ማህበራዊ
የንባብ ዘመን ፭ …
የመጋቤ ሐዲስ እሸቱ በኲር መይሐፍ ርጢን ተመርቋል።በሌላው ጊዜ ክቀጠሮ 1 ሰአት አርፍዶ የሚመጣው ሰው ከመግቢያው ሰዓት ት 1 ሰዓት ቀድሞ አዳራሹን አጨናንቆት ነበር። አባታችን ብጹዕ አቡነ ናትናኤልና ብዙ ሊቃውንት በምርቃቱ ላይ ተገኝተዋል። የሲሳይ የበገና ት/ቤት መዘምራን የበገናና የክራር ዝማሬ፣ ዘማሪ ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑና ሊቀመዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍም ተገኝተው የንስሐ ዝማሬን አቅርበዋል። ስለ መጽሐፉ ዳሰሳ በዲ.ን ብርሃኑ አድማስ የቀረበ ሲሆን መጽሐፉ በመጽሐፍ መልክ ሳይሆን በስብከት መልክ የተዘጋጀ እንደሆነ፣ እውቀት በመጨመር፣ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርተ መለኮትን በማስተላለፍና ለአንባብያን ደግሞ በቀጥታ ከእግዚአብሔር ጋር እንዲገናኙ በማድረግ መጽሐፉ ትልቅ ጥቅም እንዳለው ገልፀዋል። ከሁሉም በላይ ደግሞ መጽሐፉ የመጋቤ ሐዲስን ሊቅነት ለማሳየት ሳይሆን ማንኛውም አንባቢ ሊረዳው በሚችለው መልኩ መቅረቡ መይሐፉ ልዩ አድርጎታል። ይላል ዲ/ን ብርሃኑ አድማስ።
በማስቀጠል ሙሐዘ ጥበባት ዲ.ን ዳንኤል ክብረት መጽሐፉን አስመልክትሌ 7ቱን የንባብ ደረጃዎችን በማዘካከር (አንባቢ፣ ማዕምረ መጻሕፍት፣ በላዔ መጻሕፍት ፣ መፈክራነ መጻሕፍት፣ ደራሲያን፣ በዓለ መጽሐፍ፣ መበይነ መጽሐፍ) በቤ.ክ የነበረውን የማንበብና የመፃፍ ትውፊት በማስታወስ፣ መጽሐፉ በነዚህ የንባብ ደረጃዎች የሚያሳዳግ መሆኑን መስክሯል። በማስቀስጠል ደግሞ ረ/ፕ ነቢዩ ባየም “ለየኔታ የተጻፈ ደብዳቤ” በሚል ርዕስ የኔታ በተለያዩ መድረኮች የተናገሯቸውን ወርቃማ ንግግሮችን እያነሳ “እነዚህ የኛ መነባንብ ናቸው” በማለት የእሳቸው ንግግር ምን ያህል ዘመኑና የሚዋጅ፣ የዘመኑን ችግር የሚፈታ መሆኑን በክብር ገልጧል። በስተመጨረሻ መጋቤ ሐዲስ እሸቱ የተለመደውን አስደናቂና ወርቃማ ንግግራቸውንና ምስጋናቸውም ካቀረቡ ብኋላ፤ መጽሐፉ በብጹዕ አቡነ ናትናኤል ተመርቋ። ብጹዕነታቸውም ለመጋቤ ሐዲስ ሌሎች መጻሕፍት እንዲፅፉ አደራ ብለው በጸሎት ዘግተውታል።
ይህች ርጢን የተባለችው መጽሐፍ “ነገረ ድኅነትን” ዋና ጉዳይዋ አድርጋ በ160 ገጾች ተዘጋጅታ በ70 ብቻ የምትሸመት፣ ወርቅ ከሆኑት ሊቅ የተፈለቀቀች ወርቅ መጽሐፍ ናትና ያንብቧት። ርጢን ማለትም ትርጉሙ … በመጽሐፉ መግቢያ ገጽ 14 ያገኙታል።
 ሙሐዘ ጥበባት ዲ.ን ዳንኤል ክብረትም ያዘጋጀውና በቅርቡ በ”ክልስ ዕትም” ይበልጥ ተብራርቶና ሰፍቶ የወጣ “#ራእየ_ዮሐንስ” መጽሐፍን በማስመልከት ታላቅ ጉባኤ እንዳዘጋጀ ታውቋል።የካቲት 10 2010

Categories: ማህበራዊ

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s