ፖለቲካ

የወያኔ “ዕዉራን” ምሁራን የሚጠነስሱት ሴራ ያብቃ ቢንያም ሙሉጌታ

የወያኔ “ዕዉራን” ምሁራን የሚጠነስሱት ሴራ ያብቃ
የወያኔ ህወሃት ባለስልጣናት የኛ የሚሏቸውን የትግራይ ምሁራንና ካድሬዎቻቸውን
ብቻ ለይተው ለመጥቀም እንዲሁም ሌላኛውን ለመጉዳትና ለማሸማቀቅ ላለፉት 26
ዓመታት በሁሉም ኢትዩጵያዊ መታወቂያ ላይ ዘር እንዲጠቀስ በማድረግ ከፍተኛ
የሆነ አገርን የማፍረሻ ቫይረስ ሲረጩ ቆይተዋል።
ይህ ህወሃት ወያኔ የረጨው የዘር ቫይረስ የትግራይ ህዝብ ሙሉ በሙሉ
እንደተስማማው እርግጠኛ መሆን ባይቻልም ነገር ግን ትግራይ ውስጥ ምንም
አይነት ተቃውሞ የማይሰማው አንዳንድ የትግራይ ፀሀፊዎች እንደሚሉት በትግራይ
ብዙ ጭቆና አለ በትግራይ የሌለውና የጠፋው ጭቆናውን የሚያጋልጥ ነው እያሉ
ሲሉ እንሰማለን። ሆኖም ግን ሌላው ኢትዩጵያዊ በወያኔ ህወሀት ቀንበር ተጭኖበት
ሲገደል ሲታሰር ብዙ በደል ሲፈፀምበት የትግራይ ህዝብና ምሁራን ዝምታ የተለመደ
ነው።
ህወሀት ወያኔ በመታወቅያ ወረቀት ላይ የጠመደው የዘር ፈንጂ ሌላውን ኢትዮጵያዊ
እያጠፋ እየበታተነ እየከፋፈለ እንዳለ የትግራይን ህዝብና ሙሁራን እንደሚያቁ
ግልፅ ነው። ገዢው ፓርቲ ኢትዩጵያን በዘር የመከፋፈል ክፉ አጀንዳ ብዙዎችን ዋጋ
አስከፍሏል። በቅርብ ግዜያት እንኳን ብዙ ታዝበናል። በጉራ ፈርዳ የአማራ
ተፈናቃዮች ከ20 ዓመታት በላይ ከኖሩበት መሬታቸው አማራ ስለሆናችሁ በዚህ ክልል
መኖር አትችሉም ተብለው ተፈናቅለዋል እንዲሁም በኦሮሚያ እና ሶማሊያ አካባቢ
ህወሀት ወያኔ ሆን ብሎና አቅዶ የእርስበርስ ግጭት በመፍጠር በሁለቱም
አካባቢዎች የሚገኝ በብዙ ሺህ የሚቆጠር ዚጎቻችን ህይወታቸውን ንብረታቸውን
አጥተዋል። ለዘመናት ከኖሩበት የመኖርያ አካባቢያቸውም ተሰደዋል።
ወያኔ ህወሀት እንደዚህ የመሳሰሉ የእርስ በእርስ ግጭቶችን በብዙ ኢትዩጵያ
አካባቢዎች ላይ ተግባራዊ አድርጓል እያደረገም ነው። አሁን ግን ግጭቱም በማንና
ለምን እንደሚፈፀም ሁሉም ኢትዩጵያዊ ጠንቅቆ ተረድቶታል። ይህ አምባገነን ገዢ
በሀገሪቱ ላይ ያለው የህዝቦች አንድነት፣ሰላም እና መግባባት እንዲቀጥል ፈፅሞ
አይሻም። ለምሳሌ በኦርቶዶክስ ሀይማኖት በየገዳማቱ ላይ እያደረሰ ያለው ጥቃት እና
በሀይማኖቱ መሪዎች መካከል በጳጳሳቱ እንዲሁም በሊቀ ጳጳሳቱ ብሎም በሲኖዶሱ
መካከል ሰርጎ በመግባት ሀይማኖቱን ለማበጣበጥ እና ለመከፋፈል ባደረገው
እንቅስቃሴ አሁንም ድረስ ህዝበ ክርስቲያኑን እንዳሳዘነ እና እንዳስቆጣ ይገኛል።
በየእምነት ተቋማቱ ውስጥ ወያኔ እጁን በማስገባት ችግር ፈጣሪዎቹ እነሱ
መሆናቸው እየታወቀ መፍትሔ አፈላላጊ አካል ነን ብለውም ከፊት የሚቆሙት
ራሳቸው ናቸው። በኢትዩጵያዊው ሙስሊሙ ህብረተሰብ ውስጥ አክራሪነትንና
ሽብረተኛነትን ለመዋጋት በሚል የይስሙላ ፖሊሲ ነድፈው ሙስሊም ህብረተሰብን
ለመከፋፈል ለመበታተን ለማጋጨት ብዙ ደክመዋል። በእነዚህና መሰል ብዙ
ቀውሶች ወቅት ከትግራይ ተወላጅ ሙሁራን የአገዛዙን የተዛባ ፍትህ የሚያወግዝ
ድምፅ እረጭ ፀጥ ማለቱ ያሳዝናል። ከፋሺስት ወራሪ ጦር ኢትዩጵያ ሀገራቸው
ለመታደግ የተዋደቁት ቀደምት የትግራይ ተወላጆች አጥንት ይወቅሳቸዋል። የፈሰሰ
የደማቸውም ጩኽትም ከተኙበት ወያኔያዊ አዚም ያነቃቸው ዘንድ እመኛለሁ።
አምባገነኑ የትግራይ ወያኔ በሀገራችን ኢትዮጵያ ላይ ያለው ግልፅ የሆነ ደባ ከዚህ
በኋላ ሊቆም ይገባል። ሀገሪቱን እንደነ ዮጎዝላቪያ፣ሶማሊያ፣ሩዋንዳ እና ሶሪያ
ለመበታተን አንግቦ የተነሳውን አጀንዳ ማስቆም የግድ ነው። ይህንን አምባገነን
ሰይጣናዊ ስርዓት በጊዜ ካለመወገዱ የተነሳ ለአዲሱ እና ተተኪው ትውልድ ተሻጋሪ
ጥፋትና ቀውስ ፈፅሟል። በአማራው፣በጋምቤላው በኦሮሞው በአፋሩ በተቀረው
ኢትዮጵያዊ ላይ እያነጣጠረ በመፈፀም ላይ የሚገኘው ጥቃት ፈተናውና መዘዙ
ውሎ አድሮ የኋላ ኋላ ለራሱ ለትግራዮም ተወላጅ መትረፉ የማይቀር ነው።
የኢትዮጵያ መከራ እንዳያበቃ በማድረግ እና የህወሀት ወያኔ መሪዎችን እድሜ
የሚያረዝመው ዘረኝነት ህሊናቸውን ያሳወራቸው የትግራይ “ዕዉራን” ምሁራን
የሚጠነስሱት ሴራ የበለጠ ሀገሪቱን ወደ ውስብስብ ችግር ውስጥ እየከተተ ይገኛል።
እነዚሁ ህጋዊ የሆኑ ዘራፊ ቡድኖች የሀገሪቱ ሀብት ምዝበራ ላይ በዋና ተጠቃሚ
ስለሆኑ ስለሚፈጠረው ቀውስ እና ስለ ነገይቱ ኢትዮጵያ ምንም አይገዳቸውም።
እነርሱ የሚረጩት መርዝ ብዙ ታማሚዎችንም አፍርቷል። ዛሬም ህልማቸው መዋለ
ንዋይ ብቻ ነው። መዝረፍ ማድከም ባዶ ማድረግ አላማቸው ነው። የትግራይ ህዝብ
ከወያኔ ጋር አብረው ኢትዮጵያዊነትን የሚያፈርሱ ዘረኝነትን የሚያስፋፉ
በመሆናቸው ታሪክ ይፋረዳቸዋል።
በአሁን ወቅት ገዢው ፓርቲ ከግብር አበሮቹ ጋር በመሆን ኢትዮጵያዊነት ትርጉመ
ቢስ ደረጃ ያደረሱት መስሎ ቢሰማቸውም፤ ኢትዮጵያዊነት ግን በደም ውስጥ ያለ
የማይቀየር ማንነት ነው። በህወሀት ወያኔ እና በትግራይ ዕዉራን ምሁራን ጥምረት
የሚመራው የዘር ማጥፋትና ኢትዮጵያዊነትን ማፅዳት ዘመቻ የረዘመ ዘመን
ያስቆጠረ መሆኑ ግልፅ ቢሆንም፤ገና የትጥቅ ትግል ሲጀምር ኢትዮጵያዊነትን
ማዳከም አማራውን እና ኦሮሞውን በማጣላት ማህበራዊ ህይወቱንም ማናጋት
አጀንዳው ነበር። ይህንን በሀገሪቱ ላይ ለ26 ዓመት በአምባገነንነትና በዘረኝነት
ስልጣንን ለብቻው በመያዝ የሚገዛው ወንበዴ ቡድን ማንና ምን እንደሆነ
ኢትዮጵያዊ የሆነ ሁሉ ጠንቅቆ ስለተረዳው በተባበረ ክንድና በአንድ ኢትዯጵያዊት
የሚያምን ሁሉ ከፊት ለፊቱ ያለውን ሀገር አድኑን ተጋድሎ እየተባበረ ወያኔ ህወሀትን
የሚማርክበት “ዕዉራን” ምሁራን ትግራዮችን የሚስቆምበት ወሳኙ ጊዜ አሁን
ነው።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!

Categories: ፖለቲካ

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s