ሬዲዮ ዘመራ

ስለ ሸገር የምለው አለኝ

“ነፍጠኛው ስርዐት ስማቸውን ቀየራቸው ከተባሉት ቦታዎች ውስጥ መርካቶ፣ ፒያሳና ካዛንቺስ ይገኙበታል፤ እነዚህ ጣሊያናዊ ስሞች ናቸው፤ የክሪስፒና የምኒልክ፣ የተፈሪና የሙሶሎኒ ዝምድና ይጣራልን፡፡

* የታሪክ መፅሐፍቱ “Oromo migration movement” ሲሉን ከርመው አይ “Oromo population movement” ነው ብለው አስተካከሉና መዳ ወላቡ ከህዝቡ መስፋፋት በፊት የኦሮሞ ማዕከልና መነሻ መሆኑን ነገሩን፡፡ መስፋፋቱ ደግሞ እ.ኤ.አ ከ1522-1618 ነው እስከዛ ድረስ አዲስ አበባ የማን ነበረች?

* ከክርስቲያኑ ግዛተ አፄ እና ከሙስሊሙ የ16ኛው ክ/ዘ አታካችና ረጅም ጦርነት በኋላ የሁለቱም ወገን ጃይንቶች ገላውዲዎስና ኢማም አህመድን ሞት ተከትሎ ተዋጊዎቹ መዳከማቸው ለኦሮሞ ግስጋሴ አይነተኛ ሚና ተጫውቷል፡፡ አፄ ሚናስ የጦራቸውን መሳሳት ተከትሎ የኦሮሞ ተዋጊዎችን ከመግጠም ወደ አባይ ማዶ መሻገርን ሲመርጡ ሰሜን ሸዋ በኦሮሞች እጅ ወደቀ፤ ኢምር ኑር ኢብን ሙጃህዲን ደግሞ ሀረር ገብተው ከተሙ፤ ኋላም የኦሮሞችን ግስጋሴ ለመግታት ኢሚር ኑር ኢብን ዳውድ የሀረር ግንብን አሳነፁ የቀረው የሙስሊሙ ግዛት በኦሮሞ ተዋጊዎች ተያዘ፣ አሁንም እንደተያዘ ነው፡፡

* አፄ እያሱ ሁለተኛ “ሁሉም በያለበት ይርጋ” ሲሉ ያስነገሩት አዋጅ የኦሮሞን ግስጋሴ ቢገታም የያዙትን አካባቢ እንዲለቁ አላስገደደም፤ በዚህም ወሎ አካባቢ ብዙ ቦታዎች በኦሮምኛ ስያሜያቸው  እየተገለገሉ ይገኛሉ፡፡

* በዚህ አጋጣሚ ግን የኛ ሠፈር ስያሜ አልተቀየረም፤ እንደደረሠኝ መረጃ አካባቢውን ይገባናል ያሉ ሁለት ብሔረሰቦች እስኪስማሙ ተብሎ ነው አሉ፡፡ የመኮንኖቹ መኖሪያና ጠቅላይ ሚኒስቴር ቢሮ መሀል የሚኖረውን ማወቅ ለእናንተ ተትቷል፡፡

ቢኒያም ተስፋዬ (binikonjo5@gmail.com)

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s