ፖለቲካ

አምስቱ አምባሳደሮች

አምስት አምባሳደሮች ተጠርተዋል። ለሹመት ይሁን ለሽረት አልታወቀም። አቶ ስዩም መስፍን የጤና ችግርም ስላለባቸው ሊሆን ይችላል። ለነገሩ አብዛኞቹ የህወሀት/ኢህአዴግ ባለስልጣናት ከስነልቦና በተጨማሪ በተለያዩ ውስብስብ የጤና ችግሮች በውጭ ሀገራት የሚመላለሱ ናቸው። የቻይና አምባሳደርነት እንደ ርስት ከህወሀት ሰዎች ውጭ የማይታሰብ በመሆኑ አቶ ብርሃነ ግብረክርስቶስ ስለሚተኳቸው የቻይናው ጉዳይ ብዙም አዲስ ነገር የለውም።

ሆኖም ከተጠሩት አምስት አምባሳደሮች አንደኛው ስለመመለሳቸው በእጅጉ ያጠራጥራል። የተዘፈቁበት ሙስና በአፍጢማቸው ሊደፋቸው ከተቃረቡት አንዱ እንደሆኑ ይነገራል። ከዋናዎቹ የህወሀት ዘራፊዎች ባልተናነሰ መልኩ ሙልጭ አድርገው የዘረፉ ናቸው በሚል በዝርዝር በተደገፈ ማስረጃ የሚያነሷቸው አሉ። አቶ ግርማ ብሩ።

ከህወሀት መንግስት ጋር የሚያቆም ዓላማ የላቸውም። ዘረፋና ሌብነቱ እንጂ። የሰሞኑ እስራት ለአቶ ግርማ ብሩ ምቾት የሚሰጣቸው አይደለም። ከአሳሪው የህወሀት ቡድን ጋር ከተሰለፉ ምንም አይሆኑም። በእርግጥ ያለው ሁኔታ አስተማማኝ አይደለም። ባለስልጣናት የልብ ትርታቸው ወዴት እንደሚመታ እርግጠኛ መሆን አልቻሉም። ማን አሳሪ፡ ማን ታሳሪ መሆኑ ባለየበት ሁኔታ ወደ አዲስ አበባ መመለስ ለአቶ ግርማ ብሩ የሚያዋጣ አይደለም።
ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s