ማህበራዊ

“ የአስተርጉዋሚ ያለህ“

ወገኖች ሁላችን በተናጠል በየቦታው የምንጮኸው ጩኸት ለተወሰነ ጊዜ አስጨብጭቦልን ወይም አስጨብጭቦብን ያበቃና: ወረተኝነት ስለሚያጠቃን ሌላ በአዲስ ቃና የሚጮህ ጩዋሂ ብቅ እስኪል ድረስ የቀደመውን ጩኽት እንረሳዋለን: አዲሱ ጩዋሂ ሰው ምንም እንኩዋን ብዙ ባይቀይረውም የቀደመውን ጩኸት በልዩ ቅኔ ስላስጮኽው ብቻ ጆሮ እንሰጠዋለን!
ለእኔ እንደሚመስለኝ በአሁኑ ወቅት እጅግ በጣም የሚያስፈልገን
“ ጩሃዊ ሳይሆን አስረተርጉዋሚ :ድልድይ ሰሪና ሰባራውን ጠጋኝ “ ነው::“
ምክንያቱም የምንጣላው በምናባችን ውስጥ ባለችና ለአለም አቀፍ ዲፕሎማሲያዊ ፍጆታ ሲባል ጉዳይ የምታስፈፅምና የምትፈራረም ኢትዮጵያ እንጂ እንጂ ለትውልድ ጥላ ከለላ የሆነች ኢትዮጵያ የለችም::
ስለዚህ
1. በአገር ውስጥም በውጭም ላለው ሕዝብ አስተርጉዋሚ ያስፈልጋል!
2. ደጋፊ ነኝ በሚለውና ተቃዋሚ ነኝ በሚለው መሐል አስተርጉዋሚ ያስፈልጋል!
3. በ ተቃዋሚና በተቃዋሚ ተብዬዎች መሐል አስተርጉዋሚ ያስፈልጋል!
4- ኢትዮጵያ እንደ አገር ትቀጥል ወይም አትቀጥል በሚሉት መሐል አስተርጉዋሚ ያስፈልጋል!
5.በምሑር ነኝ ባዩና በአገር ወዳዱ መሐል አስተርጉዋሚ ያስፈልጋል!
6. ወያኔ በትውልድ ላይ ያደረሰው ታሪክ የማይዘነጋው በደል ሁሉ እንዳለ ሆኖ: ነገር ሁሉን ሁሉ በወያኔ ላይ ማሳበቡና መራገሙ ብቻ ሳይሆን: አያገባኝም ብሎ እጁን አጣጥፎ የተቀመጠው ሁሉ ተጠያቂ ስለሆነ አስተርጉዋሚ ያስፈልጋል::
7. በመጨረሻም ምንም አይነት የፖለቲካ ስልጣን የማይፈልጉ: ታናሹንም ታላቁንም የሚያጠፋውን የሚገስፁ: አድርባይ ያልሆኑ: ትውልድን ለማቀራረብና ለማስታረቅ የሚችሉ: የመንግስትንም የተቃዋሚ ድርጅቶች ጉዳይ አሰፈፃሚ ያልሆኑ“ በድብቅ ሳይሆን በግልፅ የሚሰሩ አዛውንትና ሽማግሌዎች “ አስመሳይ ያልሆኑ የሐይማኖት ድርጅት ጉዳይ አስፈፃሚዎች“ በጣም ያስፈልገናል: :
“ ምን ሴት ብታውቅ በወንድ ያልቅ“ እየተባለ የሴቶችን ሐሳብ ከመናቅ ወይም ከመስረቅ: እናቶች በቤተሰብ እንኩዋን ፀብ ሲነሳ አስታራቂዎች ናቸውና እናቶችና ሴቶችን የሚንቅ መንፈስ መፈወስ አለበት:
ስለዚህ ይህን መልዕክቴን ስለ አገር መልካም ለሚመኝ ሁሉ አድርሱልኝ:: አደራ! አደራ!
“የአስተርጉዋሚ ያለህ“
የትውልድ እናት
ሰዋስው

Categories: ማህበራዊ

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s