ሬዲዮ ዘመራ

“አሜሪካ ራሷን ወይንም አጋሮቿን ለመከላከል ከተገደደች ሰሜን ኮሪያን ሙሉ ለሙሉ ከማጥፋት ውጭ አማራጭ የላትም”

የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕየአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ Image copyrightEPA

ዶናልድ ትራምፕ ለመጀመሪያ ጊዜ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተገኝተው ያደረጉት ንግግር ከተለያዩ ሃገራት ትችት ገጥሞታል። በተለይ የትራምፕ ትችት የደረሰባቸው ሃገራት የፕሬዝዳንቱን ንግግር ተገቢ ያልሆነ ሲሉ ወቀሳ አቅርበዋል።
ዶናልድ ትራምፕ ኢራንን “አነስተኛ ቁጥር ካላቸው በጥባጭ ሃገራት አንዷ” ሲሏት፤ አሜሪካ ተገዳ ወደ ጦርነት ከገባች ሰሜን ኮሪያን “ሙሉ ለሙሉ ታጠፋለች” ብለዋል።
የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚንስትር የትራምፕ የማንአለበኝነት ንግግር ኋላ ቀር በሆነው ዘመን የሚደረግ እንጂ በተባበሩት መንግስታት መሆን እንደሌለበት ጠቁመዋል። ለዜጎቻቸው ህይወት መሻሻል የሚጥሩ ሉዓላዊ ሃገራትን በመፍጠር ዙሪያ ያተኩራል በተባለው ንግግራቸው ትራምፕ አብዛኛውን ጊዜ ዓለም አሁን ላለችበት ችግር መንገድ ከፍተዋል ባሏቸው “በጥባጭ ሃገራት” ዙሪያ ትኩረት አድርገዋል።
አሜሪካ ከተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤት ውሳኔ በተቃራኒ የሚሳኤል ሙከራ የምታደርገውን ሰሜን ኮሪያ ስታስጠነቅቅ ቆይታለች። “የሚሳኤሉ ሰው ራሱን በማጥፋት ተልዕኮ ላይ ነው” ሲሉ ትራምፕ የሰሜን ኮሪያውን መሪ ኪም ጆንግ ኡንን ተችተዋል። “አሜሪካ ራሷን ወይንም አጋሮቿን ለመከላከል ከተገደደች ሰሜን ኮሪያን ሙሉ ለሙሉ ከማጥፋት ውጭ አማራጭ የላትም” ብለዋል።

trump_reaction.jpg
እስራኤል፣ ሶሪያ፣ ኢራንና ሳዑዲ አረቢያ ተወካዮች የትራምፕን ንግግር ሲሰሙImage copyrightUN / EVN
አጭር የምስል መግለጫ
የእስራኤል፣ ሶሪያ፣ ኢራንና ሳዑዲ አረቢያ ተወካዮች የትራምፕን ንግግር ሲሰሙ
አንድ የስብሰባው ተሳታፊ ፊቱን በእጆቹ ሸፍኖ በማጉረምረም ምላሽ ሰጠ ሲል ሬውተርስ ዘግቧል። የስዊዲን ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ማርጎት ዋልስቶርም “ተገቢ ላልሆነ ተሳታፊ፥ ተገቢ ባልሆነ ጊዜ የተደረገ ተገቢ ያልሆነ ንግግር” ሲሉ ለቢቢሲ አስረድተዋል። ኢራን “በዴሞክራሲ ሽፋን በሙስና የተጨማለቀች አምባገነን” ነች ካሉ በኋላ “የብጥብጥ፥ ደም መፋሰስ እና የረብሻ ዋና መሠረት ናት” ሲሉ ትራምፕ ተናግረዋል።
ትራምፕ በንግግራቸው “የሶሻሊዝም አምባገነን” ናት ያሏትን ቬንዙዌላን እርምጃ ሊወስዱባት እንደሚችሉ አስጠንቅቀዋል። ቬንዙዌላ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሆርጌ አሪዬዛ “ማስፈራሪያ” ያሉትን ንግግር አጣጥለዋል። “ትራምፕ የዓለም ፕሬዝዳንት አይደለም። የራሱን መንግስት አንኳን ማስተዳደር አቅቶታል” ሲሉ የቬንዙዌላ የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ገልጸዋል።

credit  – https://www.bbc.com/amharic/news-41330382

Categories: ሬዲዮ ዘመራ

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s