ የሚያስቆመው አንዳችም ሀይል የለም ስርዓቱም ክፉኛ አቁሱሎታል ኢኮኖሚውን አሽመድምዶታል ፣ የአፈና መዋቅሩን በጣጥሶታል አንድም አዳክሞታል እናም የስርቱን መውደቅ ዋና ዋና ምልክቶች አሳይቶኧል

የአሜሪካና የምዕራባውያን ኢኮኖሚያዊና ሎጅስቲካዊ እርዳታና ትብብር አያድነውም አብቅቶለታል ይህ ማለት ግን የቆሰለው አውሬ የፈሪ ዱላውን በማንሳት ህዝባችንን ለመጨፍጨፍ በድጋሚ የአስቸኲይ ጊዜ አዋጅ በማወጅ በኦሮሚያ ከህዝብ የወገኑ ባለሰልጣናትን ማሰር ከ 15 በላይ ንጹሃን ዜጎችን ገድሎ በመቶ የሚቆጠሩ አቁሰሎ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን ወደ ማሰቃያ ማጎሪያ ካምፖች አግዟል በተጨማሪም ዜጎችን የሚወነጅልበት ከአንታይ ተረሪዝም ህግ ጎን ለጎን አፋኝ አዋጅ ለሰደሰት ወር የሚጸና ህግ በተጭበረበረ እና በግፍ ውሳኔ አጽድቆአል

አሁን ሁሉም ለይቶለታል ህዝቡም መንግስትም ተፋጠዋል ለኢትዮጵያ ህዝብ የሚበጀውም ብችኛው አማራጭ ነጻነቱን ማስከበር በተበታተነ መልኩ ሳይሆን በተደራጀ በተጠና በተቀነባበረ ህዝባዊ እምቢተኝነት ነው

በኦሮሚያ ፣ በጒራጌ ፣ በአማራ እና በተለያዩ የሃገራችን ክፍሎች በቅርቡ የተደረጉት ህዝባዊ እምቢተኝነት አገዛዙን ምን ያህል በኢኮኖሚያዊ ችግር እንዳሰከረውና ክፉኛ እንዳቆሰለው በተጨባጭ አይተናል ይህም በቀጣይነት የምንስራበት የምናየው ይሆናል

በውጭ የሚገኙ ዜጎች የውጭ ምንዛሪ ተአቅቦ ዘመቻ ትልቅ ተጽእኖ በኢኮኖሚው ላይ መፍጠሩ በተጨባጭ እየታየ በመሆኑ ቀጣይነት ስለሚደረግበት አገዛዙን ክፉኛ እንደሚያዞረው ይታመናል

በመጨረሻም ድምጻዊ ቴድሮስ ካሳሁን እንዳለው ዳገት ላይ የ መቶ ሚሊዮን ሀዝብ ጉልበት እንዳይዝል ነው ጥሪ የምናስተላልፈው
ኢትዮጵያዊ የሆንክ ሁሉ ዳር እስከ ዳር ለነጻነትህ ለህልውናህ ለምንወዳት ሃገራችን በጽናትና በቁርጠኝነት ታገል ይሄ አብዮት ካመለጠ የሚጠብቀን የዘለዓለም ባርነት ይሆናል

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ
እግዛብሄር ክንድ ይሁነን !

ተመስገን ተስፋዬ ከኖርዌይ

Categories: ፖለቲካ

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s