ማህበራዊ

እኮ ምን አረገች ? ሴትማ እናት ነች።

ሴትማ ነበሩ ከወንድ በላይ የቆሙ
ዝናር የታጠቁ ጠላት ያወደሙ
አጥንትም ከስክሰው ደምን የገበሩ።

ሴትስ አልነበረች የእናት ልክ የሆነች
በሆድ ተሸክማ
ወፈ ሰማይ ጀግናን አምጣ የወለደች
አሳድጋ ለፍታስ አስተምራ የዳረች
ወግ ማዕረግ ያስያዘች ?

ጠበቀች የሰው ዘር
እንዳይጠፋ ከምድር
ማነው የሚፈታ
እንቆቅልሽ ብዙ
የምዬን ውለታ?

እኮ ምን አረገች ?
ማንንስ በደለች ቁም ስቅል አሳየች?
ተንገላታ ኖራ ልጆቿንም አጥታ
ስትኖር በእዬዬ በልቅሶና ዋይታ
ሁልጊዜ ጠዋት ማታ
እኮ ምን አረገች ? ምን ጥፋትን ሰርታ ?
ትዳሯ የሚፈርስ ኑሮዋ የሚፈታ።

እናት ዓለም ጠኑ
ልጆቿ እንዲዝናኑ
ነጋ ጠባ ፀሎት ከምድር ተደፍታ
አንገቷን አጋንጣ እጆቿን ዘርግታ
ልመና አሰምታ አቅርባ ሠላምታ
የምትኖር ፀንታ ምን ሳታመነታ።

ድሎትም ፍስሃ ተድላና በረከት
እንዲወርድላቸው ለልጆቿ ምቾት
የጤና የሠላም የፍቅር ሰንሰለት
እናት እንዴት ትሙት ?
በጨካኞች ጥይት
ለምን ታልቅስ እናት ?
በክፉዎች ጥፋት።

እናትን የነካ ሴትን የደፈረ
በቁሙ ያስቀረው እያደናበረም እየተወገረ!

ለሁሉም የበደሉ ግምባር ቀደም ተጠቂ የዓለም እናቶችና ሴቶች እንዲሁም በእናቶች ላይ ለሚደርሰው በደልና ግፍ እንዲገታና እንዲቆም ዋይታና ጩኸት ለሚያሰሙ ቡድኖች ሁሉ ይሁን !

ሠሎሞን ታምሩ ዓየለ
መስከረም ፱ ቀን ፳፻፲ ዓም

Categories: ማህበራዊ

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s