ሬዲዮ ዘመራ

ኢሬቻ የምስጋና በአል!!

አገራችን ኢትዮጵያ ዛሬ ታሪክን የሚያጣምሙ ገዢዎች እንደሚሉት ሳይሆን   የሦስት ሺህ አመት ታሪክ ያላት አገር ናት።  አንድንድ ጸሓፊዎች፣ ከዚህም አልፈው፣ ወደፊትም ተራምደው፣ ይህቺ አገር፣ከአምስት ሽህ አመት በላይ እንደኖረችና እንደቆየችም፣ይናገራሉ። ሌሎቹ፣ ደግሞ ሰባት ሽህ አመት  የሚለውን አሃዝ፣ ለእኛ  ይመርጣሉ ተመራማሪ ጠበብቶች፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ቆፍረው ከአገኙት ጥንታዊ ቅርሳ-ቅርሶች ተነስተው፣ ከአርባ ሽህ አመት በፊት፣ የሰው ልጆች ፣ አሁን  ኢትዮጵያ ተብሎ በሚታወቀው ግዛት ውስጥ፣ ይኖሩ  እንደነበርም ፣በደረሱበት ጥናታቸው፣ ሁሉም ተስማምተው  ይህን ሐቅ  በአንድነት ያረጋግጣሉ።ከዚህም የተነሳ ኢትዮጵያ  የሰው ልጅ ከጥንት ጊዜ ጀምሮ የኖረባት ቦታ እንደሆነች ብዙ የሳይንሳዊ መረጃዎች ያረጋግጣሉ። ኢትዮጵያ ከ  (82) በላይ የሚሆኑ ብሔረሰቦች የሚገኙባት «የብሄረሰቦች ሙዚየም» ልትሰኝ የቻለች ድንቅ  ሀገር ነች።ከዚህ ጋር ተያይዞ እነዚህ ብሄረሰቦች የራሳቸው የሆነ ቋንቋ እና ባህል አላቸው   ባህል ደግሞ በአንድ ማህበራዊ ቡድን ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች የሚማማሩት፣ የሚፈጥሩትና የሚለዋወጡት የባህሪና የእሣቤ መወራረስ ነው። አንዱን ማህበረሰብ ከሌላኛው የምንለይበት ከመሆኑም በላይ ሰዎችንም ከእንሠሣት ለመለየት ባህል አይነተኛ ሚና አለው። የአንድ ህዝብ ባህል ስንልም እምነታቸውን፣ የሥነምግባር መመሪያቸውን፣ ቋንቋቸውን፣ የአምልኮ ሥርአታቸውን፣ ሙያቸውን፣ የቴክኖሎጂ ፈጠራቸውን፣ የአለባበሣቸውን ሁኔታ፣ የምግብ አመራረታቸውንና አዘገጃጀታቸውን፣ የፖለቲካና የምጣኔ ሀብት ሥርአታቸውን ሁሉ ያጠቃልላል ።ለዛሬው የምንዳስሰው ወቅታዊ የሆነውን የኢሬቻን  በአል የአከባበር ባህል ነው

ኢሬቻ ምንድነው

በኦሮሞ ባህል የሚታወቅ እና በየአመቱ የሚከበረው የኢሬቻ ባህል ብዙዎች እንደሚሉት አምልኮ ሳይሆን ባህል ነው። እሬቻ ማለት መስማማት፣ አንድነት፣ እርቅ ፣ማለት ነው ። ማን እና ማን ነው የሚታረቀው ቢባል በክረምት ወራት ዘመድ እና ዘመድ በዝናብ እና በውሃ መሙላት ምክንያት ተራርቆ ሳይገናኝ ክረምቱን ሰልሚያሳልፍ ውሃው ሲጎድል እግዚአብሄር ታረቀን፣ ምህረት አደረገልን፣ በውሃው መሙላት ምክንያት የተለያየን ቤተሰቦች እንድንገናኝ አደረገን፣ በእድሜያችንም ላይ አዲሱን ዘመን ጨመረልን ማለት ነው።ባጠቃላይ ”ኢሬቻ የምስጋና ቀን ነው።

በየአመቱ የሚከበረው የኢሬቻ በዓል  በቢሾፍቱ ሆራ አርሰዲ በሚሊዮን የሚቆጠር  ህዝብ የሃይማኖት ልዪነት ሳይገድበው ከእራቱም አቅጣጫ በመሰባሰብ እርጥብ ሳር እና አደይ አበባ በመያዝ ለዋቃ ወይንም ለእግዚአብሔር ምስጋና ያደርሳሉ የ2010 የኢሬቻ በአል የሚከበረው በሃዘን እና በቁጭት ነው

ባሳለፍነው የ 2009 አመተ ምህረት እንደወትሮው ሁሉ ኢሬቻን ሊያከብር ባማረና ባሸበረቀ ጌጣጌጥ እና በባህል ልብስ አጊጦ አምላኩን ሊያመሰግን  በእጁ  ቄጤማ ይዞ የተመመው ህዝብ ባላሰበው እና ባልጠበቀው ቅጽበት ወደ አፈር የተቀየረበት ነብሰ-ጡር ፣ወጣት፣አዛውንቱ፣ህጻናትን ጨምሮ ከአፈር የተዋሃዱበት፣የብዙዎችን ደስታ ወደ ዘላለም ሃዘን የተለወጠበት አሰቃቂ እና አሳዛኝ አመት ነበር በእለቱ ከሁለት ሚሊዮን አምስት መቶ ሽህ በላይ ሰዎች መገኘታቸው  በተለያዩ ሚዲያዎች የተገለጸ አሃዝ ነበር።

 ‘ሂውማን ራይትስ ዋች’ የተሰኘው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ቡድን የ2009 ዓ.ም የኢሬቻ በዓልን አስመልክቶ በቅርቡ ባወጣው ሪፖርት ”ፀጥታ ኃይሎች አስለቃሽ ጭስ በመጠቀማቸው እና መውጫ መንገዶችን በመዝጋታቸው በተፈጠረ ግርግር በመቶዎች ሊቆጠሩ የሚችሉ ሰዎች ተረጋግጠው ሞተዋል” ብሏል።

በባለ 33 ገፁ ሪፖርት ላይ እንደተጠቀሰው፤ ተረጋግጠው ከሞቱት ሰዎች በተጨማሪ በጥይት ተመተው የተገደሉም እንዳሉ ቡድኑ አረጋግጫለሁ ብሏል።

የኢትዮጵያ መንግሥት ለጠፋው ህይወት ፀረ-ሰላም ያላቸውን ኃይሎች ተጠያቂ አድርጎ ነበር።አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝም የፀጥታ ኃይሎችን ”ስላምና መረጋጋትን” አሰፍነዋል በማለት አመስግነው እንደነበር ሪፖርቱ አስታውሷል።

በዕለቱ የሞቱትን ሰዎች ቁጥር የኢትዮጵያ መንግሥት 55 ነው ሲል፤ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ደግሞ 678 ያደርሰዋል። ሲል ቬኦኤ ዘግቧል

በእለቱ ወያኔ ይውረድ የሚለው የህዝብ ተቃውሞ ያስፈራው ህወሃት ቀድሞውንም ተዘጋጅቶበት ስለነበር ቃታውን ሲስብ ጊዜ አልፈጀበትም በቅርቡም የኢሬቻ ሰለባዎች አንደኛ ዓመት መታሰቢያ ከመድረሱ አንድ ወር አስቀድሞ  መታሰቢያ ሀውልት አቁሞላቸዋል በመታሰብያ ሃውልቱ ላይም ላይ ማቾቹ “በድንገተኛ ሞት” ህይወታቸውን እንዳጡ ጽፏል ይህም ከፍተኛ ቁጭት እና ትችትን  ቀስቅሷል፡፡የሚያሳዝነው ሆን ብሎ በአስለቃሽ ጭስ እና በጥይት የፈጀውን ህዝብ በድንገት የሞቱ ብሎ ሃውልት ማቆሙ  የቆሰለውን የኢትዮጵያ ህዝብ በቁስሉ ላይ ጨው እንደመጨመር ይቆጠራል

ዛሬም የኢሬቻ በአል በቀረበበት ወቅት የሚጋጭ እና የሚጣረስ የባኣል አከባበር ፕሮግራም መውጣቱ ግርምትን ፈጥሯል በዘንድሮው የኢሬቻ በዓል ላይ የብሄራዊ ደህንነትን ጨምሮ፥ የመከላከያ ሰራዊትና ፌደራል ፖሊስ ፀጥታ የማስከበር ስራ እንደሚሰሩ የፈደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀኔራል አሰፋ አብዩ ይፋ አደረጉ። ኮሚሽነሩ በተለያዩ ሚዲያዎች የተዘገቡትን ዜናዎች በቀጥታ ባያስተባበሉም፣ ከዜናዎቹ በተቃራኒ ልዩ ጥበቃ እንደሚደረግና በርካቶች ከበዓሉ በፊት በቁጥጥር ስር እንደዋሉ ተናግረዋል። ቢቢሲ በበኩሉ የኦሮሞ አባገዳዎች ምክር ቤትን ዋቢ አድርጎ በኢሬቻ በዓል ላይ ባልተለመደ መልኩ የትኛውም የመንግሥት አካል ድርሻ አንደማይኖረው አስታውቋል። የቢቢሲን ዘገባ ተከትሎ ደግሞ በርካታ የኢንተርኔት የዜና አውታሮች መረጃውን አሰራጭተዋል።

በዘንድሮው የኢሬቻ በዓል ላይ የታጠቀ የመንግሥት ኃይል እና ባለስልጣናት መንግሥትን ወክለው እንደማይገኙ አባገዳዎች ምክር ቢትን ጠቅሶ የዘገበው ቢቢሲ የአማርኛው ክፍል፣ አንድም የታጠቀ ሃይል፣ እንደምይገኝና ለመታሰቢያ ቆመ በተባለው ሃውልት ላይ የተጻፈው ጽሁፍ መፋቁን፣ እንዲሁም 300 የሚሆኑ ወጣቶች የስነስርዓት ማስከበሩን ስራ እንደሚሰሩ ነው የዘገበው።

ያለፈው አመት የኢሬቻ በአል ጥሎት ያለፈው ጠባሳ የማይረሳ ነው። ሙሽራዋን ነፍሰ ጡር፣ እናቶችን፣ አባቶችን፣  ወጣቶችን እና ሃገር ተረካቢ ህጻናትን የፈጀ በአል ነው። ለዚህ ደሞ ተጠያቂው ህወሃት እንደሆነ    ምስክር አያሻም  ለአለፉት 26 አመታት   ኢትዮጵያን… የጦርነትና የቀውስ፣የፍጅትና  እንዲሁም የትርምሰ ሜዳ እንድትሆንና፣  ዛሬም እንደሚታየው የሱማሌ እና የኦሮሞ ህዝብ የእርስ በእርስ ችግር ውስጥ እንዲገባ ፣በሃረር እና በቦረና፣ በሲዳማና ወላየታ፣ በቅማንት እና በአማራ በአፋር እና በኦሮሞ፣ በአማራና በአፋር ወዘተ ግጭቶች እየተነሱ በርካታ ህይወትን እየቀጠፈ ነው ።ንብረትንም እያወደመ ነው። በህዝቦች መካከል  ብሄር ብሄረሰቦች እያሉ መከፋፈሉ የተቻለውን አሰተዋጽኦ፣ጥሩ አድርጎ አበርክቶአል። …ረሃቡ፣… ድህነቱ፣ የበሽታ መስፋፋቱ፣… ስደቱ፣… ለየት ያለ አስተሳሰብ ያላቸውን ሰዎች ክትትሉና ግድያውም፣….እሥራቱም…ይህ ሁሉ በዜጎች ላይ እየተባባሰ ቀጥሏል።ይህ ሁሉ  ደሞ የሆነው  ከሌላ ነገር ሳይሆን፣ ከስልጣን ጥማት እና ፣  ከጎጠኝነት አጀንዳም የመነጨ  ነው። ኢትዮጵያ  ሐብቱዋንም፣አቅሟንም ፣ክብርዋንም፣ አንድነትዋንም፣ዜጎችዋንም  ያጣችውና፣ ወላጆችም ልጆቻቸውን ያጡት ልጆችም ወላጆቻቸውን ያጡት በዚሁ አገዛዝ ነው ይህ ሊያቆም የሚችለው ደሞ ኢትዮጵያውያን በአንድነት ስንቆም እና ከፋፋዪን ባንድነት ስንታገለው ብቻ ነው በኢ ሬቻ ህይወታቸውን ላጡ ሁሉ ነብሳቸውን ይማረው  ያጡት፣

ሰፊው የኢትዮጵያ ህዝብ ያሸንፋል

 

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s