ፖለቲካ

የቄሮ ማሳሰቢያ የህወሓትን መንደር እየናጠው ነው፡፡ ቄሮ የደወለው ደግሞ ጥግ ድረስ ይሰማል፡፡

የቄሮ ማሳሰቢያ የህወሓትን መንደር እየናጠው ነው፡፡
ቄሮ የደወለው ደግሞ ጥግ ድረስ ይሰማል፡፡

ከነገ ወዲያ ማለትም ከረቡዕ እለት ነሀሴ 17/2009 ጀመሮ እስከ እሁድ እለት ነሀሴ 21/2009 ለአምስት ቀናት መንግስት እያደረሰብን ያለውን ፈርጀ ብዙ የመብት ረገጣ ለመቃወም በተጠራው የቤት ውስጥ መቀመጥ ህዝባዊ አድማ በተመለከተ፣ የቄሮ አስተባባሪዎች የሚከተሉትን ማሳሰቢያዎች ሰጥተዋል፥

1) ረቡዕ እለት ከጠዋቱ 12 ሰአት ጀምሮ በኦሮሚያ በሁሉም አካባቢዎች ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ አይኖርም። ማንኛውም አይነት የትራስፖርት አገልግሎት አይኖርም፤ የንግድ ቤቶችም ባጠቃላይ ዝግ ይሆናሉ።

2) ይሄን ማሳሰቢያ ወደ ጎን በመተው ማንኛውም አድማውን ሊያደናቅፍ የሚችል እንቅስቃሴ ማድረግ በጥብቅ የተከለከለ ነው:: ይህን ሲያደርጉ የተገኙት ላይ በያካባቢው ያሉ የቄሮ አደረጃጀቶች እርምጃ የመውሰድ ሙሉ ሀላፊነት ተሰጥቷቸዋል። ከዚህ ጋር ተያይዞ ሊደርስ ለሚችለው የንብረት ውድመት ተጠያቂዎችም ማሳሰቢያውን ጥሰው ንብረታቸውን ሲያንቀሳቅሱ የተገኙ ባለንብረቶች እራሳቸው ይሆናሉ።

3) በተጨማሪም የትራንስፖርት አገልግሎት ስለማይኖር፣ የመንግስት ሰራተኞችም ወደ ስራ ለመግባት አይገደዱም።

4) ሆስፒታሎችን ጨምሮ ሌሎች የጤና ተቋማት ግን ይሄ በቄሮ የተጠራው አድማ አይመለከታቸውም። እነዚ ተቋማት መደበኛ ግልጋሎታቸውን ሳያቋርጡ ለህብረተሰቡ እንዲያቀርቡ ቄሮው አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ ያደርጋል።

ሰላማዊ ትግላችን ይሳካል!
እናመሰግናለን
ቄሮዎቹ

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s