ዜና

ባለፈው ሳምንት ለኢትዮጵያ መንግስት ተላልፈው የተሰጡት የኦጋዴን ነፃነት ግንባር የአመራር አባል ውዝግብ አስነሱ

ባለፈው ሳምንት የኢትዮጵያ መንግስት የኦጋዴን ነፃነት ግንባር አመራር አባል አብዲ ከሪም ሼክ ሙሳ ከሶማሊያ ጋልማዱግ ግዛት አፍኖ ወደ ኢትዮጵያ መመለሱን ግንባሩ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።የሶማሊያ መንግስት አብዲ ከሪምን አሳልፎ በመስጠቱ የነፃነት ግንባሩ ማዘኑን ገልፆ የሶማሊያ መንግስት ተጠያቂ መሆን አለበት ብሏል። በሌላ በኩል አሶሼትድ ፕረስ አሙስ እለት እንደዘገበው “የሶማሊያ መንግስት ህገ-መንግስቱን በመጣስ ዜጋውን አሳልፎ ለሌላ ሀገር ሰጥቷል” በማለት ሶማሊያዊያን ቁጣቸውን እየገለጹ ነው።የሶማሊያ የህግ ባለሙያ የሆኑት ዘካሪያ ሐጂ መሀመድ መንግስት ለዜጋው ጥበቃ ከማድረግ ይልቅ ለምን ለጠላት አሳልፎ እንደሰጠ ለህዝቡ ማብራሪያ እንዲሰጥ ጠይቀዋል።የሶማሊያ መንግስት እስካሁን ያለው ነገር ባይኖርም የሀገሪቱ የደህንነት ቢሮ ጉዳዩን በሚስጥር መያዝ ያስፈልጋል ብሏል።

የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አብዲ ከሪም ዜግነቱ ኢትዮጵያዊ መሆኑን ገልጾ፤ ሶማሊያ በቆየበት ጊዜም የኢትዮጵያን የጉዞ ሰነድ ይጠቀም ነበር ብሏል።ሶማሊያ ውስጥ በመሸሸግ በፀረ-ሠላም ተግባር ላይ ተሰማርቶ የነበረው አብዱልከሪም በፍላጎቱ ወደ ሀገሩ የተመለሰው የሶማሊያ መንግስት ሁኔታዎችን  በማመቻቸቱ  ነው ሲልም ሚኒስቴሩ ገልጿል።

የሀወሃት ቡድን አብዲ ከሪም በፍላጎቱ ነው ወደ ሀገሩ የተመለሰው ቢልም  እጆቹ በካቴና ታስረው በወታደር ሲጠበቅ የሚያሳይ ምስል በሶሻል ሚዲያ በስፋት ተለቋል።

Categories: ዜና, Uncategorized

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s