ዜና

75 ህገ-ወጥ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በማላዊ መታሰራቸው ታወቀ

75 ኢትዮጵያዊያንና አንድ ቡሩንዲያዊ ስደተኞች በአምስት ማላዊያን አሽከርካሪዎች በመታገዝ በህገ-ወጥ መንገድ ወደ ማላዊ  ሲገቡ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የማላዊ የኢምግሬሽን መምሪያ ሀላፊ አርብ ዕለት አስታወቀ።

   የማላዊ ሰሜናዊ ግዛት የኢሚግሬሽን የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆኑት ብላክዌል ሉንሱ በበኩላቸው 76ቱ ህገ-ወጥ ስደተኞች በሦስት ሚኒባሶች ተጭነው ሲጓዙ በቺዊታ ተራራ አካባቢ መያዛቸውን ገልጸዋል። የማላዊ መንግስት ህገ-ወጥ ስደተኞች በሀገሪቱ ላይ የሚያስከትሉትን ተፅዕኖ የግንዛቤ ማስጨበጫ ዘመቻዎች በሚያደርግበት በአሁኑ ሰዓት አሽከርካሪዎቹ  እንዲህ አይነቱን ህገ-ወጥ ተግባር መፈጸማቸው አስገራሚ ነው ብለዋል።ስደተኞቹ  ለተለያዩ ወንጀሎችንና በኢቦላ በተጠቁ ሀገራት ሲያልፉ በሽታውን ለማስፋፋት በር ይከፍታል በማለት ሀላፊው አብራርተዋል።

 ስደተኞቹ  ሁሉም ወንዶች ሲሆኑ ሙዙዙ በተባለ እስር ቤት እንደሚገኙም ታውቋል። ዛሬ ነሃሴ 30 2009 ሰኞ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል።

*****

Categories: ዜና, Uncategorized

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s