ማህበራዊ

ተከለከለ?!  እውነት ከሆነ ነገ ቅዱስ ዮሃንስን፤ ገናን ማክበር ላለመከልከላችን ምን ዋስትና አለን?!

ተከለከለ?!
እውነት ከሆነ ነገ ቅዱስ ዮሃንስን፤ ገናን ማክበር ላለመከልከላችን ምን ዋስትና አለን?!
ይህ ነገር እውነት ነው?
መከልከል ብርቅ ሆኖብን ሳይሆን ፖለቲካዊ ኪሳራውን ከመንደር ብሽሽቅና ከእንካ ሰላንትያ በማሳነሳቸው መልስ ስለማጣለትና ሁልግዜ እንደ አዲስ ስለሚገርመኝ ነው። ከዚህ በፊት የቴዲን ኢንተርቪው ኢቢሲ ቀርፆ ካላስተላለፈው ፀቡ ከኢትዮጵያ ጋር ነው የሚል ፅሁፍ ፅፌ እንደነበር ይታወቃል። ለነገሩ የሆነ ነገር ሲያናድደኝ ምንም ግራና ቀኝ ሳላይ የምተነፍሰው ነገር ማንን እንደሚያስከፋና ማንን እንደሚያስደስት አስልቼ አላውቅም። እውነት መሆኑንና ማለት የፈለኩትን ማለት የምችል ሰው መሆኔን ብቻ ነው እራሴን የምፈትሸውና ለራሴ የማረጋግጠው። ታዲያ ያ የቴዲ የኢቢሲ ኢንተርቪው ያልተላለፈበትን ምክንያት ለማወቅ የጠየኩት ጥያቄ መልስ አግኝቶ አያውቅም…ሳይተላለፍ በዛው የመቅረቱ ጉዳይ አሁንም ይገርመኛል። በተለይ ኮንሰርትን በተመለከተ ቀድሞ ማሳወቅ ብቻ እንጂ መፍቀድና መከልከል የሚችል አካል መኖሩንም አላውቅም ነበር። በባለፈው አንዱ ኮንሰርት ተከለከለ ሲባል ምክንያቱን ለማወቅ ስንጠይቅ ብዙ ኮንሰርቶች ከመዘጋጀታቸው አንፃር እነሱም ተዘናግተው መጨረሻ ስለመጡ ከጥበቃው አቅም በላይ ሆኖ ነው እንጂ ቀድመው ቢያሳውቁ ኖሮ ማንም ሊከለክል የሚችል አካል የለም ተባልን። ይሔንን መልስ ከመቀበልና ለሌላ ግዜ ከመጠንቀቅ ውጪ ሌላ ማድረግ ስለማይቻል ለሁላችንም በሙያው ውስጥ ላለነው ትምህርት የሚሆነን መስሎን ምንም ከማለት ተቆጥበን ነበር። ዛሬ ግን ያ የለም የተባለው ከልካይ አካል ኬት መጣ?
እውነት ከሆነ ከልካዩ አካል ማን እንደሆነ ለምን እንደከለከለ ሊነገረን ይገባል። ነገ በአገር ጉዳይ ላይ የሚዘፍኑ ዘፋኞች እጣ ምን ሊሆን ነው? እቺ ግን እውነት ያቺ የኛ ኢትዮጵያ ናት?!
ያቺ ኢትዮጵያ ሲባል የቴሌቪዥናችን ዳንቴል ሳይቀር የሚፈነጥዝላት ኢትዮጵያ የት ናት?
እቺኮ ሌላ ናት፤
ሁሉም እኔ ነኝ ልክ ~አውቃለሁ ሚልባት፣
ብሽሽቅ የሚያሸት~ ብሽቅ የሚያብብባት፣
ስድብ የሚነግስ ~ተንኮል የሚያምርባት፣
እቺኮ ሌላ ናት፤
መለያየት መፍትሄ~ ጠብ ራብ የሆናት፣
ስርቆት የሚከብር~ እውነት የሚያፍርባት፣
ጠብ ከፍቅር ቀሎ~ ነብስ የሚረግፍባት፣
እቺ እገር ሌላ ናት፤
የዘር ችርቻሮ ~ ንግድ የሚጦፍባት፣
አዋቂ እንደ ጭሎ~ የሚጎተትባት
እቺኛዋ ኢትዮጵያ ~ግዴለም ሌላ ናት፣
ያቺኛዋ ኢትዮጵያ ~ እናታችን የት ናት?!፤
እግዚአብሔር ሆይ አንተ መተንፈስን አትከለክል… ስለዚህ በሰጠኸን ነፃነት እንተነፍሳለን….መንግስትህ ትምጣ ፍቃድህ በሰማይ እንደሆነች እንዲሁም በምድር ትሁን…. አሜን!!!

አምለሰት ሙጬ

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s