የእኔ ሃሳብ

“መልካምነት ” ደስ ሲል!!

እኔ መልካም እንዳደረግሁላችሁ እናንተም መልካም አድርጉ ፣መልካም ስም ከመልካም ሽቱ ተበልጣለች፣ መልካም ያደረጉ በዙ ሴቶች አሉ አንቺ ግን ከሁሉ ተበልጫለሽ፣ የህይወታችን መርህ በሆነው በመጽሃፍ ቅዱስ መልካምነት በበዙ ቦታ ተጠቅሷል
ለኔ መልካምነት በብዙ መልኩ እተረጉመዋለው በመጀመርያ ደረጃ መልካምነት የተሰጠን ከክርስቶስ ነው ብዙ ጊዜ ኑሮአችን ያልጣፈጠው መልካምነት የሚባለው ጨው በውስጣችን ባለመኖሩ ይሆናል ፡፡ ምክንያቱም መልካምነት ሀገር የለውም፣ ድንበር የለውም ፣ጥቁር ነጭ አይልም ፣በነፃ አገልግሎት ወገንን ማስደሰት፣ ሁል ጊዜ ለሰው በመስጠት በማድረግ እንጂ ዉለታ የማይጠብቅ፣ የወገኑ ደስታ የሚያስደስተው፣የወገኑ ርሃብ የሚርበው፣የወገኑ ጥማት የሚጠማው፣በእያንዳንዱ ችግር ውስጥ እኔ ብሆንስ እያለ በማሰብ የሰዎችን ችግር በመፍታት ደስተኛ የሚሆን ፣ደሃ አይል ሃብታም፣ ሴቱም ወንዱም ፡በእኩል የሚያይ የማያዳላ እራስ ወዳድነት የማይስማማዉ ልዩ ነው “መልካምነት “

ለታዋቂው የግጥምና ዜማ ደራሲ ለክቡር ዶር አበበ መለሰ ኩላሊቱን ሳሚ የተባለ ወጣት ለገሰው በህይወት እንዲኖር ምክንያት ሆነው!! አቤት ታደሎ ይህን መልካም ነገር ስላደረገ ያለው የህሊና ሰላም ፣ፍቅር ፣ደስታ፣ጤና ….ብዙ ብዙ … በገንዘብ የማይተመን ፍቅር በዚህ ወንድም ወንድሙን ለገንዘብ፣ ለሃብት ፣ለአላፊ ነገር፣ እየለወጠ ገሎ መክበር በሚታይበት፣ዜጎች ነጻነታቸውን ተነፍገው በእኔ አውቅልሃለሁ በሚረገጡበት፣
ለምን ጻፋችሁ ለምን መብታችሁን ጠየቃችሁ እየተባሉ በገዛ ወንድሞቻቸው በጭካኔ በሚደበደቡበት፣ ጥፍራቸው እየተነቀለ በብዙ መከራ በመሰቃየታቸው ሞትን በሚናፍቁበት፣በየማጎርያ ቤቱ ካለሃጥያታቸው በወህኒ ተጥለው በሚሰቃዩበት በዶፍ ዝናብ በክረምት ከቤት ንብረታቸው እየተፈናቀሉ በጭካኔ ደጅ በሚጣሉበት፣ እና የሚሰማው የሚታየው በሚዘግንንበት በዚህ ክፉ ዘመን ያልኝን ላካፍል ብሎ ህሊናን አሳምኖ በንጹህ ኢትዮጵያዊነት ያደረገው መልካምነት መገለጫ ቋንቋ የለውም መልካምነት የህሊና ሰላም ነው መልካም መሆን ደስተኛ ያደርጋል ሳሚ እንዳንተ አይነት መልካሞችን ያብዛቸው!!ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር የለም!!

Categories: የእኔ ሃሳብ

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s