ፖለቲካ

አበዮቱ እንዳይቀለበሰ ወጣቱን ከሞት እንታደግ! ለኢትዮጵያውያን ዳይስፖራ  

ለውጥ ፈላጊ የሆነው መላው የሃገራችን በለውጥ ማእበል እየተጕዋዘ እነሆ ሶሰት አመታት ተያይዞታል   በተለየም ወጣቱ ዋነኛ የለውጡ አካል በመሆን ከፈተኛ የህየወት መሰዋትነት እየከፈለ ከአረመኔው የአጋዚ እና የመከላከያ ጦር ጋር ግብገቡን አጠናክሮ አገዛዙን እያንገዳገደው አንዳንድ ለውጠችን ስረአቱን በማሰገደድ የሚከተሉትን ለውጦች በደም በተከፈለ ዋጋ ለታረከና ለትውልድ አኩሪ ሰራ ሰረቷል

1,  የኦሮሚያን ማሰተር ፕላን አስረዞኧል
2,  ከሞላ ጎደል የኦሮሞን ህዝብ ለማእከላዊ መንግሰት እንዳይገብር ክልሉ በራሱ እንዲቆም አስችሎታል
3,  የኦሮሞ ህዝብ ፍርሃትን በመሰበር በመላው ኢትዮጵያ በአማራው እንዲሁም በሁሉም ክልሎች ከፈተኛ መነቃቃትን በመፈጠር ዳር እሰከ ዳር ትግሉን አቀጣጥሎአል
4,  ከሞላ ጎደል የፈደራል መንግሰትን መዋቅር በጣጥሶአል
5,  አንድ ለምስት መዋቅርን ወይም አደረጃጀተን አዳከሞአል
6,  የአገዛዙን ባለስልጣኖች እንዲሁም የካድሬዎችን አላግባብ የተገነቡ ፋብሪካዎችን እና ንብረት አውድሞአል
7,  ታላላቅ የህዝብ ልጆችና መሪዎችን አፍርቶአል
8,  በአገዛዙ ላይ ከፍተኛ የዒኮኖሚ ኪሳራ በጥቅሉ በማድረሰ አገዛዙን ክፉኛ አንገዳገዶታል
9,  ቄሮ  ፋኖ  ዘረማ የሚባሉ የወጣት አደረጃጀት በመፈጠር ትግሉን በመምራት አገዛዙን የፊጥኝ ወጥረውታል
10,  በአገዛዙ አጋር ድርጀቶች እንዱንሁም በቲፒኤልፍ የመዋቅር እና የስልጣን ለውጥ እንዲደረግ አስገደዶአል
11,  ኢሃዴግ ራሱ በስብስብሰናል አጥፍተናል ጥልቅ ተሃደሶ ያሰፈለገናል በሎ ወራትን ባስቆጠረ ግምገማ እስካሁን የተቀደደ ቈምጣውን ሲሰፋ ሲያጠብ መከራውን እያየ እንዲዘልቅ አሰገደዶታል
12,  በመቶዎች የሚቆጠሩ የፖለቲካና የሀሊና እስረኞችን ስርአቱ ተገዶ እንዲፈታ አድርጎአል በአጠቃላይ በርጅሙ አብዮት ትግል ክነዚህ ውጤቶች በተጨማሪ ብዙ ውጤቶችን አስገኝቶአል

በሃገር ቤት ያለው ትግል በውጭ ያለውን ያልተቀናጀ ትግል በልጦና ልቆ ይህን ታላቅ ውጤት ቢያፈራም በዳያስፖራ የትግሉ እንቅስቃሴ የተቀናጀ ባለመሆኑ በሃገር ቤት ያለው ትግል እንዱጉዋተት ምክንያት ሆኖኧል ምክንያቶቹም

1,  ብሄር ተኮር ድርጀቶች መበራከት ተቀራርቦ እና ተስማምቶ አለመስራት
2,  በብሄር የተደራጇ ወያኔ የሚያራምደውን ብሄር ተኮር አደረጃጀት ተቀራራቢ በመሆኑ ለአገዛዙ ምቹ ሁኔታን መፍጠሩ
3,  የተቃዋሚዎች የጎን ለጎን ፍትጊያ ፣ ልፊያ ፣እርግጫ፣መጠላለፍ፣መደነቃቀፍ፣መደነቁዋቆር፣መጯጯህ እና አለመሰማማት
4,  ብሄር ተኮር በሆኑም ሆነ ባለሆኑ የተቃዋሚ ድርጀቶች ተግባብቶና ተሰማምቶ አለመሰራት ህዝባችንን ለ27 ዓመት በወያኔ አስክፊ ጭቆና እንዲረገጥ አድርጎታል

እነዚህ ዋነኛ የለውጥ ሀይላትም ባይሆኑ በሃገራችን ጉዳይ ዝምታን ፣ ቸልተኝነትን ፣ እኔ ምን ችገረኝ ፣ አያገባኝም የማይሉ የወገን ሰቃይ የኔም ፣የሀገር ጉዳይ የኔም ነው የሚሉ እንቅልፍ አጥትው ካላቸው ጊዜ ፣ከገንዘባቸው እና ከውቀታቸው ለሃገርና ለወገን የሚታተሩና የሚደከሙ በጽኑ የወያኔን መንግስት ባደባባይ የሚታገሉ የሰርአቱን የለየለት በአንድ ዘር የተደራጀ የሃገር ሃብት ዝርፊያ ፣ ወታደራዊ የበላይነት ፣ ግድያ፣ አፈናና እሰራት እንዲሁም ሰቆቃ በተለያየ መንገድ ይሚታገሉ ናችው

ሌላው እና ክፍተኛውን ቁጥር የሚይዘው ቸልተኛው ፣ ዝምተኛው፣ አኩራፊው፣ ነጋዴው፣ ባልተኟው፣ተቺው፣ሃገር ቤት የሚመላለሰው እና ሌሎችን የጨምራል
ባጠቃላይ በውጭ ሃገር ተስዶ የሚኖር ኢትዮጵያዊ ቁጥሩ 2 ሚሊዮን እንደሚደርስ ይነገራል
ነገር ግን ክብዙ ውጣ ውረድ በኌላ የመኖሪያ ፍቃድ ሲያግኙ ሀገራቸውን እና የወገናቸውን ስቃይ ይረሳሉ
አንዳንዶች ፖለቲካ አንወደም አንፈልግም ይላሉ ሌሎች ደሞ በትልቅ ፍርሃት ራሳቸውን ይደበቃሉ ወይንም ይስወራሉ
አብዛኞች ደሞ አንድ ሳንቲም ሳያዋጡ ፣ የድርጀት አባል ወይም ደጋፊ ሳእይሆኑ ነጻ ሚዲያ እንደ ኢሳትና ኦማን እንዲሁም የራድዮ ፕሮግራሞችን ይክታተላሉ
ሌሎች ደሞ የተቃዋሚዎችን ቁመት ፣ ስፋትና ጥበት ይለካሉ ፣ይመዘናሉ ፣ ይተቻሉ ፣ይነቅፋሉ ካስፈለገም ይዝልፋሉ
ሌሎች ደሞ ተቃዋሚ ጥርስ አዎጣ  ወይንስ አላወጣም ለመንግስት ማሰረጃ ያቀበላሉ
ሌሎች ደሞ በዕድር ፣ በበዓል፣በስርግ ፣ በልድት፣ በሃዘን ፣በእቁብ እና በእምነት ተቁዋማት ሲገናኙ አብረው በአንድ ላይ ሲሆኑ በሃገር እና በወገን ጉዳይ በጋራ ለመቆም ሲቸገሩና ሲንገዳገዱ ይታያል

ባጠቃላይ አብዮቱ እንዳይቀለበስ ወጣቱ እንዳይገደል እንዲሁም ዒሰብአዊ ድብደባ ፣ በጀምላ እሰረና ሰቆቃ እንዲይደርሰበት ለማሰቆም የሚያስችል አቅምና ጉልበት በዳያሰፖራው እጅ ይገኛል

እንዴት መቃወም እንችላለን ?

ግድያን ፣አፈናን ፣ እስራትን እና ሰቆቃን እንዲቆም በመላው ዓለም የምንገኝ ኢትዮጵያወያን በተመሳሳይ ቀንና ሰዓት በዓለም ላይ ያሉ ከተሞችን አውራ መንገዶች ፣ ዔምባሴዎችን እና ታዋቂ ዓለም አቀፍ ተቋማትን ማጥለቅለቅ

የየትኛውንም ድርጅት አርማም ሆነ መለያ አለመያዝ
አንድ ወይም ሁለት ሰንደቅ ዓላማ በሥምምነት ለመለያ እንዲያገለግል ብቻ መያዝ
ጾታ፣ብሄር ፣የፖለቲካ ድርጅት፣ሃይማኖት እና ልዪነት  ይማይገድበው ሰላማዊ  ሰልፍ በኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባኛል የሚል መለኪያው ስብአዊነት ወገናዊነት እና ሀገርን የማዳን ብሄራዊ መሬት የሚያንቀጠቀጥ አገዛዙን ከምራባውያኑ ጋ የሚያቆራረጥ የጋራ መድረክና ታላቅ ሰላማዊ ስልፍ በማድረግ ብዙ ህይዎትና መስዋትነት የተከፈለበት አብዮት እንዳይቀለበስ ፣  ግድያ ፣ አፈና ፣ እስራት፣ አሰቃቂ ድበደባ እና ሰቆቃ እንዲቆም ባጭር ጊዜ ማድረግ እንችላለን

አንድነት ሃይል ነው !!!
ተመስገን ተስፋዬ ከኖርዌይ

Categories: ፖለቲካ

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s