ሬዲዮ ዘመራ

የቡርማ ሙስሊሞች ጉዳይ በዶ/ር ኡመር አ/ካፊ

21317694_1500412386691220_3796637244053598276_nከጊዜህ ላይ 90 ሴኮንድ ወስደህ ስለ ቡርማ ሙስሊሞችን ችግር ብታውቅ ምን ይመስልሃል?
ታሪኩ ባጭሩ ይህን ይመስላል!
3,000,000 ሙስሊሞች የሚኖሩባት አራካን የተሰኘች አንዲት ሃገር ነበረች። ከዚች ሃገር ጎረቤት በሆነችው ቡርማ የአራካን ሙስሊሞች በሚያደርጉት ዳዕዋ ምክንያት እስልምና አየተስፋፋ ሄደ። ቡርማ ውስጥ አብዛሃኛው ማህበረሰብ የቡድሃ እምነት ተከታይ ነው። በ1784 /ማለትም ከዛሬ 230 አመታት በፊት/የቡርማ ቡድሂስቶች በአራካን ሙስሊሞች ላይ ባሳደሩት ቂም ምክንያት ወረራ በመፈፀም ብዙ ሙስሊሞችን ገደሉ። አራካንንም ወደ ቡርማ በማስገባት መጠሪያዋን ሚንማር የሚል ስም አደረጉ። ሙስሊሞች አነስተኛውን ቁጥር የሚይዙ ሲሆን ብዛታቸው ከ 3 ― 4 ሚሊዮን ይደርሳል።

በአንፃሩ ደግሞ ቡድሂስቶች 50,000,000 ይሆናሉ። 
ሙስሊሞች የራሳቸውን መንደር በማበጀት የንግድ ልውውጦች እና የራሳቸውን ማህበራዊ ህይወት መምራት ጀመሩ። በዚቹ መንደር ውስጥ የተለያዩ ማህበራት ያሉ ሲሆን መሳጂዶችንና ዱኣቶችን ይደጉማሉ።

አሁንም የቡርማ ቡድሂስቶች ወደ ሙስሊሞች መንደር በመዝመት ከሃገር ለማስወጣት እንቅስቃሴ ጀመሩ። ብዙም ሳይቆይ አሰቃቂ የሆነ ግድያ (እርድ) ፈፀሙ። ይህም የሆነው በሙስሊሞች አካባቢ በመዘዋወር ሰዎችን የሚያስተምሩ ፣ ኒካህ የሚያስሩ ፣ ቁርኣን የሚያስቀሩ ወደ አስር የሚጠጉ ሃፊዞችንና ዳኢዎችን በመያዝ ብርቱ የሆነ ድብደባ ፈፀሙባቸው።

ይህም አልበቃ ብሏቸው ሰውነታቸውን በሳንጃ ተጫወቱበት። እንደውም ያንደኛውን ምላስ በገመድ ካሰሩ በኋላ ያለምንም ርህራሄ ጎለጎሉት። ከዚያም ሁሉንም ተራ በተራ እግር እና እጃቸውን በመቆራረጥ ገደሏቸው። ይሄን ሁሉ ግፍ የሚፈፅሙት ለ ኢስላምና ሙስሊሞች ካላቸው ጥብቅ ጥላቻ የተነሳ ነው።

ሙስሊሞችም ከኢማሞቻቸው፣ ከኸጢቦቻቸው እና ከዱኣቶቻቸው ለመከላከል እንቅስቃሴ አደረጉ። ቡድሂስቶችም በአፀፋው የሙስሊሞችን መንደር በእሳት አያያዙት። በእሳት አደጋው የተቃጠሉ ቤቶች ቁጥር ወደ 2600 ገደማ ደርሷል። በዚህም ቃጠሎ ምክንያት የሞተው ሞቶ የሸሸውም ሸሸ። ወደ 90,000 የሚደርሱ ሙስሊሞች በየብስም በባህርም ወደ ሌሎች አገሮች ተሰደዱ።

መታረዱም ይሁን መገደሉ አሁንም ድረስ እንደቀጠለ ነው። ሚስቶቻቸው፣ እህቶቻቸው፣ ልጆቻቸው… አይናቸው እያየ የአስገድዶ መደፈር ወንጀል ተፈፅሞባቸዋል።

እየተፈፀመባቸው ካለው አስቃቂ እና ማብቂያከሌለው ግፍ ውስጥ ይሄ ጥቂቱ ነው። ለዲናችን ያለን ተቆርቋሪነት ለምን ጠፋ??? 
ሁላችንም ለነሱ ምን ማድረግ እንዳለብን እራሳችንን እንጠይቅ።

ለጊዜው ቀጣዮችን ነገሮች ማድረግ ይኖርብናል
1 ዱኣእ
2 ጉዳያቸው እንዲታወቅ ማድረግ
ይህንን አንብበህ ስትጨርስ ለሌሎች አስተላለፍ!! 
አላህ በቂያችን ነው።ምን ያማረ መመኪያ!! 

Categories: ሬዲዮ ዘመራ

Tagged as:

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s