ማህበራዊ

ሹመተ ጵጵስና (የእግዚአብሔ እንደራሴነት)፟

የኢትዮጵያ ስልጣኔ እና ታሪክ፣ነጻነት እና ጅግንነት፣ አንድነት እና መልካም ስነምግባር፣ እንግዳ ተቀባይነት እና ፍቅር፣ ዋና ምንጭ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ነች፡፡ በሌሎች ክፍለ አለማት እንዲህ ተሟልተው የማይገኙ እነዚህ አኲሪ እሴቶች የተፈጠሩት እና ተጠብቀው የኖሩት በቤተክርስትያን ነው፡፡በቤተክርስትያን ደግሞ የተለያዪ መንፈሳዊ እውቀት ያላቸው አባቶች ለህዝባቸው ከልጅነታቸው ጀምሮ መንፈሳዊ ትምህርቶችን ይሰጣሉ፡፡በነዚህ መንፈሳዊ ትምህርቶች እየታገዙ ኅብረተሰቡን በምግባር በሃይማኖት እና በተቀደሰ ባህል መቅረጽ ፣ህዝቡም ሰለሃገሩ ነጻነት እና አንድነት መከበር እና ስለሃይማኖቱ ህልውና ጠንክሮ እንዲቆም እና ሲያስፈልግም መስዋእትነትን እንዲከፍል እነዚህ አባቶች ያደረጉት አስተዋዕጾ ከፍተኛ ነው፡፡ኦርቶዶክሳዊ ሃይማኖትንም ሆነ
ኢትዮጵያን በመልካም ሁኔታ የፈጠሩ እና ለዛሬው ትውልድ ያበረከቱ ናቸው፡፡

ባሳለፍነው ሳምንት 20 ኛው የኢ/ኦ/ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአውሮፓ መንፈሳዊ ጉባኤ በስዊድን ስቶኮልም ደብረ ሰላም መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ከሓምሌ 7 2009 -ሐምሌ 9 2009 ዓ/ም ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ ተካሂዷል፡፡ በዚህ መንፈሳዊ ጉባኤ ላይ ብፁዕ አቡነ ኤልያስ፣ ሌሎችም ከተለያዩ አለማት የመጡ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ አዕይንተ እግዚአብሔር ካህናት ዲያቆናት አገልጋዮች እና ምዕመናን በተገኙበት በአለ ሲመት ተፈጽሟል፡፡

በአለ ሲመት /ሹመት/ ለተለየ ተልዕኮ የሚሰጥ በገንዘብ፣ በንብረት እና በሰው ሀብት ላይ የማዘዝ እና የማስተዳደር ሥልጣን ነው፡፡ በተለይ ደግሞ መንፈሳዊ ሲመት ሲሆን ምድራዊ ላይደለ ሰማያዊ ተልዕኮ የሚሰጥ ሥልጣን በመሆኑ ለዚሁ መግቦት /አገልግሎት/ በትምህርታቸው ልቀት በመንፈሳዊነታቸው ብቃት እና በሃይማኖታቸው ጽናት ለተመረጡ አገልጋዮች እንደየ ደረጃቸው እና ማዕረጋቸው የሚሠጥ የሥራ ድርሻ ሲሆን ጵጵስና ደግሞ በተለየ መልኩ የመዕመናንም ሆነ የአገልጋዮች የበላይ የእግዚአብሄር እንደራሴ ሆኖ እግዚአብሔር ቅን እና እሩህሩህ እንደሆነ ሁሉ ብቅንነት እና በርህራሄ ማገልገል ነው፡፡

ሐዋርያት የሰበሰቧት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ከመጀመሪያዎቹ ሐዋርያት ጀምራ እስከ አሁንም ድረስ ከዲቁና እስከ ጵጵስና ለተመረጡ አገልጋዮቿ ሥርዓተ ሲመት ስትፈጽም ኖራለች፡፡ ቤተ ክርስቲያን በምድር ያለች የእግዚአብሔር እንደራሴ የፀጋው ግምጃ ቤት እንደመሆኗ ምእመናንን ለመጠበቅ እና ለማሠማራት እንድትችል ሥልጣነ ክህነት የምትሰጥበትን ጥብቅ ቀኖና በፍትሕ መንፈሳዊ በመደንገግ እና በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ደግሞ ዝርዝር የአፈጻጸም መመሪያ በማዘጋጀት በትምህርታቸው የበሰሉትን በሃይማኖታቸው ነቅ በምግባራቸው ጠንቅ የሌለባቸውን አገልጋዮች ስትሾም ኖራለች፡፡ ወደፊትም ትኖራለች!

በኖርዌይ /ኦስሎ/ ቅዱስ ገብርኤል እና አቡነ ተክለሃይማኖት አስተዳዳሪ የነበሩት መለአከ ብስራት ቆሞስ አባ ሃብተእየሱስ ለገሰ አቡነ ሕርያቆስ በመባል ተሹመዋል፡፡ ይህ በስደት ላሉ ወገኖች ሆነ ለዚ ላበቃቻቸው ቤተክርስትያን እጅግ በጣም ደስ የሚያሰኝ ዜና ነው፡፡ አቡነ ህርያቆስ ከላይ እንደገለጽኩት በትምህርታቸው የበሰሉ በሃይማኖታቸው ነቅ በምግባራቸው ጠንቅ የሌለባቸው በመሆናቸው ለዚህ ሹመተ ጵጵስና ማዕረግ በቅተዋል አቡነ ሕርያቆስ በዜማ፣አቋቋም በዱጓ፣በትርጓሜ እና በሌሎችም እውቀቶች የበሰሉ አባት ሲሆኑ በኦስሎ ቅዱስ ገብርኤል እና አቡነ ተከለሃይማኖት ቤተክርስትያን የሚገኙ በኖርዌ አገር የተወለዱ ህጻናትን በማስተማር ለዲቁና በማብቃት ቤተክርስቲያኒቱ የነበረባት የዲያቆናት አገልጋዮች ችግር እንዲፈታ ከፍተኛ አስተዋዕጾ አድርገዋል፡፡ አሁንም በማስተማር ላይ ይገኛሉ፡፡ ለዚ ማዕረግ እና ክብር የበቁት አባታችን የአገልግሎት ዘመናቸው የተባረከ ይሁንላቸው፡፡እንግዲህ ለቤተክርስትያን መተንፈሻ ሳንባ አባቶቻችን ናቸው እና እ ረጅም እድሜ ይስጥልን

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s