ዜና

የህወሓት መንግስት ግራ መጋባቱ ተጠቆመ ! ! !

ቢቢኤን ነሐሴ 01/2009

በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች እየተካሔዱ ያሉ ህዝባዊ ተቃውሞች በህወሓት ላይ ድንጋጤ መፍጠራቸው ተጠቆመ፡፡ በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች ህዝቡ የስራ ማቆም እና ከቤት ያለ መውጣት አድማ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ የተመለከቱት የህወሓት አመራሮች፣ እንዲህ ያሉ ተቃውሞች መቋጫ ማጣታቸው እንዳሳሰባቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡ ህወሓት የህዝቡን ትኩረት ለመሳብ የተለያዩ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችን እያሰረ ቢሆንም፣ ህዝቡ ግን መብት እና ነጻነቱን አደባባይ ወጥቶ ከመጠየቅ ወደኋላ አላለም፡፡

ህወሓት በተለያየ ጊዜ አድማ እና ተቃውሞዎችን በኃይል በጠመንጃ ለማስቆም ቢሞክርም፣ ያሰበው ሳይሳካለት መቅረቱ አይዘነጋም፡፡ ህዝባዊ ተቃውሞዎች ከመቆም ይልቅ ዕለት ዕለት ተባብሰው በመቀጠል ላይ ይገኛሉ፡፡ በህወሓት መንግስት በእጅጉ የተማረረው የኢትዮጵያ ህዝብ፣ በተለያዩ አጋጣሚዎች እና ምክንያቶች በህወሓት አመራሮች ላይ ተቃውሞውን እያሰማ ይገኛል፡፡ የህወሓት አመራሮች ነፍሰ ገዳይ እና ዘራፊ መሆናቸውን ከመናገር ተቆጥቦ የማያውቀው የኢትዮጵያ ህዝብ፣ አሁን ላይ የህወሓትን ህልውና ከፍተኛ ስጋት ላይ ጥሎታል፡፡ ይህ የተገለጠለት ህወሓት በተደጋጋሚ እየተካሔዱ ያሉ ተቃውሞዎችን በምን መልኩ ማስቆም እንዳለበት ግራ እንደገባው ምንጮች ጠቁመዋል፡፡

በአዋጅ የህዝብን ተቃውሞ ማፈን የሚቻል የመሰለው ህወሓት፣ ለአስር ወራት የቆየ የአስችኳይ ጊዜ አዋጅ ማዋጁ ይታወቃል፡፡ ሆኖም ህዝቡ በአስቸኳይ አዋጅ ስር ሆኖ ከነፍሰ ገዳይ የህወሓት ወታደሮች ጋር በመታገል ተቃውሞውን ሲያሰማ መቆየቱ አይዘነጋም፡፡ በመስከረም ወር መጨረሻ አካባቢ አዋጁ በታወጀ በማግስቱ፣ በባህርዳር ከተማ ህዝባዊ ተቃውሞ ተካሒዶ እንደነበር የሚያስታውሱ ታዛቢዎች፣ ከአዋጁ በፊትም ሆነ በኋላ ህዝባዊ ተቃውሞዎች መካሔዳቸውን ይናገራሉ፡፡ ይህም የሚያሳየው ይላሉ ታዛቢዎቹ፤ ‹‹ይህ የሚያሳየው የህዝብን መብት በአዋጅ ማፈን እንደማይቻል ነው፡፡››

በዛሬው ዕለት በአማራ እና በኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች የተካሔዱ አድማዎችን ተከትሎ ህወሓት ወታደሮቹን ወደከተማዎቹ መላኩን መረጃዎች ጠቁመዋል፡፡ የተሰማራው የፖሊስ እና ወታደራዊ ሰራዊት አድማውን ምክንያት በማድረግ የተዘጋጉ አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን እና የንግድ መደብሮችን በኃይል ለማስከፈት ቢሞክሩም ሳይሳካላቸው ቀርቷል፡፡ ዛሬ የተጀመረው አድማ ነገ እና ከነገ ወዲያ ቀጥሎ እንደሚውል መነገሩ ደግሞ፣ ህወሓትን ይበልጥ ስጋት ላይ እንዲወድቅ እንዳደረገው ለማወቅ ተችሏል፡፡

Categories: ዜና, Uncategorized

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s