ሬዲዮ ዘመራ

Zemera Radio Weekly News 01 oct 2017

በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል አፋጣኝ የምግብ እርዳታ እንደሚያስፈልግ  የተባበሩት መንግስታት አስታወቀ

በሺዎች የሚቆጠሩ የኦሮሞ ተወላጆች ከሶማሌ ላንድ መፈናቃላቸው ተገለጸ

ኢትዮጵያ በየጊዜው ኢንተርኔትን አገልግሎት በመዝጋቷ ከ130 ሚሊዮን ዶላር በላይ እንዳጣች መገለጹ የዛሬ አበይት ዜናዎች ናቸው

ዝርዝር ዜናዎች

በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል አፋጣኝ የምግብ እርዳታ እንደሚያስፈልግ  የተባበሩት መንግስታት አስታወቀ

በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል አፋጣኝ የምግብ እርዳታ እንደሚያስፈልግ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት  አስታወቋል፡፡ የመንግስታቱ ድርጅት የምግብ እርዳታ ማስተባበሪያ ፋኦ ባወጣው ሪፖርት እንደጠቆመው፤ በሶማሌ ክልል ሁለት ሚሊዬን 300 ሺህ ሰዎች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው አስታውቋል፡፡ በክልሉ ለድርቅ ተጎጂዎች ተብሎ የተቀመጠው ምግብ ማለቁን የገለጸው ፋኦ፣ በአሁን ሰዓት ከሶማሌ ክልል ህዝብ 42 በመቶ የሚሆነው ለአስቸኳይ የምግብ እርዳታ እንደተጋለጠ ይፋ አድርጓል፡፡ በክልሉ ከሰው በተጨማሪም እንስሳት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኙ ሪፖርቱ አትቷል።የምግብ እርዳታው በአስቸኳይ የማይገኝ ከሆነ በአካባቢው አስከፊ የሆነ  የሰብዓዊ ቀውስ ሊፈጠር እንደሚችል ከወዲሁ በሪፖርቱ አስገንዝቧል።በሚቀጥለው ወር ይጥላል ተብሎ የሚታሰበው የዝናብ መጠንም አነስተኛ እንደሚሆን  ስጋቱን ገልጿል።በሶማሊ ክልል ባለፈው ሰኔ ወር ብቻ 69 ህፃናት በምግብ እጦት መሞታቸውን ድንበር የለሽ የሀኪሞች ማህበር መግለጹ የሚታወስ ነው። የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልልን ጨምሮ በኦሮሚያ፣ በአማራ፣ በአፋር እና በደቡብ ክልሎች የተከሰተው የድርቅ አደጋ አሁንም አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ይገለጻል። በኢትዮጵያ በአጭር ጊዜ ውስጥ አስቸኳይ የምግብ እርዳታ የሚያስፈልገው የህዝብ መጠን  ወደ  9 ሚሊዮን ማሻቀቡን ባለፈው ወር የተባበሩት መንግስታት ይፋ ማድረጉ ይታወሳል፡፡

በሺዎች የሚቆጠሩ የኦሮሞ ተወላጆች ከሶማሌ ላንድ መፈናቃላቸው ተገለጸ

በምስራቅ ኢትዮጵያ በኦሮሞና በኢትዮጵያ ሶማሊ ጎሳዎች የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ በሺዎች የሚቆጠሩ የኦሮሞ ተወላጆች ከጎረቤት ሶማሌ ላንድ መፈናቀላቸውን ተነግሯል፡፡  የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት እሮብ ለሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን እንደገለጹት፣ ከሶስት ሺህ በላይ የኦሮሞ ተወላጆች ከጎረቤት ሀገር ሶማሊ ላንድ መፈናቀላቸውን ገልጿል። ከሶማሌ ላንድ የተፈናቀሉት የኦሮሞ ተወላጆች  በውጫሌ አካባቢ በጊዜዊነት ተጠልለው እንደሚገኙ ታውቋል።በኦሮሚያ እና በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የተፈጠረው ግጭት አሁንም ሁነኛ መፍትኤ አለማግኘቱን ተከትሎ፣ አልፎ አልፎም ቢሆን ግጭት እንደሚከሰት ይነገራል። በኦሮሞና ሶማሊ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች በተነሳው ግጭት ከ400 ሰዎች በላይ እንደሞቱ መረጃ አለኝ በመማለት አዲስ አድማስ ባለፈው ሳምንት እትሙ ዘግቧል።የመንግስት አፍቃሪ የሆኑ ሚዲያዎችም  ግጭቱን ተከትሎ በሁለቱም ወገኖች ከ250 ሺህ ሰዎች በላይ ከቀያቸው መፈናቀላቸውን እየዘገቡ ነው።በሀረር፣ጭናቅሰንና ውጫሌ  አካባቢ በጊዜዊነት የተጠለሉ የኦሮሞ ተወላጆች በግዳጅ ወደ ትውልድ መንደራቸው በመሄድ በቋሚነት እንዲሰፍሩ እየተደረገ መሆኑ እየተነገረ ነው።

ኢትዮጵያ በየጊዜው ኢንተርኔትን አገልግሎት በመዝጋቷ ከ130 ሚሊዮን ዶላር በላይ እንዳጣች ተገለፀ

ኢትዮጵያ ባለፉት ሁለት ዓመታት ለ36 ቀናት ያህል የበይነ-መረብ አገልግሎቶችን በዘጋችበት ጊዜ ከ130 ሚሊዮን ዶላር በላይ አጥታለች ሲል የምሥራቅ እና ደቡባዊ አፍሪካ ዓለም አቀፍ የመረጃ ቴክኖሎጂ ፖሊሲ ትብብር የተሰኘው ተቋም ገለፀ።

የተቋሙ ጥናት የኢንተርኔን መዘጋት በሃገራት ምጣኔ ሐብት ላይ ያደረሰውን ጉዳት በተለያዩ መለኪያዎች የገመተ ሲሆን፤ በዚህም መሰረት ኢትዮጵያ ለ36 ቀናት ያህል ኢንተርኔትን በዘጋችበት እንዲሁም በየጊዜው በሚፈጠረው የማህበራዊ ሚዲያ መናወጥ በጥቅሉ ከ130 ሚሊዮን ዶላር በላይ ማጣቷን አብራቷል።ኢንተርኔት በተዘጋበት በእያንዳንዱ ቀን  ከ3.4 ሚሊዮን ዶላር በላይ፤የመልክዕት ማስተላለፊያ መተግበሪያዎች  በታወኩበት አንድ ቀን ደግሞ ከ870 ሺህ ዶላር በላይ አገሪቷ ታጣለች ሲል ጥናቱ ግምቱን አስቀምጧል።ኢትዮጵያ ህዝባዊ አመፆች በተከሰቱ ቁጥር የኢንተርኔት አገልግሎት የሚቋረጥ አልያም የሚታወክ እድል ይገጥመዋል።ባለፈው አመትም ብሔራዊ ፈተና በሚሰጥበት ወቅት ፈተና ሾልኮ እንዳይወጣ  ለመከላከል በሚል ኢንተርኔት ሙሉ በሙሉ መዘጋቱ የሚታወስ ነው።

ጣናን ለመታደግ የሚደረግው ርብርብ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ተጠየቀ

ከለፉት ዓምስት ዓመታት ወዲህ በጣና ሀይቅ ላይ የተከሰተውን የእምቦጭ አረም ሙሉ በሙሉ  ለማጥፋት የተጀመረው ርብርቦሽ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ተጠየቀ።ከክልሉ የአካባቢ ጥበቃ ቢሮ የተገኘው መረጃ እንደሚጠቁመው፤በአረም ከተሸፈነው 40 ሄክታር የሀይቁ ከፍል በህብተረሰቡ ጥረት የጸዳ ቢሆንም አሁንም ከ10 ሄክታር በላይ በአረም ተሸፍኖ እንደሚገኝ ተገልጿል።በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት UNESCO በስነ-ህይወት ብዛህነት የተመዘገበው ጣና ሐይቅ ከተጋረጠበት አደጋ  ማዳን የሁሉም ኢትዮጵያዊ ሀላፊነት ነው በማለት  የአካባቢው ነዋሪዎች ጥሪ እያቀረቡ ይገኛሉ።አረሙ በጊዜ እርምጃ ካልተወሰደበት በአባይ ግድብም በሂደት አሉታዊ ተጽዕኖ እንደሚያሳድር የዘርፉ ባለሙያዎች እያስጠነቀቁ ነው።

ለጣና ያላቸውን አጋርነት ለመግለጽ ዛሬ እሁድ የተለያዩ የእግር ኳስ ክለቦች “የጣና ሳምንት” በማለት የወዳጅነት ጨዋታ አንደሚያደርጉ የወጣው መርሃ-ግብር ያሳያል። በዚህም መሰረት ባህርዳር ከተማ ከአውስኮድ ፣ፋሲል ከተማ ከቅዱስ ጊዮርጊስ፤ በባህርዳር ዮኒቨርሲቲ ስታዲየሞ  ዛሬ ይጫወታሉ።እሮብ በ24  ባህርዳር ከተማ ከቅዱስ ጊዮርጊስ  እንዲሁም  በ27 ቅዳሜ  አውስኮድ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ለጣና እንደሚጫወቱ ታውቋል።

የኢትዮጵያ ምንግስት  በጎረቤት ሃገራት ያሉ ስደተኞችን በማስገደድ ወደ ሀገር ቤት ይመልሳል የሚለውን የሂዩማን ራይትስ ዎችን ክስ አስተባበለ

ሳምንት ሂዩማን ራይትስ ዎች የተሰኘው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ቡድን የኢትዮጵያ መንግሥት እንደ ኬንያ ባሉ ጎረቤት ሃገራት ተጠልለው የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን  የዓለም አቀፉን ህግ በመጣስ ወደ ሀገር ቤት አስገድዶ እንደሚመልስና የተለያዩ የማሰቃየት ተግባር እንደሚፈጽምባቸው ባለፈው ሳምንት አሳውቆ ነበር። በኬንያ ተጠልሎ የሚኖር አንድ ኢትዮጵያዊ ለቢቢሲ ምስክርነቱን ሲሰጥ “የኢትዮጵያ መንግሥት የደህንነት ሰዎች ባለፈው ሰኔ ወር አፍነው ሊወስዱት እንደሞከሩ አስረድቷል።”  ይህንን ተከትሎ በናይሮቢ የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት ዲና ሙፍቲ “ስደተኛ ኢትዮጵያዊያንን በህገ-ወጥ መንገድ ወደ ሀገር ቤት ለመመለስ መንግስታቸው እንዳልሞከረ ማስተባበያ ሰጥተዋል።” የኢትዮጵያ መንግሥት መሰል ወቀሳዎች እና ክሶች ሲቀርቡበት ይህ የመጀምሪያው አይደለም። የመብት ተሟጋች ደርጅቶች የኢትዮጵያ መንግሰት በስደት የሚኖሩ የፖለቲካ ሰዎችን  ከሌላ ሀገር አስገድዶ በመመለስ የተባበሩት መንግስታትን የስደተኞችን ሕ ህግ  ይጥሳል በማለት ይከሳሉ።

 

 

 

Categories: ሬዲዮ ዘመራ

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s