ማህበራዊ

የዓመቱ በጎ ሰው 30 እጩዎች ታወቁ

የበጎ ስው ሽልማት ኮሚቴ ሰብሳቢ ሙአዘ ጥበባት ዳንኤል ክብረት ዛሬ በኢንተር ኮንትኔንታል ሆቴል በሰጡት መግለጫ 30 እጩዎችን አስታውቀዋል።

በዚህም መስረት …

1.መንግስታዊ የሥራ ሐላፊነትን በብቃት መወጣት ዘርፍ

*ዶ/ር መስፍን አርአያ፡-ለብዙ ዓመታት የአማኑኤል ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር

* አቶ ገመቹ ዳቢሶ ~ ዋናው ኦዲተር

* አቶ ማቴዎስ አስፋው ~ የአዲስ አበባ ፕላን ኮሚሽን ኮሚሽነር

2.ሚዲያና ጋዜጠኝነት

* እሽቴ አሰፋ (ሽገር ሬድዮ)

* ንጉሴ አክሊሉ (ለብዙ አመታት በኢትዮጵያ ሬዲዮ ያገለገለና በአሁኑ ሰዓት የአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ ጋዜጠኛ)

* ሽገር ኤፍ ኤም

3.ማህበራዊ ጥናት

* ኤመሪተስ ፕ/ር ባህሩ ዘውዴ ( የዘመናዊቷ ኢትዮጵያ ታሪክ ተመራማሪ፣የታሪክ መምህርና የታሪክ መጻህፍት ደራሲ)

* ዶ/ር የራሰ ወርቅ አድማሴ (በአ/አ/ዩ የነገረ ማህበረሰብ ተመራማሪ)

* ዶ/ር ካሳሁን ብርሃኑ (በአ/አ/ዩ/የፓለቲካ ሳይንስ ተባባሪ ፕሮፌሰር)

4.ለኢትዮጵያ መልካም የሠሩ የውጭ ሀገር ዜጎች

* ቦብ ጌልዶፍ (በ1977 ድርቅ ወቅት ዓለም ዐቀፍ የሙዚቃ ባለሙያዎችን አስተባብሮ ለኢትዮጵያ እርዳታ የሰበሰበ)

* ዶ/ር ካትሪን ሐምሊን (የፌስቱላ ሆስፒታል መስራች)

* ፕ/ር ጃኮብ ሽናይደር (በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የሚያገለግሉ የስዊዘርላንድ ሐኪም)

5.ቅርስ፣ባህልና ቱሪዝም

* ጉዞ አድዋ

* አቶ ገ/ኢየሱስ ሃ/ማርያም (የጉራጌ አካባቢ ቅርሶችና ባህልን በማጥናት፣በመጠበቅና ማሰባሰብ)

* የደ/ማርቆስ ዩንቨርስቲ

6.ሳይንስ

* ዶ/ር ቦጋለ ሰለሞን (የካንሰር ስፔሻሊስት)

* ኤመሪተስ ፕ/ር ንጉሴ ተበጀ (በአ.አ.ዩ ተ/ፕ/ር)

* ሎሬት ዶ/ር ለገሠ ወ/ዮሐንስ (የብልሐርዚያን መድሃኒት ያግኙ)

7.ኪነጥበብ (ቴአትር ዘርፍ)

* ተስፋዬ ገሠሠ (ታዋቂ የቴአትር ባለሙያና መምህር)

* ጌትነት እንየው (ገጣሚ፣ተዋናይ፣ጸሃፊ ተውኔትና አዘጋጅ)

* ዓለማየሁ ታደሰ(ተዋናይ፣አዘጋጅና፣የቴአትር መምህር)

8.ንግድና የሥራ ፈጠራ

* ኢ/ር ጸደቀ ይሁኔ (የፍሊንት ስቶን ባለቤት)

* አቶ ሰለሞን ሙሉጌታ (የእሽሩሩ የሥልጠና ማእከልባለቤት)

* ሸዋ ዳቦና ዱቄት

9.መምህርነት

* መ/ር ፈቃደ ደጀኔ (ከ1970 ጀምሮ በመምህርነት በመርሃ ቤቴና አርሲ ያስተማሩ፣በገጠር ት/ቤት ያሰሩ፣ልጆችን እየረዱ የሚያስተምሩ)

* መ/ር ሰለሞን ጸደቀ (በወሎቦረና፣ጋሞጎፋ፣ደ/ማርቆስ፣ወለጋ፣ጉራጌ ዞን ከ1973 ጀምሮ የሠሩ፣በገጠር ት/ቤቶችን ያሰሩ፣ለገጠር ህዝብ የልማት ተቋማትን ያሰሩ፣ትምህርታቸውን የሚያቋርጡ ተማሪዋችን የሚያስተምሩ)

* አቶ ማሞ ከበደ ሽንቁጥ (የታወቁ የትምህርት ባለሙያ፣በጎልማሶች ትምህርት ላይ ለውጥ ያመጡ)

10.በጎ አድራጎት

* መቅደስ ዘለለው (የተቀናጀ የቤተሰብ አገልግሎት ድርጅት መስራች)

* ዳዊት ሃይሉ (የውዳሴ ዳይግኖስቲክ ማእከል ባለቤት፣ለብዙ ችግረኞችን በነጻ ህክምና እንዲያገኙ ያስቻሉ)

* ሰለሞን ይልማ (በደ/ዘ/ት ከተማ ችግረኞችን በመርዳት የሚታወቅ) ሆነዋል።

***
5ኛው የበጎ ሰው ሽልማት መርሐ ግብር ነሐሴ 28 ቀን 2009 ዓ.ም በኢንተርኮንትኔንታል ሆቴል ይካሄዳል።

***
የእርስዎ የበጎ ሰው ተሸላሚ ማነው?

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s