ሬዲዮ ዘመራ

ቻይና የሰሜን ኮሪያን ኩባንያዎች ልትዘጋ ነው 

ሰሜን ኮሪያImage copyright Getty Images  አጭር የምስል መግለጫ ሰሜን ኮሪያ በርካታ ፀረ-አሜሪካ ሰልፎችን አካሂዳለች

የተባበሩት መንግሥታት በሰሜን ኮሪያ ላይ የጣለውን ማዕቀብ ተግባራዊ ለማድረግ በግዛቷ ውስጥ የሚገኙ የሰሜን ኮሪያ ኩባንያዎችን እንደምትዘጋ ቻይና አሳወቀች።

ኩባንያዎቹ በታህሳስ ወር መጀመሪያ ላይ ይዘጋሉ። የቻይና እና የሰሜን ኮሪያ ጥምር ኩባንያዎችም ለመዘጋት ይገደዳሉ።

የፕዮንግያንግ ብቸኛ አጋር የሆነችው ቻይና፤ ከሰሜን ኮሪያ ጋር ያላትን የጨርቃ ጨርቅ ንግድ ያገደች ሲሆን የምትልከውን የነዳጅ መጠንም ቀንሳ ነበር።

ይህ ሰሜን ኮሪያ ለስድስተኛ ጊዜ ጠንካራ የኑክሊዬር ሙከራ ካከሄደች በኋላ የመጣ ውሳኔ ነው።

መስከረም 1/2010 ዓ.ም ቻይና አባል የሆነችበት የፀጥታው ጥበቃ ምክር ቤት በሰሜን ኮሪያ ላይ በሙሉ ድምፅ አዲስ ማዕቀብ መጣሉ ይታወሳል።

የቻይና የንግድ ሚኒስትር እንዳሉት ሰሜን ኮሪያ በቻይና ግዛቶች ውስጥ የሚገኙትን ኩባንያዎቿን እንድትዘጋ የ120 ቀናት ጊዜ ተስጥቷታል።

ሰሜን ኮሪያ በፖለቲካና በንግድ ዘርፍ ከተቀረው ዓለም የተነጠለች ሲሆን አብዛኛው የንግድ እንቅስቃሴዋም ከቻይና ጋር ነው።

ቻይና፤ ለጎረቤት ሃገር ሰሜን ኮሪያ ጥበቃ ታደርግላት የነበረ ቢሆንም የምታደርገውን የኑክሊዬር ሙከራ ግን አጥብቃ ትቃወማለች።

በያዝነው የፈረንጆቹቸ ዓመት ቻይና ከፕዮንግያንግ ታስገባ የነበረውን የድንጋይ ከሰል ያቆመች ሲሆን የብረት እና የባህር ውስጥ ምግብ ንግድንም አቋርጣለች።

የእርሶ መሳሪያ ሚዲያ ፕሌይ ባክን ማጫወት ኣልተቻለም።

ሰሜን ኮሪያ ለምን ኑክሊዬርን መረጠች?

በጨርቃ ጨርቅ ምርት ንግዷ ላይ ከተጣለውን ዕገዳ በተጨማሪ ሰሜን ኮሪያ በጣም የምትፈልገውን የውጪ ምንዛሪ የምታገኝባቸውን በርካታ ምንጮችን አጥታለች።

ቤይጂንግ፤ በተለያዩ ጊዜያት ቻይናን ሲያወድሱና ሲወቅሱ ከነበሩት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት በኩል በሰሜን ኮሪያ ላይ እርምጃ እንድትወስድ ግፊት ሲደረግባት ቆይቷል።

ዶናልድ ትራምፕ የሰሜን ኮሪያውን መሪ ኪም ጆንግ ኡንን ”እራስን በማጥፋት ተልዕኮ ላይ ያለው ባለሮኬቱ ሰውዬ” በማለት ግልፅ የሆነ የቃላት እሰጣገባ ውስጥ ገብተዋል።

የትራምፕ ‘የጥላቻ ንግግር’ ወቀሳ ቀረበበት

በተጨማሪም ትራምፕ ሲያስጠነቅቁ አሜሪካንንና ወደጆቿን ከሰሜን ኮሪያ ጥቃት ለመከላከል ከተገደዱ ”ሰሜን ኮሪያን ሙሉ ለሙሉ ከመደምሰስ” ውጪ ምርጫ አይኖርም ብለዋል።

ኪም በበኩላቸውም ትራምፕን ”እብዱ” በማለት፤ ፕሬዝዳንቱ የሰጡት አስተያየት ሰሜን ኮሪያ እራሷን ለመከላከል የምታካሂደው የኑክሊዬር ፕሮግራም ትክክል እነደሆነ እንዲያምኑ እንዳደረጋቸውና ትራምፕ ጦርነት እንደወጁባቸው ክስ አቅርበዋል።

ኪም፡ ‘እብዱ’ ትራምፕ ለንግግሩ ዋጋ ይከፍላል

ዛሬ ሃሙስ በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የቻይና የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ሉ ካንግ እንደተናገሩት ”በኮሪያ ልሳነ ምድር የሚካሄድን የትኛውንም ጦርነት እንቃወማለን።”

”ማዕቀብና ድርድር እንዲካሄድ ማበረታታት በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የቀረቡ አስፈላጊ ነገሮች ናቸው። እኛም አንደኛውን አማራጭ ችላ በማለት ለሌላኛው አፅንኦት መስጠት የለብንም” ብለዋል።

bbc amharic

Categories: ሬዲዮ ዘመራ

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s