ሬዲዮ ዘመራ

የምስራች! ከዘመራ ራዲዮ

የምስራች! ከዘመራ ራዲዮ ተአማኒነት ያለው መረጃ ለአንድ ሀገር እና ህዝብ እጅግ ጠቃሚ ነው፡፡ የአንድ ሀገር ህዝብ በሀገሩ ስለሚከናወኑ ጉዳዮች መረጃ የማግኘት ያልተገደበ መብት አለው።ሀሳቡንም የመግለጽ መብት እንዲሁ።ሀገራችን ከመቼውም ጊዜ በላይ ዜጎች መረጃን የማግኘትና የመስጠት መብታቸውን ገድባለች።ይህን የተነፈገ የመናገር፣የመጻፍና የማወቅ መብት ዜጎች እንዲጎናጸፉ መታገል የሁሉም ዜጋ ሀላፊነት ነው።እኛም የበኩላችንን አስተዋጽዖ ለማድረግ “ዘመራ ራዲዮ”ን በመመስረት ወደ ስራ ገብተናል።ዘመራ ራዲዮ የሚዲያ መርሆዎችን ያከብራል።በየሳምንቱ እሁድ 15 ሰዓት ላይ ይተላለፋል። ነጻ ሚዲያዎች ለሙያ ስነ-ምግባር ታማኝ በመሆን፤ በመንግስት የተደበቁ እውነታዎችን በማጋለጥ ትክክለኛ መረጃን ለህዝብ በማድረስ እረገድ ከፍተኛ ሚና መጫወት ይገባቸዋል፡፡ በአንድ ሀገር ጤናማ ዲሞክራሲን ለማስፈን ሚዲያዎች የአንበሳውን ድርሻ እንደሚወስዱ ይታወቃል። እንደሚታወቀው ሃገራችን ኢትዮጵያ ከመቼውም ጊዜ በላይ በአስቸጋሪ እና አስጨናቂ ሁኔታ ላይ ትገኛለች። ገዥው ቡድን የህዝብ ሚዲያ የሆኑትን 100% በመቆጣጠር በየቀኑ የሀሰት ፕሮፖጋንዳ እየነዛ ህዝቡን አሰልችቶታል። ያለፉት 26 የጨለማ፣የግፍ፣ የጭቆና ዓመታት ዜጎች በሃገራቸው ጉዳይ ላይ ሃሳብን በነጻነት የመገለጽ፣ የመጻፍ፣እና የመናገር መብታቸውን ተነፍገዋል። ይልቁኑም በጻፉና በተቃወሙ ቁጥር ለእግረ ሙቅ ሲዳረጉ ተመልክተናል ። አሁን ዘመኑ በፈጠረው ማህበራዊ ሚዲያ ተጠቅመን በአገዛዙ የተገደበውን መረጃ የማግኘት መብት ለህዝባችን ሳንታክት ልናደርስ ይገባል።በዚህ መሰረት ዘመራ ራዲዮም ወቅታዊና ታዓማኒነት ያላቸውን መረጃዎች ለህዝባችን ለማድረስ ዝግጅታችን ጨርሰናል። ዘመራ ራዲዮ በየማጎርያ ቤቱ ለሚሰቃዪ ጋዜጠኞች፣ፖለቲከኛች፣የመብት ተከራካሪዎች እንዲሁም በእየ ሀገሩ ተበትነው የመብት ረገጣ ስለሚፈጸምባቸው ኢትዮጵያዊያንም ድምጽ ትሆናለች።በሃገራችን ብሎም በአለም ላይ እየተከናወኑ ስላሉ የተለያዪ ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎችን በመቃኘት ወቅታዊ ወረጃዎችን ለእናንተ ታደርሳለች፡፡ እናንተም ገንቢ አስተያየታችሁን አካፍሉን። አድራሻችን/ኢሜል/Zemraradio2017@gmail.com
ዘመራ ራዲዮ እናመሰግናለን!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s