ዜና

በጣና ሐይቅ ላይ የተከስተውን እምቦጭ የተሰኘ አደገኛ አረም ለማስወገድ ዘመቻው ቀጥሏል

በጣና ሐይቅ ላይ የተከሰተው እንቦጭ የተሰኘ አደገኛ አረም ለማስወገድ ህዝባዊ ዘመቻ ተጀመረ። የክልሉ አንዳንድ መስሪያ ቤቶች፤ የባህር ዳር ከተማ ነዋሪዎችና የሐይቁ ተፋሰስ አካባቢ ነዋሪዎች በመቀናጀት አረሙን በእጅ የመንቀል ተግባር እያከናወኑ ነው። አረሙን ለማስወገድ የሚያስችል መሽን በሀገር ውስጥ ተሰርቶ በሙከራ ላይ መሆኑም ተገልጿል። ከሸዋ፣ወሎ፣ጎንደርና ከተለያዩ አካባቢዎች ሀገር ወዳድ ወጣቶች ጣናን ለመታደግ የበኩላቸውን ጥረት እያደረጉ ነው።

የክልሉ ደንና የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን የሆኑት ዶክተር በላይነህ እንዳሉት ጣና የአማራ ክልል ብቻ ሳይሆን የመላው ኢትዮጵያ ህዝብ ውድ ሀብት በመሆኑ የፌዴራል መንግስትም ድጋፍ እንዲያደርግ ጠይቀዋል።ጣና ላይ የተከሰተውን የእንቦጭ አረም በጋራ ተረባርበን ካላጠፋነው ለአባይ ግድብም ከፍተኛ ስጋት ነው ሲሉ ገልጸዋል።አረሙን የማስወገድ ዘመቻው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የባህር ዳር ከተማ አስተዳድር ገልጾ፤ እስካሁንም ስፋቱ 25 ሄክታር የሚሆን በእንቦጭ የተሸፈነ መሬት ማስወገድ እንደተቻለ ተጠቅሷል።

Categories: ዜና, Uncategorized

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s