ፖለቲካ

አግባው ሠጠኝ ማን ነው? (Gashaw Mersha)

አግባው ሠጠኝ ተወልዶ ያደገው በሠሜን ጎንደር ዞን ነው። አግባው እንደ ማንኛውም ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ሁሉ የኢህአዴግን መንግሥት በመቃወምና ኢህአዴግ በጎንደር ህዝብ ላይ የሚያደርሠውን ግፍ በማጋለጥ ይታወቃል። አግባው በተለይ ኢህአዴግ ለሡዳን ቆርሶ ሥለሰጠው መሬት ሥፋትና መጠን መረጃውን ለሚዲያ በማጋለጥ ይታወቃል። በዚህ የተነሳ ከመንግሥት ጥርሥ የተነከሠበት አግባው በተደጋጋሚ በደል ያሥተናገደ ሲሆን በሠሜን ጎንደር መተማ አካባቢ የነበረውን የእርሻ መሬቱን እንዲያጣም ተደርጓል። አግባው ይሄ ሁሉ ሳይበግረው በመታገል በ1997 ዓ.ም ቅንጅትን ወክሎ ለተወካዮ ምክር ቤት ያሸነፈ ሲሆን ቅንጅት ለአየለ ጫሚሶ በዳረጎትነት ሲበረከት እንደ ጓደኞቹ ሁሉ የአንድነትና የሠማያዊ ፓርቲ አባልና የሠሜን ጎንደር ሰብሣቢ በመሆን አገልግሏል። አግባው የሠሜን ጎንደር ሠብሣቢ ከመሆኑ በተጨማሪ የሠማያዊ ፓርቲ ብሄራዊ ምክር ቤት አባልም ነበር።

አግባው ሠጠኝ በጥር 2007 ዓ.ም የጥምቀት እለት ቦምብ ልታፈነዱ ነበር ተብለው ከጎንደር ታፍኖ በአዘዞ መከላከያ ካምፕ ለ1 ሳምንት ከፍተኛ ድብደባና ሥቃይ ካሥተናገደ በኋላ ወደ አዲሥ አበባ ማዕከላዊ በማምጣት ለ4 ወራት ማንነቱ ላይ እየተዘባበቱ ደብድበውታል። በኋላም በሽብር ክሥ ተከሶ ወደ ቅሊንጦ ዞን 1 ተዛወረ። አግባው በቅሊንጦ ማረፊያ ቤት ለተደጋጋሚ ድብደባ የተጋለጠ ሲሆን ለወራት ብቻውን ጨለማ ቤት እንዲቀመጥ በማድረግ የአዕምሮ መላሸቅ እንዲደርሥበት ጥረት ተደርጓል። አግባው ሠጠኝ በተከሠሠበት ወንጀል ነጻ መሆኑን ፍርድ ቤቱ ቢያረጋግጥም “የቅሊንጦን እሥር ቤት አቃጥላቹሃል” ተብለው ከተከሠሡት መካከል አግባው አንዱ ነው። በዚህ የተነሳ በሸዋሮቢትና ዝዋይ ማረሚያ ቤቶች ከፍተኛ ግፍን አሥተናግዷል።

አግባው በተደጋጋሚ እንደሚገድሉት ሲዝቱበት “እነሡ ከሚገድሉኝ ራሴን በርሃብ አድማ እገድላለሁ” በማለት ለ14 ቀናት ምግብና ውሃ ባለመውሠድ ራሡን ለመግደል ሙከራ አድርጓል። የርሃብ አድማ ላይ በነበረበት ወቅት በሠዎች ድጋፍ ፍርድ ቤት ቀርቦ “እኔ ነጻ ሠው ሆኘ ሣለ እንደ ወንጀለኛ እየተቆጠርኩኝ መኖርና በማንነቴ ላይ የሚደርሠውን ግፍ መቋቋም ሥላቃተኝ እራሴን በርሃብ አድማ ለመግደል ቆርጫለሁ” ብሎ ተናግሮ ነበር። በወቅቱ በሠዎች ማግባባት ምግብ እንዲበላ በማድረግ ከሞት ሊተርፍ ችሏል።

አግባው በቅርቡ ወደ ዝዋይ ተወሥዶ ከፍተኛ ድብደባ እንደደረሠበት ለፍርድ ቤቱ የገለጸ ሲሆን የማረሚያ ቤቱ ሃላፊዎች ግን “ከእሥር ቤት ሊያመጥ ሙከራ እያደረገ ነው፣ ከጥበቃ ፖሊሶች ጠብመንጃ ለመቀማት እየሞከረ ሥለሆነ ከአቅማችን በላይ ነው” የሚል ደብዳቤ ጽፏል። አግባው ግን ለህይወቴ ዋሥትና የለኝም። በጎንደር ለሚሆነው ሁሉ አግባው ተጠያቂ እንደሆነ እንደተነገረው አሥታውቋል። ሊገድሉኝ ይችላሉ እያለ እየጮኸ ነው። የሠብአዊ መብት ተሟጋቾች፣ ጋዜጠኞች፣ ፖለቲከኞች ይህን መረን የለቀቀ አግባው ሠጠኝ ላይ የሚደረግን ግፍ ተባብረን ማሥቆም ካልቻልን ነገ ቢገድሉት የማንወጣው ጸጸት ላይ እንወድቃለን!!
#በአግባው_ጉዳይ_ዝም_አንልም!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s