ዜና

በቀለ ገርባ በካቴና ታስረው ፍርድ ቤት ቀረቡ – ዋስትናቸው ተቀባይነት ሳያገኝ ቀረ

(ዘ-ሐበሻ) የዋስትና ጥያቄያቸው ተቀባይነት ሳያገኝ ፍርድ ቤት ሲመላለሱ የቆዩት እውቁ ፖለቲከኛ አቶ በቀለ ገርባ በዛሬው ዕለት የዋስትና ጥያቄያቸው በፍርድ ቤቱ ተቀባይነት እንዳላገኘ ምንጮች አስታወቁ::

እንደ ምንጮች ዘገባ አቶ በቀለ አንዴ ዳኛ ታሟል ሌላ ጊዜ መዝገብ አልቀረበም የሚሉ አሰልቺ ምክንያት እየተሰጠ የዋስትና ጥያቄያቸው ሲጉላላ የሰነበተ ሲሆን በዛሬው ዕለት ብርቱካናማ የ እስረኛ ልብስ ለብሰው እጆቻቸው ወደፊት በካቴና ታስሮ ፍርድ ቤት ቀርበው ዋስትና ተከልክለዋል::

እንደምንጮች ዘገባ አቶ በቀለ ገርባ የታደሙበት ችሎት ከ እስረኞች በስተቀር ሌሎች ታዛቢዎች እንዲገቡ አልተፈቀደም:: ምክንያቱም ችሎቱ በ እስረኞች ሞልቷል የሚል ነበር::አቃቤ ሕግ “አቶ በቀለ በዋስ ቢለቀቁ ሕዝብ ሊቀሰቅሱ ይችላሉ” በሚል ነው ፍርድ ቤቱ ዋስትናውን እንዲከለክል የጠየቀው::

 

 

Categories: ዜና, Uncategorized

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s