ሬዲዮ ዘመራ

ጎንደር ዛሬም ታሪክ ሰራ!

የጎንደር ሕብረት ለኢትዮጵያ አንድነት (ልዩ ዕትም)

ወያኔ ከደደቢት በርሃ ይዞ የመጣውን የትግራይ ተስፋፊነትye gondar hibret ተግባራዊ ለማድረግ ሲል ጎንደር ላይ ቅማንትና ዐምሐራን በመለያየት እሳት አንድዶ፤ የመሬት ተሥፋፊነቱን ተግባራዊ አድርጎ ትግራይ ላይ ቁጭ ብሎ በመንፈላሰስ እድሜውን ለማራዘም ያቀደውን፤ ሕልም የጎንደር ሕዝብ አከሸፈው። ጎንደሬው ቅማንትም ዐምሐራም አንድ ነን በማለት በምክር አልሰማ ያሉትን፤በሰፌው የልዩነት ፕሮፓጋንዳ ሲያላዝኑ የከረሙትን ቀንደኛ የወያኔ ካድሬዎችን በምርጫ ካርዱ የሃፍረት ሸማ አካናንቦ አንድነቱን አረጋግጦ “አርፋችሁ ተቀመጡ” ብሎ ወደ መጡበት መልሷቸዋል። ይህን ብዙ የተደከመለትን የከፋፍለህ ግዛው የጎሳ ፖለቲካ በጎንደር ሕዝብ አፈር ድሜ ሲገባ ማየት፤ ለጎንደሬዎች፤ የአንድነትና የጀግንነት ታሪክ ምሥክር መሆኑን በማረጋገጣችን፤ ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ የአንድነት ተስፋና ኩራት ነው ብንል አናፍርበትም።
አንቅጽ 39ን መከታ በማድረግ መላው የቅማንት ማህበረሰብ ሳይወክላቸው “ወኪል ነን” ብለው ከኢትዮጵያ እስከ አሜሪካ ሲያላዝኑ የከረሙ የወያኔ ቅጥረኞች የሐፍረት ሸማ ለብሰዋል። ታዲያ ከዚህ ታሪካዊ የህዝብ ድምፀ ውሳኔ በኋላ ምን ይሉ ይሆን? መቸውም ጉደኛ ናቸውና “ምርጫችን ያከሸፉት የጎንደር ህብረት አባላት ስለሆኑ በነሱ ላይ እንዝመት” ሊሉ ይችላሉ፤የተለመደ ሙሾአቸው ነውና።

አዎ! ጎንደር ህብረት ለኢትዮጵያ አንድነት ለህዝብ አብሮነት፤ ለወንድማማችነት፤ ለነፃነት፤ ለአጠቃላይ አገራዊ ዲሞክራሲያዊ ሥራዓት የሚታገል ማህበራዊ ድርጅት ነው። ይህ ዓላማ ህያው እንዲሆን ደግሞ ቀዳሚ መሰረት እና ትኩረት ያደረገው ጎንደር ላይ ወያኔ እያደረሰ ያለውን እርኩስ ተግባር መታገል በመሆኑ የጎንደር ሕዝብ እየደረሰበት ያለውን የመከፋፈል አጥፍቶ ጠፊ አደጋ ተባብሮ እንዲከላከል ብሎም እስከ መጨረሻው ወያኔን ለማስወገድ አላማቸው አድርገው በመላ አገራችን ከሚታገሉ ሌሎች ድርጅቶች ይሁን ስብስቦች ጋር እንዲያብር በማድረጉ ላይ ሌት ተቀን ሰርቷል፤ አሁንም ለዚህ የተቀደሰ ሕዝባዊ አላማ በርትቶ ይሰራል። ለሶሻል ሚዲያ አንበሶች፤ ለዘርኛ የወያኔ ግብረ በላዎች አንዲትም ስንዝር እንኳ ከአቋዋሙ ፈቀቅ አይልም። እናም ሳትጠራጠሩ መሰረታዊ ዓላማችን ይኽው መሆኑን አረጋግጡ

ይድረስ ለቅማንት ማህበረሰብ፦ የቅማንት ማህበረሰብ በማንነቱም በነፃነቱም የማይደራደር፤ በቃል ብቻ ታሪክ እንደሚመሰክረው ወራሪ ጠላትን አሳፍሮ ወደ መጣበት የመለሰ ባለታሪክ ንፁህ ጎንደሬ/ኢትዮጵያዊ ነው። ይህን ታርክ የሰራው እንደ ጎንደሬም እንደ ኢትዮጵያዊም ሆኖ በአካባቢው በውህደት እና በጋራ ከሚኖረው የአካባቢው ሁሉም ማህበረሰቦች ጋር አብሮና ተባብሮ፤መርቶ እና አቀናብሮ መሆኑንም ለሰከንድ እንኳ የሚጠራጠር ያለ አይመሥለንም።

ዛሬ ላይ ግን፤ይህን በወርቅ የተፃፈ ታሪክህን በመነጣጠል ጥቁር ታሪክ ሊያቀልሙህ የተነሱ ከአብራክህ የወጡ በወያኔ የዘረኝነት ማደንዘዢያ መርፊ የተወጉ ልጆችህ እንደ ጎንደሬ በሁሉም አካባቢዎች ሰርተህ በባለቤትነት መኖር እንጅ፤ እንደ እንሰሳ በአጥር ውስጥ መቀመጥ ፍላጎትህ አለመሆኑን በነፃነት እንዳትናገር ቀን በፍጥጫ፤ ለሌት በፍራቻ አንገትክን ደፍተህ እንድትቀበላቸው ያላደርጉብህ በደል አልነበረም። ይሁን እንጅ ትናንት በ12 ወረዳዎች ላይ የራስክን ድምጽ ውሳኔ እንድታሰማ ባጋጠመህ እድል የእውነተኛ ፍላጎትህ ከሌሎች አብረውህ በውህደት ከሚኖሩ ማህበረሰቦች ጋር መሆኑን አረጋግጠሃል። ይህ ውጤት በሌሎች ድምፅ ባልሰጠህባቸው ወረዳዎች የህዝብ ውሳኔ እድሉ ቢያጋጥምህ ኖሮ የምትሰጣቸው ምላሽ ተመሳሳይ ሊሆን ይችል እንደነበር ሊርዱልህ ይገባል። በእርግጠኝነት ይህ በ12 ወረዳዎች የታየው የህዝበ ውሳኔ ውጤት በሌሎች 42 የቅማንት ቀበሌዎች ጭምር ታሪካዊ ፍላጎት መግለጫ ነው። ይህን ኃይልህን እያዩ አሁንም ተስፋ ሳይቆርጡ በስልጣንና በገንዘብ ለተገዙ ካድሬዎች በሚመጣብህ ቀጣይ ተፅኖ ጭራሽ እንዳትንበረከክ አደራ እንላለን።

የትግራይ ሙሁራን ሆይ! ወያኔ በመላ የኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ እየወሰደ ያለው ፀረ-ህዝብ እርምጃ ሁሉ በትርግራይ ሕዝብ ስም እየማለና እየተገዘተ መሆኑን በግልጽ ታውቃላችሁ። ይህ ወያኔ በትግራይ ሕዝብ ስም እየወሰድ ያለው የዘር ማጥፋት እርምጃ የትግራይን ሕዝብ በመላው ኢትዮጵያዊ ዘንድ ከፍተኛ ጥላቸው ውስጥ እያስገባው መሆኑን በእርግጠኝነት እየተከሰቱ ካሉት ማህበረሰባዊ ምላሾች አኳያ ታውቃላችሁ ብለን እንገምታለን። ማንም ኃያላን በጉልበታቸው ዘለዓለም እንዳልኖሩ ሁሉ፤ የወያኔ ፀሐይም እያሽቆለቆለች መጥታለች። ሆኖም ይህን ሃቅ ላለመቀበል በግትርነት ወያኔ እያደረሰ ያለውን ታሪካዊ በደል በዝምታ በመመልከትም ይሁን የጥቅም ተካፋይ በመሆን በትግራይ ሕዝብ ላይ ሊደርስ የሚችለውን የወደፊት ግፍና መከራ ተባባሪ እንደሆናችሁ እያየን ነው። ይህ ትልቅ በደል ለወደፊት ከባድ ዋጋ እንደሚያስከፍል ከወዲሁ አውቃችሁ በእናንተ እየማለ በጥፋት ማዕበል እየተገፋ ያለውን ወያኔን በመቃወም “ሕዝባችን ለቀቅ አድርግ” ማለት ነበርባችሁ። ነገር ግን አይናችሁን በሻሽ ሸፍናችሁ በጥቅም ህሊናችሁን ሸጣችኋል። ምሁር ማለት ለህዝብና ለሐገር መቆም እንጅ፤ እንደ እንሰሳ ሆንድን ሞልቶ ለማደር የበደለኛ ተባባሪ መሆን አልነበረባችሁም። አሁንም በደሎች ተደራርበው እየመጡ ስለሆን ከፍጹም በደል ተጠያቂነት ለመዳን ንቁ! በቀሪዋ ጊዜ ወያኔን እንታገለው፤ ህዝባችን ከከፉ አደጋ እናድነው።

የትግራይ ሕዝብ ወይ! ወያኔ በሕዝብ ላይ መከራ እያወርደ፤ አገር እያፈረሰ ያለው በአንት ስም ነው። ወያኔ ማለት የትግራይ ሕዝብ ማለት አይደለም፤ አንተን አይወክልም። በትንንሽ ጥቅማ ጥቅም እያታለለ ከቀሪው ኢትዮጵያዊ ወገንህ ጋር ሆድና ጀርባ እያደረገህ ነው። ይህ መንግሥት ሲያልፍ በሌሎእች አገሮች እንዳየነው ሁሉ ግፍና መከራ በአንተ በወገናችን ላይ እንዲደርስ አንፈልግም፤ አንመኝምም። ስለዚህ ከአሁኑ “ከኢትዮጵያዊ ወገናችን ጋር አታጋጩን፤ አታቀያይሙን” ብለህ ልጆችህን ምክረ። እጅ ለጅ ተያያዘህ አደባባይ በመውጣት ተቃወም፤ ከሌሎች ወገኖችህ ጋር ትግሉን አፋፍም። የወያኔ እድመሜ ከአስራ አንደኛው ሰዓት ላይ ደርሷልና።

የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ! ዛሬ በጎንደር፤ በሐርር፤በደቡብ፤ በጎጃም እና በተላያዩ አካባቢዎች በግፍ የሚፈሰውን የሰው ልጅ ደም እየሰማህና እያየህ ከያንዳንድህ ቤት እስከሚደርስ መጠበቅ እጅግ ስህተት ነው፤ ይህንም ማድረግ ፈጽሞ የለብሕም። በህብረት ተነስተህ ከሚሞተው ወገንህ ጎን በመቆም የጨፍጫፊውን ጊዜ ማሳጠር የግድ የሚለህ ወቅት ላይ መሆንህን ተረድተህ፤ ትግልህንም በመላ ኢትዮጵያ ታቀጣጥል ዘንድ ጥሪያችን እናስተላልፋለን።

በመጨረሻም የጎንደር ህዝብ ሆይ! ወያኔ ሰሞኑን የጎንደርን ሕዝብ አከርካሪ ለመስበር ቅማንት እና አማራን ነጣጥሎ ለማዋጋት የጎነጎነው ተንኮል በ12 የምርጫ ቀበሌዎች በዝረራ ቢከሽፍም እንደገና በሌላ መንገድ ሊመጣብህ እየተዘጋጀ ነው። ለቅማንቱ ማህበረሰብም 42 ቀበሌዎችን ይዛችሁ ተከለሉ፤ እንደ ከብትም ተዘጉ የሚለው አባዜ እየመጣብህ ነው። ትናንት እንዳደረከው ሁሉ ዛሬም “አንድ ነን አንለያይም፤ ሁላችንም ጎንደሬዎች ነን” ማለት አለብህ። የወያኔን መንግሥት በአንድነት ቁመን ከሥልጣን ማሰወገድ ብቻ ነው ስላምና መረጋጋት፤ ማንነትም ይሁን ዲሞክራሲያዊ መብት ሊከበር የሚችለው። በመነጣጠል፤ኃይልን በመክፈል ለወያኔ የከፋ በደል ከመጋለጥ ውጭ ፈጽሞ ጥቅም የለውም።

ጎንደር አንገትና ማትብ ሆነህ አንድነትክን አሳይ!

ድል ለሰፊው ሕዝባችን

የጎንደር ሕብረት ለኢትዮጵያ አንድነት

Categories: ሬዲዮ ዘመራ

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s