ዜና

የሰሜን ጎንደር ለሶስት መከፈል ህዝባዊ አመጹን ያጠነክረዋል እንጂ አያቀዘቅዘውም

ጎንደር በሦስት ዞኖች መከፋፈሉዋ የጎንደርን ህዝብ አስቆጥትዋል በዚህ በአዲሱ የሰሜን ጎንደር ክፍፍል በለምነታቸው የሚታወቁት ማይፀምሪ፣ ወልቃይትና ሁመራ አለመካተታቸው እየተካሄደ ያለው ሕዝባዊ አመጽ ላይ ነዳጅ እንደማርከፍከፍ ይቆጠራል ተብሏል፡፡ ይህ የወያኔ መሰሪ ክፍፍል መሀል ጎንደር፣ ሰሜን ጎንደር፣ ምዕራብ ጎንደር በሚሉ የተከፋፈለ መሆኑ ተነግሯል፡፡ በዚህ መሰረት መሀል ጎንደር፣ ከተማው ጎንደር ሲሆን የሚያካትታቸው- ጎንደር ዙሪያ፣ ምዕራብ በለሳ፣ ምስራቅ በለሳ፣ ወገራ፣ ጠገዴ፣ ታች አርማ ጨሆ፣ ማሰሮ፣ አለፋ፣ ጣቁሳ፣ ምዕራብና ምስራቅ ደምቢያን ነው፡፡ ሁለተኛው ሰሜን ጎንደር የተባለ ሲሆን ከተማው ደባርቅ፣ በስሩ የሚገኙት ዳባት፣ ደባርቅ፣ ጃን አሞራ፣ በየዳ፣ አደርቃይ፣ ጠለምት መሆናቸው ታውቋል፡፡  ሦስተኛው ምዕራብ ጎንደር ሲሆን ከተማው ገንዳ ውሀ፣ የሚያካትታቸው መተማ፣ ቋራ፣ ምዕራብ አርማጨሆ፣ መተማ ዮሀንስና ምድረ-ገነት ናቸው፡፡ ይህ ሰሜን ጎንደርን የመሰነጣጠቅ ዘመቻ ዋናው ሰበቡ አምና በተከሰተው አርድ አንቀጥቅጥ ሕዝባዊ አመጽ ሳቢያ እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡ ይህ ክፍፍል ውሎ አድሮ የጎንደርን ሕዝብ እርስ በእርስ እንዲጋጭ ለማድረግና የተዘረፉት፣ ተቆርጠው የተወሰዱት የጎንደር አካላት የሆኑትን ሁመራን፣ ወልቃይትን፣ ማይፀምሪን ለማስመለስ የሚደረገውን ሕዝባዊ አመጽ ለማሽመድመድ የታለመ ደባ ነው ፡፡ ይህ ሁኔታ በአሁኑ ሰዐት እየተካሄደ ያለውን በጎዝ አለቆች የሚመራውን የጎንደር ሕዝብ ሕዝባዊ አመጽን ያጠነክረዋል ተብሏል፡፡

Categories: ዜና, Uncategorized

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s