ሬዲዮ ዘመራ

ሁሌ እናስታውሳቸው  ተቀብሮ እንዳይቀር አኩሪ ታሪካቸው!በመኮንን ተስፋዪ

ገነት ግርማ ማን ናት???? ባላማዋ ፀንታ እስካሁን በመታገል ላይ የምትገኝ የኢህአፓ ኮከብ!!!

የውጭ ወራሪን ለመመከትም ሆነ ለፍትህ፤ ዲሞክራሲና ለነፃነት በኢትዮጵያ ህዝብ በተደረገው ትግል ሴቶች ከወንድ ጓዶቻቸው ጎን ቆመው ያሳዩት መስዋእትነትና ጀግንነት የተሞላው ተሳትፎ በታሪክ መዝገብ ላይ ተፅፎ ሲዎሳ ይኖራል።

ጣልያንን ካንበረከከው ከአድዋ ጦርነት በኋላ በሰፊው ሴቶችን ያሳተፈው የካቲት 66 አብዮት ሴቶች በአብዮት ውስጥ ያላቸውን ሚናና ካለነሱም ተሳትፎ ግቡን እንደማይመታ በገሃድ አሳይቷል። ሴቶች ለመብታቸው የሚያደርጉት ትግል ለዲሞክራሲ ከሚደረገው ትግል ተነጥሎ ስለማይታይ እጥፍ ድርብ ጉልበት ይሰጣቸዋል፤ ወደ ትግሉ ጎራ ለመግባትም ጉልበት ይሆናቸዋል።

በኢህአፓ ስር ተደራጅተው ለህዝባዊ መንግስትና ዲሞክራሲ በግንባር ቀደምትነት ከፋሺስት ደርግ ብሎም ከዘረኛው ወያኔ ጋር ሲታገሉ የወደቁ ሴት ጓዶች ቤት ይቁጠራቸው!! ከወንድ ጓዶቻቸው ባልተናነሰ ሁኔታ በማደራጀትም ሆነ ብቁ አመራር በመስጠት በድርጅቱ ዉስጥ ተሳትፏቸውን አሳይተዋል አስመስክረዋልም።

በትግሉ ከወደቁት ሌላ አሁንም በፅናት ሙሉ ህይወታቸውን የትግሉ ነው ህይወቴ ብለው የቆሙና ላዲሱ ትውልድ አርአያ እየሆኑ ያሉት ይጠቀሳሉ !!!

የጀግናዋ ገነት ግርማ አጭር ታሪክ ይቀጥላል!!!

ገነት ግርማ ከእናትዋ ከወይዘሮ ሳሌም ፓውሎስና ከአባትዋ ከመቶ አለቃ ግርማ ወ/ጊዮርጊስ በግንቦት 1943 ዓም ተወለደች። አስተዳደጓም ያፍቃሪ ቤተሰብ ያልተለየው ስለነበር አስተዳደግና የቤተሰብ ፍቅር ወሳኝ ነውና ልበ ሰፊ ህዝብ አፍቃሪና ሓገር ወዳድ እንድትሆን አድርጓታል። ዕድሜዋ ለትምህርት እንደደረሰም የመጀመርያና ሁለተኛ ትምህርቷን በአዲስ አበባ ካጠናቀቀች በኋላ ወደ ፈረንሳይ አገር በመጓዝ የከፍተኛ ትምህርቷን ተከታትላለች።

ገነት የአፄውን ስርአት በመቃወም በተነሳው አለም አቀፍ የኢትዮጵያ ተማሪዎች እንቅስቃሴ በመሳተፍ በግንባር ቀደምትነት ታግላለች፤ የትግል ጓዶቿም እስከዛሬ የሚያስታውሱትን ፅናትና ብቃት አሳይታለች። በፈረንሳይና በአውሮፓ ያደረገችው ፅኑ ትግልም አርአያነት አለው። ተማሪዎች ባደረጓቸው የንቃት ማዳበርያ ዘመቻወች፤ የተቃውሞ ሰልፎች እንዲሁም ኤምባሲዎችን የመያዝ እርምጃወች በሰፊው የተሳተፈች ሲሆን ለኢራን፤ ለፓለስታይን ለደቡብ አፍሪካ በተደረጉ የተቃውሞ ሰልፎችና የርሃብ አድማዎች ተሳታፊ ነበረች።

ትግሏ ለኢትዮጵያ ህዝብ መብት ቢሆንም የሴቶችን ጥያቄና መብት ለማስከበር ልዩ ትኩረት በመስጠት ገነት የኢትዮጵያ አለም አቀፍ የሴቶች መብት የሚያስከብር ማህበር መስራችና ብርቱ አባል ሆና ታግላለች።

ኢህአፓም ከተመሰረተ ከአመት በኋላ ተቀላቅላና አባል ሆና በፅኑነትና በቆራጥነት ይኽው እስከዛሬ ስትታገል ቆይታለች።

ገነት የሚያውቋት ሁሉ በደግነቷና ፅናቷ፤ በቆራጥነቷና ንቃቷ፤ በግልፅነቷና አይበገሬነቷ እንዲሁም በብሩህ ተስፋዋ ያስታውሷታል። እንደኢህአፓ በፅናት የታገለችና በድርጅቱ ላይ ጥቃትና ጉዳት ቢደርስም መስመር ሳትለቅና ቃል ኪዳኗን ሳታፈርስ እስከዛሬ ኮርታ የምትገኝ እውነተኛ ታጋይ ኢህ አፓ ነች።

የኢህአፓ ሁለተኛ ጉባኤ ነፃ ባወጣው ቋራ በተካሄደ ጊዜ ከፈረንሳይ ቋራ ተጉዛ የበኩሏን ገንቢና ስኬታማ አስተዋፅኦ አድርጋለች።

በድርጅቱም የብተና አደጋ ተከስቶ በአገር ውስጥም በውጭ አገር ከባድ ጉዳት ሲደርስ ገነት ከሌሎች ጥቂት ጓዶች ጋር በመሆን የኼን የችግር ጊዜ በኢህአፓነት በፅናት ተወጥታለች። ለድርጅቱም መልሶ ግንባታ ከፍተኛ አስተዋፅኦ በማድረግ አይበገሬነቷን አስመስክራለች።

በምትችላቸው የተለያዩ ቋንቋዎች በአማርኛ እንግሊዘኛና ፈረንሳይኛ በየመድረኩ በመገኘት የኢትዮጵያን ህዝብና የኢህአፓን ትግል በአለም መድረክ አስተዋውቃለች። በሬድዮን መግለጫ ሰጥታለች፤ ድርጅቷንና ያስተማራትንም ህዝብ ወክላለች። በየአመቱ በጀነቫ በሚደረገው የስብአዊ መብት ኮሚሽን ስብሰባ በመገኘት ፋሺስቱን ደርግና አረመኔውንና ዘረኛውን ወያኔ በማጋለጥ ከፍተኛ ትግል በማድረግ አክብሮት አትርፋለች። የወያኔን ፀረ ዲሞክራሲነትና ዘረኛነትንም ከመጀመርያው ጀምሮ በተግባር ተዋግታለች፤ በአለም መድረክም አጋልጣለች። ገነት የህዝብን ጠላቶች አምርራ የታገለች ቢሆንም ቂም የማትይዝና ይቅር ባይ መሆኗም ይታወቅላታል።

ገነት የጓድ ኢያሱ አለማየሁ ባለቤትና ፀደይ የምትባል የአንዲት ሴት ልጅ እናት ናት። ገነት ጓደኞቿንና ቤተሰብዋን አፍቃሪ ብትሆንም አባቷ ፕሬዘዳንት ተብለው ቢሾሙም ባላማዋ ፀንታ የቆየችና ፀረ ወያኔ ትግሏን ላንድ አፍታም ያላቋረጠች ጓድ ናት።

ገነት ድርጅቷ በጠራት ቦታ ሁሉ መገኘት ግዴታዋ ስለነበር ለሰላምና እርቅ ጉባኤ ኢድሃቅን ወክላ ሄዳ በወያኔ ታስራ በነበረችበት ወራቶች ላንድ አፍታም ለወያኔ ሳትበገር በመቆየት ጀግንነቷን ያስመሰከረች ጓድ ናት።

የገነት ግርማ ጽኑ የአላማ ቆራጥነትና ከወጣትነት እድሜዋ ጀምሮ ለትግሉ ያደረገችው ከፍተኛ አስተዋፅኦ በተለይም የሴቶችን መብት በተመለከተ በአሁኑ ወቅት ከወያኔ ጋር በመዋደቅ ላይ ላለው ተተኪው ወጣት ትውልድ በአርአያነት የሚወሳ ነው!!!!!!!!!!!!!!!!!

የጠፉ፤ ያለፉ፤ ህይወታቸውን ለትግሉ የሰጡ፤ እየሰጡ ያሉ እንዲሁም የተሰዉ ጓዶቻችንን የማስታወስ ብሎም የቆሙለትን አላማ ግብ የማድረስ ሃላፊነት ኢትዮጵያዊ ግዴታችን ነው!!!!

ወያኔ፤ ወያኔነትን፤ ጽንፈኝነትን፤ጎጠኝነትን፤ በአንድነት እንዋጋ!! አንድነት ሃይል ነው !!! ውድቀት ለወያኔ!!

ኢትዮፕያዊነት ምንግዜም አቸናፊ ነው!!!!!

ክብር ለጀግኖቻችን!!!

የተለያዩ የህዝብ ልጆችና ሰማዕታት አጭር ታሪክ (BIO)ይቀጥላል !!!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s