ፖለቲካ

የከፍታው ዘመን እና የዘር ፖለቲካው ድምር ውጤት

የሰው ልጆች በተለያዩ  መስፈሪያዎች /መለኪያዎች /  ጊዜን ሰፍረዋል ወይም ለክተዋል።እነዚህም መስፈርያዎች ለእለታት  ለዘመናትና  ለአመታት  ምልክት ይሆኑ ዘንድ   የፀሀይንና  የጨረቃን  እንቅስቃሴ  መሰረት ያደረጉ  ሲሆኑ  እነዚህም እለት ፤ ወር  እና  አመት ናቸው። እነዚህን የተፈጥሮ ኩነቶች በመከተልም ዘመን እንቀይራለን የተለያዪ ባእላቶችንም እንደየወቅታቸው  እናከብራለን።

ባሳለፍነው ሳምንት የህወሀት አገዛዝ  የአስራ ሶስተኛውን ወር የጳጉሜን ቀናቶች የኢትዮጵያ የከፍታ ዘመን በማለት  የተለያዪ ስያሜ ሰጥቶ  ማክበሩ ይታወቃል። ይህ ሁኔታ ሁላችንንም  ያስደመመ ሆኖ እንደተለመደው ህወሃትን ትዝብት ላይ ጥሎ አልፏል። በተለያዪ መሪ ቃላት፣በማርሽ ባንድ፣ ሰንደቅ አላማን በማውለብለብ፣ እና የትራንስፖርት አገልግሎትን ለ5 ደቂቃ ያህል እንዲቆም በማድረግ እራሳቸውን ሲያታልሉ ያሳለፉበት ሳምንት ነበር።

የህወሃት አገዛዝ እንደሚለው ኢትዮጵያ የከፍታ ዘመን ላይ አይደለችም።በታሪኳ አይተው ወደማታውቀው የፖለቲካ ቀውስ ውስጥ ገብታለች።ሀገሪቱን ሸንሽነው ሽንሽነው ወደ እማያባራ ግጭት ውስጥ እየከተቷት ነው።ለዚም የሰሞኑን የሶማሊና የኦሮሚያ ክልሎችን ግጭት መጥቀስ በቂ ነው።ከ9 ሚሊዮን ህዝብ በላይ  የሚላስ የሚቀመስ በቤቱ አጥቷል።በተለይ በዚህ ሁለት ዓመት ውስጥ በሽህ የሚቆጠሩ ንጹሀን ዜጎች በአገዛዙ ወታደሮች በግፍ ተገድለዋል።በርካታ ፖለቲከኞች፣ጋዜጠኞችና ስለ ሀገራችን ጉዳይ ያገባናል ብለው ሀሳባቸውን የገለጹ ሁሉ በየ ማጎሪያ ቤቱ እየተሰቃዩ ነው።በመላ ሐገሪቱ ህዝባዊ እቢተኝነት እየተካሄደ ነው።በዚህም ቀድሞ በዝምታ ሰላም የሚመስለው የሀገሪቱ ሁኔታ አሁን የእርስ በእርስ ግጭት በተለያዩ ቦታዎች እያቆጠቆጡ ነው።ባሳለፍነው ሳምንት በአሜሪካ የተካሄደ አንድ ጥናት እንዳመለከተው ኢትዮጵያ ያልተረጋጉ ሐገራት ምድብ ውስጥ ደረጃዋ ማሽቆልቆሉን አመልክቷል። የምስራቅና የማእከላዊ አፍሪካ ሐገራት በአለም ላይ ካሉና ጥናቱ ካካተታቸው 178 ሐገራት ያልተረጋጉና ሰላም የደፈረሰባቸው ከተባሉ ሀገራት በመጀመሪያው ረድፍ ላይ ተቀምጠዋል። እንግዲህ በዚ ሁሉ ቀውስ ውስጥ ሆኖ ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ እንደሚባለው የተለያዪ ስያሜ የተሰጣቸው የጳጉሜ ቀናቶች ተክብረዋል

ያስደመሙኝ የቀናቶቹ ስያሜ ብዙ ቢሆኑም “የአንድነት ቀን” “የሀገር ፍቅር ቀን”  “የኢትዮጲያ ቀን” እና “የንባብ ቀን ነው!የሚሉት አንድነትን፣ የሀገር ፍቅርን እና ኢትዮጲያዊነትን አያንፀባርቁም።“የአንድነት ቀን”፣ “የሀገር ፍቅር” “የንባብ ቀን” እና “የኢትዮጲያ ቀን” በሚል የተዘጋጀው መርሃ ግብር የህወሃት  መንግስት የሚከተለውን የተሳሳተ የፖለቲካ አቅጣጫ በተጨማሪ በስልጣን ላይ ያለው ቡድን ያለበትን ስር የሰደደ የዕውቀት እጥረት (knowledge deficiency) በግልፅ ያሳያል።

የአንድነት ቀን

ባለፉት ሃያ ስድስት  አመታት የህወሃት አገዛዝ  “አንድነት፣ የሀገር ፍቅር ወይም ኢትዮጲያዊነት” ምንም ቢናገር፥ ቢያደርግ በብዙሃኑ ዘንድ ተዓማኒነት የለውም። የህወሃት አገዛዝ  ስለ ሀገራዊ አንድነት፣ ፍቅርና ዜግነት ቢናገር፥ ቢከራከር ተቃዋሚዎች ቀርቶ የራሱ ደጋፊዎች እንኳን በሙሉ ልብ አምነው አይቀበሉትም።ሀወሃት የእርስ በእርስ ግጭቶችን መለኮሱን አሁንም እንደቀጠለበት በሃገሪቱ ያሉት ገጽታዎች አመላካች ናቸው፡፡ህወሃት ለዘመናት ያቀደው የታላቋ ትጋራይ የበላይነት እስኪረጋገጥ ድረስ እድሜውን ለማራዘም የሚችለው ሕዝብን ከህዝብ፣ ጎሳን ከጎሳ፣ ብሔረሰብን ከብሔረሰብ፣ ሀይማኖትን ከሀይማኖት፣ ወዘተ. በማጋጨት ብቻ ነው። ለዚህም ነው ጠንክሮ የሚሰራው በጎንደር፣በኦሮምያ እና በሌሎችም የሃገሪቱ ክፍሎች ሕዝባዊ አመጹ ክንዱን አስተባብሮ በአንድነት እንዳይቆም ለማድረግ የሚዘራው የዘረኝነት ሴራ ለሁሉም የኢትዮጵያ ህዝብ ግልጽ እና ግልጽ ነው።።የዚህን ግፍና በደል ግፍ ቀማሽ የሆኑት ዜጎች ጥቂት አይባሉም ጭናክሰን እና አወዳይን፣ ኦሮሞዎችን ከሶማሌዎች ጋር፣ ጉጂዎችን ከሲዳማዎች ጋር፣ ወላይታን ከሲዳማ ጋር፣ ቅማንትን ከጎንደሮች ጋር፣ ወልቃይት ላይ ትግሬዎችን ከአማራዎች ጋር፣ ሰሜን ሸዋ ላይ አማሮችን ከአፋሮች ጋር፣ ወዘተ. በማጋጨት ፀረ-ወያኔው ሕዝባዊ አመጽ በወያኔ ላይ ተባብሮ መቆም አንዳይችል በከፋፍለህ ግዛ የጨቋኞች ይትበሀል ሕዝብን እርስ በእርስ እያጋጨና ደም እያቃባ ያለው አገዛዝ በአደባባይ የአንድነት ቀን ብሎ ማክበሩ ለኢትዮጵያ ህዝብ ያለውን ንቀት ያሳያል ፡፡

የሀገር ፍቅር ቀን

የሃገር ፍቅር ቀንም ከዚ በተለየ መልኩ አይታይም የሃገር ፍቅር ማለት የህዝብ ፍቅር ማለት ነው። ህዝብን ያልወደደ መንግስት እንዴት ሃገሬን እወዳለሁ ሊል ይችላል የሃገር ፍቅር ማለት የህዝብ ፍቅር ነው በልብ ውስጥ እንደማህተም ታትሞ የሚኖር ህያው ስሜት ነው!! የሃገር ፍቅር ሲባል ለሃገር የህይወት መስዋእትነትን እስከመክፈል ድረስ ነው። አባቶቻችን ሃገራቸውን ከመውደዳቸው የተነሳ ብዙ መስዋእትነትን ከፍለዋል።  የዴሞክራሲና የሰላም፣ የፍትህና የእኩልነት ዋስትና በሌለባት በዜጎች መካከል መግባባት እንዳይፈጠር ተገተው በሚሰሩባት ፣ ዜጎች ለመኖራቸው ዋስትና በሌለበት፣ ድህነትና ኋላቀርነት በተንሰራፋበት፣ድንበር ተቆርሶ በሚሰጥበት፣ዜጎች ከቀዪያቸው እየተፈናቀሉ መሬት ለባእዳን በሚቸበቸብበት  የአገር አንድነትን በማፈራረስ ላይ በሚሰራበት የአንድነት ቀንን ማክበር ታላቅ ፊዝ ነው።

 የንባብ ቀን

ማንበብ በሚያሳስርባት ኢትዮጵያ ቀኑ “የንባብ ቀን ነው! ተብሎ ተከብሯል የከፍታ ዘመን እያሉ መቶ በመቶ በተቆጣጠሩት ሚዲያ ህዝቡን ሲያደነቍሩት የከረሙት ህወሃቶች የነሱን መደንቆር አላስተዋሉትም  አንድ ሰው ሲደነቁር ህመሙ ለተደነቆረበት ሰው ነው እንጂ ለደነቆረው ሰው አይታወቀውም።

ዛሬስ በከፍታው ዘመን በ2010 በጋምቤላ በአንድ ጀንበር አምስት መቶ የሚደርሱ የአኝዋክ ልጆች ተሰየፉ፣ ተጨፈጨፉ፤ በቢኒሻንጉል በተመሳሳይና በተደጋጋሚ አማራዎች ተገደሉ፣ በበደኖ ገደል ውስጥ ተጣሉ በአርሲ፣ በወተር፣ በቆቦና በደደር እንዲሁም በዋተርና በሞያሌና አካባቢው ላይ ጭፍጨፋ ተካሂዷል። ደቡብ ክልልም የተለያዩ ቦታዎች እልቂት ተፈጽሟል፣ የሰው ልጆች ተጨፈጨፉ፣ የሚጠየቅ የለም።አሁን አሁን ጭፍጨፋ በአዋጅ ሁሉ ፈቃድ እየተሰጠው ንጹሃን እየተፈጁ ነው። የት ነው ማቆሚያው? እየባሰ እንጂ እየላላ የሚሄድ ነገር አይታይም። የፈለገው ክልል ተነስቶ ያፈናቅላል። የፈለገው ክልል ተነስቶ ድንበሩን ያሰፋል። የፈለገው ክልል ተነስቶ እንደ አገር ከሌላ አገር ጋር ስምምነት ያደርጋል፤ የፈለገ ክልል ተነስቶ ማንነትን በጥይትና በሃይል ያስቀይራል። የፈለገ ክልል ታሪክ እየገለበጠ ወደ ራሱ ይወስዳል። የፈለገ ክልል ያስራል፣ ይፈታል፤ ብዙ ብዙ የተወገዙ ድርጊቶች ይፈጸማሉ … ወዘተ አሁን የሚያሳስበው የነገው ነው። ለምን? ቢባል እየባሰ እንጂ እየለዘበ የሚሄድ ነገር አልታየም!!እልቂቱ ማቆምያ አጣ ዜጎች በኢትዮጵያ መኖር ስቃይ ሆነባቸው የከፍታው ዘመን በዘር ፖለቲካው ድምር ውጤቱን እያባዛው ነው

 

Categories: ፖለቲካ

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s