ዜና

በምስራቅ ሐረርጌ በኦሮሞና ሶማሌ ልዩ ሀይል ፖሊስ መካከል የተቀሰቀሰው ግጭት እየተባባሰ መሆኑ ተገለጸ

በምስራቅ ኢትዮጵያ በመኢሶን ከተማ አቅራቢያ ከፍተኛ ጦርነት እየተካሄደ እንደሚገኝ ተገለጸ።በኢትዮጵያ ሶማሌና በኦሮሞ ጎሳዎች መካከል በወሰን ምክንያት የተቀሰቀሰው ግጭት ለወራት መዝለቁ የሚታወቅ ሲሆን ባሳለፍነው ሳምንት በርካታ የአካባቢው ነዋሪዎችን ያሳተፈ ጦርነት መካሄዱን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል።የሶማሌ ጎሳዎች ልዩ ፖሊስ እየተባሉ በሚጠሩት ወታደሮች መደገፋቸውን መረጃዎች አመልክተዋል።የጥፋት ሀይል በሆነው በልዩ ፖሊስ በግልፅ በመታገስ የሶማሌ ጎሳዎች  ወንዶችን እየገደሉ፣ሴቶችን እየደፈሩ እንዲሁም ከብቶቻችን  እየዘረፉ ነው ሲሉ የመኢሶን አካባቢ ነዋሪዎች ገልጸዋል።እስካሁን በሁለት ሳምታት ብቻ በግጭቱ ከ50 በላይ ዜጎች ህይወታቸውን ሲያጡ፤ ከ100 በላይ የሚሆኑት ለከፍተኛ ጉዳት መዳረጋቸውን ዘገባዎች አመልክተዋል።

በኢትዮጵያ ላለፉት 26 ዓመታት የጎሳ ፌደራሊዝም ተግባራዊ ከተደረገ ወዲህ እንዲህ አይነቱ ግጭት እየተለመደ መጥቷል። ባሳለፍነው ወር  በዚሁ አካባቢ ከፍተኛ ጦርነት እየተካሄደ እንደሆነ በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ መግለጫ ሲያወጣ፤ የህወሃት ቡድን ሀሰት ማለቱ የሚታወስ ነው።

Categories: ዜና, Uncategorized

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s