ፖለቲካ

የእናት ሃገር ግብር

የእናት ሀገር ግብር

ቅኝት = ቴዎድሮስ ካሳሁን

ቀን ይወጣል ብየ በቀን ተናግሬ
ማታ በጨለማ ሲነቀነቅ አጥሬ

ሠው በተናገረ ሲገረፍ በርቃኑ
ፀሀይ ባትጠልቅም ይጨልማል ቀኑ

በባለጊዜወች እጅ ስንሞት በከንቱ
ቀናችን ታሞብን ጠፍቶ መድሀኒቱ

ወጣት ያለጊዜው በቆሼ ተጠብሶ
ሌላኛው ሲበላ ለወቅቱ አጎንብሶ

የኔ እናት ሲርባት አባቴ ሲያነባ
አንደኛው ከኛ ቤት ህንፃ እየገነባ
~~~
ፅዋው ገደቡን ሲያልፍ ግፍ ሲፈስ ባገሩ
በሀብታም ቆሻሻ ድሀወች ታጠሩ

ከቶ ሰላም ላልኖር በጓሮ ሾልኬ
የገዳይን ጊዜ ግደለው አምላኬ

ለእንባችን ክብር ለግሰን ዳንኪራ
ሞቶ የሚያሸንፍ አድርገን ጠንካራ።

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s