ሬዲዮ ዘመራ

ስም ያጣሁለት ዘመነ ህወሓት በአርሴማ መድህኑ

ዘመነ ሰማዕታት በቤተ ክርስቲያናችን ታሪክ መሠረት የስደት ዘመን በመባል ይታወቃል። ሰማዕት የሚለው ቃል በሃይማኖታዊ አስተምሕሮ ስንመለከተው ስለ እግዚአብሔር፣ ስለ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በአጠቃላይ ስለ ሃይማኖታቸው እውነትን በመመስከራቸው፤ ጀርባቸውን ለግርፋት፣ ሰውነታቸውን ለእሳት፣ አንገታቸውን ለስለት አሳልፈው ለሰጡ፤ በድንጋይ ተወግረው፣በስለት ተቆርጠው በስጋቸው ሞተው በነፍሳቸው የለመለሙ ናቸው።
በዘመነ ወያኔ ደግሞ በየቤተክርስትያኑ እና በየመስኪዱ ሰማእት የሚሆኑት ለሃገራቸው እና ለነጻነታቸው የሚጮሁ ናቸው። በዚህ ባሳለፍነው በ26 የስቃይ ፣የመከራና የግፍ አመታት በበደኖ በአርባ ጉጉ፣ በአማራ፣ በኦሮምያ ፣በሶማሌ ክልል፣ ከፋ፣ ጋምቤላ፣ አምቦ፣ ወለጋ፣ ጎንደር፣ ወሎ፣ ሸዋና ጎጃም ጎንደር ወዘተ በሁሉም የአገሪቱ ክልል የተገደሉ ወገኖች ቁጥራቸው በሚሊዮን እንደሚቆጠር እራሳቸው ገዢዎቹ መስክረዋል።

እነዚህ ወገኖች ጸረ ሰላም፣አሸባሪ፣ዘራፊ፣ትምክህተኛ እና ሌላም ሌላም ስም እየተሰጣቸው ቢገደሉም እውነቱ ግን ሌላ ነው ፍትህ እውነት እና እኩልነት።
በዚህ ዘመን እኮ ጳጳሳት በቆሙበት አባቶች ተግድለዋል! ሰማእትነትን ተቀብለዋል የአገራቸው ክብር ሰላም እና ፍቅር እንዳይናጋ የፈረሰው እንዲጠገን የተጣመመው እንዲቃና እንጂ ስልጣን እና ሹመት የፈለጉ አልነበሩም በአደባባይ በጥይት የተደፉት እኔስ ለዚህኛው ዘመን ስም አጣሁለት ከውጪ ለመጣ ወራሪ እጅ እና አገር አንሰጥም ብለው እነ አቡነ ጴጥሮስ ለጣልያን እንኳን እኛ ምድሪቱ አትገዛ እያሉ ምድሪቱን እየገዘቱ ትሰይፈዋል። የብፁዕ አቡነ ጴጥሮስን የዕምነት ፅናት፥የሃገር ፍቅርን ስናይ ሁሌም ከልባችን ፅላት ላይ ተፅፈው የሚኖሩ የሃይማኖት አርበኛና አገር ወዳድ ጀግና ቅዱስ አባት ናቸው። ስለእውነት እስከ መጨረሻው የመከራ ጥግ ድረስ ታግለው አለማዊ ነገር ሳያሸንፋቸው ኢትዮጵያዊነት ዋጋዋ ምን ያህል እንደሆነ ያስመሰከሩ ኩሩና ደፋር አባታችን ናቸው!
ዛሬም የአባቶቻቸውን አሰረ ፍኖት የተከተሉ ወጣቶች፣እናቶች እህቶች እና ወንድሞች ህጻናት ሳይቀሩ በስልጣን ጥመኞች እየተሰው ይገኛሉ።

ኢትዮጵያ ለአገርና ለሃይማኖታቸው የተሰዉ ብዙ ጀግናና ቅዱሳን አባቶችን ያፈራች አገር ናት ነገም ታፈራለች!!ህወሃት ማለት ሰው ሆኖ ተፈጥሮ ከሰው ያነሰ ሰብ-እና ያለው ግፈኛ እና አገር ሻጭ ሌባ ነው። ለህወሃቶች ያልገባቸው ኢትዮጵያዊነት ከምንም በላይ ታላቅነት ነው። ይህን ማመን ያስፈልጋል። ህወሃት አገርና ወገን የሚባል ሚስጥር ሳይገባው የራሱንም ክብር አገርና ወገኑን ለባዕድና ለአልፎ ሄያጅ አሳልፎ የሚሰጥ ገዳይ ጨካኝ እና ዘራፊ ቡድን ነው።

የአገርና እና የሃይማኖት ሚስጥሩና ትርጉሙ ሳይገባቸው ብርኩናቸውን ለቁራሽ እንጀራ በምስር ወጥ የሸጡ ህዝብን በጥይት መድፋት ጅግንነት የሚመስላቸው ጨካኞች እንደ ባለ እራዕይ መሪያቸው የክብር መቃብር እንኳን አያገኙም!!ጊዜው ቅርብ ነው በየ አስፓልቱ የፈሰሰው የንጹህ ወገኖች ደም ይፋረዳቸው!!

ክብር ነጭ ለብሰው ወጥተው በደም ተጨማልቀው በታቦቱ ስር ለወደቁ ምስኪን የወልድያ ወንድም እና እህቲኦቻችን ይሁን ነብሳችሁን በገነት ያኑርልን የተሰየፋችሁላት አገር እና ህይማኖታችሁ ትንሳኤዋ ቅርብ ነው!!

Categories: ሬዲዮ ዘመራ

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s